@godwillprovide2116: ሞት ይብቃን ! ሙቶች እንዴት ናችሁ እኛ ደኅና ነን ፣ ከቤተስኪያን ጓሮ ሰው ዘርተን ከረምን ፣ ከቤተስኪያን ጓሮ ሰው እየዘራችሁ ፣ ሲበሰብስ እንጂ ሲበቅል አላያችሁ ፤ ረገጡኝ ብለህ ምድር አትቆጣ ፣ ይህ ሁሉ ያንተ ነው ልብሱን ቢያነጣጣ ፤ ረገጥኩሽ ምድር መልሼ መልሼ ፣ እከፍለው የለ ወይ መላ አካሌን ክሼ ፣ እነርሱ እየሄዱ እየሸኘናቸው ፣ እንዴት ይታዘቡን የምንቀር መስሎአቸው ፤ በሉ እናንተ ሂዱ እኛም ወደዚያው ነው ፣ ድሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው ።              ና ምነው ፣ ና ምነው !!! የሞቱት የሞቱ አይደሉም ፣ ዝም ቢሉም በሕሊናችን እየተጫወቱ ነው ። ለጆሮ መናገር አቁመው ለልባችን እየተናገሩ ነው ። የምንቀር መስሎን የገፋናቸው ፣ ይደላን መስሎን እንጀራ የነጠቅናቸው ፣ ያንዱ ላንዱ ይሆን መስሎን ስማቸውን ያጠለሸናቸው በውስጣችን ያጫውቱናል ። ሞታቸው ሞታችንን ያሳስባል ። እነርሱ ሲሞቱ ሁሉም ነገር ምቹ የሚሆን መስሎን ነበረ ። መከራው ለቋሚው ይብሳል ። የሞተው አንድ ጊዜ ሲሞት ገዳይ ግን ዘጠኝ ጊዜ ይሞታል ፣ ሞትን ተመኝቶ ያጣታል ። ፍርደ ገምድል ዳኛ ቢለቀው ደም ያሳድደዋል ። የወኅኒው ደጃፍ ቢከፈትለት የሕሊና እስር ቤት ሥራውን ይጀምራል ። ነጻነት የውስጥ መለቀቅ ነው ፣ ይህም የሚገኘው ለእውነትና ለቅንነት በመኖር ነው ። ሟችስ ይሙት ገዳይ መግደል አይሰለቸውም ወይ  እስኪባል በምድሪቱ ላይ ደም ይፈሳል ። አገሩ ላይ ሁኖ አገሩ የሚናፍቀው ወገን በእንባ ይርሳል ። የሞቱት ዐረፉ እኛ ግን እየተናወጥን ነው ