@adamabusxgu: #tigraytiktok🇻🇳🇻🇳tigraytiktok የህወሓት የእብሪት ፖለቲካ እና የጥፋት ስሌት ************** በደርግ ውድቀት ማግስት “አጥፍቶ መጥፋት” በሚል ርዕስ በዮሐንስ ሙሉጌታ (የጋዜጠኛና ደራሲ ሙሉጌታ ሉሌ የብዕር ስም) የታተመውን መጽሐፍ ያነበበ ሰው፣ የደርግ ሥርዓት የነበረበት የሥልጣን አያያዝ ችግርና ግትርነት እንዴት ለራሱ ውድቀት ምክንያት እንደሆነው በግልጽ ይረዳል። ደራሲው በወቅቱ በፕሮፓጋንዳ ይቀርብ የነበረውን ገጽታ ወደ ጎን በመተው፣ የሥርዓቱን ውስጣዊ ድክመትና የአመራሩን ክፍተት በጥሩ ትረካ አሳይቶናል። ከሦስት አሥርት ዓመታት በኋላም፣ ህወሓት በተመሳሳይ የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ማለፉን መታዘብ ይቻላል። ሀገርን ለ27 ዓመታት በበላይነት የመራና ራሱን “አውራ ፓርቲ” አድርጎ ይገልጽ የነበረ ድርጅት፣ የጊዜውን ለውጥ ባለመረዳትና በውስጣዊ የፖለቲካ ስሌት ስህተት ምክንያት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከነበረበት የሥልጣን ማማ መውረዱ፣ የደራሲውን “አጥፍቶ መጥፋት” የሚለውን የታሪክ ርዕስ ዳግም የሚያስታውስ ክስተት ሆኗል። የድርጅቱ የረጅም ጊዜ የፖለቲካ ባህል የውይይትና የድርድር አማራጮችን ከማስቀደም ይልቅ፣ ልዩነቶችን በኃይል ለመፍታት መሞከር ነበር። ይህ አካሄድ ደግሞ ለትግራይ ሕዝብም ሆነ ለመላው ኢትዮጵያ ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሏል። ባለፉት ስምንት ዓመታት የተከሰቱት ፖለቲካዊ ክስተቶችም የዚህ የተሳሳተ የፖለቲካ ስሌት ማሳያዎች ናቸው። በ2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ የመጣውን የፖለቲካ ለውጥ ተከትሎ፣ ህወሓት የሰላም፣ የዕርቅና የለውጡ አካል እንዲሆን በርካታ ሀገራዊ ጥሪዎች ቀርበውለት ነበር። ሀገርን የመራትና በዓለም አቀፍ መድረኮችም የተወከለበትን የፖለቲካ ምህዳር በሰላማዊ መንገድ እንዲቀላቀል የተዘረጉለትን የእርቅ እጆች በሙሉ በእብሪትና በንቀት ገፍቷል። የለውጡን ሂደት ለመቀበል ከመዘጋጀት ይልቅ በትግራይ ክልል አጥር አጥሮ በመቀመጥ ኢትዮጵያን ለማወክ፣ ግጭቶችን ለማነሳሳት እና ሀገራዊ ተቋማትን ለማዳከም ቀን ከሌሊት ሠርቷል። የድርጅቱ ቆሞ ቀርነት እና ስሌት አልቦነት ጎልቶ የወጣው በሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ላይ በፈጸመው ያልተጠበቀ ጥቃት ነው። አብረውት የኖሩትን የትግራይን ሕዝብ ከጥቃት ሲጠብቁ የነበሩትን የመከላከያ አባላት “መብረቃዊ ጥቃት” በሚል ሰበብ ከጀርባ በመውጋት በታሪክ ያልታየ የክህደት ድርጊት ፈጽሟል። ይህ ውሳኔ ድርጅቱ የታጠቀውን ጦር ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ የትግራይን ሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ለአደጋ የዳረገ አጥፍቶ የመጥፋት ስሌት ነበር። ህገወጡ ህወሓት ከፍጥረቱ ጀምሮ የሰላም ቋንቋ የማይገባው፣ የትግራይን ወጣት ለጦርነት ማገዶ በማድረግና በሞታቸው የሚያተርፍ ድርጅት መሆኑን በተደጋጋሚ አሳይቷል። በመጀመሪያው ጦርነት የታየውን እጅግ አሰቃቂ የሰው ሕይወት መጥፋት ሳይማርበት፣ በሁለተኛውና በሦስተኛው ዙር ጦርነቶች አሁንም በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችንና ታዳጊዎችን ወደ ጦርነት ማግዷል። የሰላም አማራጮችን እና የፌደራል መንግሥቱን የሰብዓዊ ተኩስ ማቆም ውሳኔዎች እንደ ድክመት በመቁጠር በእብሪት ተወጥሮ እስከ አፋርና አማራ ክልሎች ዘልቆ በመግባት ከፍተኛ የንብረት ውድመት፣ የዜጎች ግድያ እና አስነዋሪ ድርጊቶችን ፈጽሟል። ይህም ድርጅቱ ለትግራይ ሕዝብም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ዓይነት ደንታ እንደሌለውና ብቸኛ ዓላማው ወደ ሥልጣን መመለስ ወይም አጥፍቶ መጥፋት እንደነበር ያረጋገጠ ነው። የአቶ ሙሉጌታ ሉሌ “አጥፍቶ መጥፋት” መጽሐፍ የደርግን ውድቀት እንዳሰየን ሁሉ፣ የህወሓት መጨረሻም በገዛ እጁ በለኮሰው እሳት ተለብልቦ መጠናቀቅ ሆኗል። የፖለቲካ ንቀት፣ የበላይነት አስተሳሰብ እና የትግራይን ሕዝብ ለራሱ የሥልጣን ማቆያ መጠቀሚያ የማድረግ አደገኛ አካሄድ ድርጅቱን ወደ ታሪክ ማህደር አሰናብቶታል። በሕዝብና በሀገር ላይ የተፈጸመው ይህ የጥፋት ስሌት አካሄድ እንዳይደገም ለትውልድ የታሪክ መማሪያ ሆኖ ይኖራል። በጌቱ ላቀው #Ethiopia #EBC #Tigray #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

casmaro ቆርጠህ ላክለት man United🤫
casmaro ቆርጠህ ላክለት man United🤫
Open In TikTok:
Region: ZA
Monday 26 October 2026 13:30:31 GMT
13833
945
31
221

Music

Download

Comments

user5015804544836
Eneka :
አብይን የሚጠብቅ ጌታ አይተኛም አያንቀላፋም የግብፅ ሴራ ይፈርሳል ሀገሬም ማደጓ አይቀርም፡፡
2026-10-27 06:32:55
1
aabbq235
1234 :
1111111111111111111
2026-10-26 19:57:07
0
roj01jf
ابو خلود :
👌 يحفظك الله
2026-10-26 21:03:00
2
mazzbacha
maza :
2026-10-27 07:49:16
0
user1510132062213
seman.hassen :
yes
2026-10-26 22:35:43
0
abram.abram26
HD :
2026-10-27 09:44:06
0
abush6484
abush :
🥰🥰
2026-10-27 08:16:57
0
tedilophiso
Tedi Lophiso :
yeeesse🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-10-26 18:58:10
0
teferi.hailu
Teferi Hailu :
በቃ አውነት ነው
2026-10-26 22:24:55
0
hukma173
rhmaጎደሬዋነኝ💪💪❤💛💚 :
2026-10-26 21:07:40
0
sabir.awol96
Sabir Awol :
2026-10-26 20:44:23
0
f65882
f :
🥰🥰🥰🥰🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
2026-10-26 18:44:09
0
abush6484
abush :
2026-10-27 08:16:49
0
sanyikushi1
dhalotta Khushi :
👍👍👍
2026-10-27 09:03:17
0
mohmmedmohmmed9516
سبحن الله ولحمدلله ولاحول ولا :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-10-27 07:10:01
0
teddy..adimasu..k
teddy. adimasu. king :
🥰🥰🥰
2026-10-27 06:16:59
0
eyasu.27
Eyasu 27 :
👍👍👍
2026-10-27 05:33:18
0
biruk.yegeta.liji
Mr B f :
❤️❤️❤️
2026-10-27 04:04:57
0
eyasu.27
Eyasu 27 :
🥰🥰🥰
2026-10-27 05:33:15
0
yemuu.halima
ላጪር ሂወት እረጂም ጉዞ አይ አይዱኒያ😥 :
💝💝💝
2026-10-27 03:31:35
0
user35122443388003
أحمد :
😂😂😂
2026-10-27 02:33:20
0
amiza.alla
Hamza Dlea :
😳😳😳
2026-10-27 00:46:46
0
shukure.mohammed
Shukure.Mohammed :
[Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming]
2026-10-27 00:37:08
0
dachasaalemu1
Dachuu Alamuu :
❤️❤️❤️
2026-10-26 13:37:04
0
To see more videos from user @adamabusxgu, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About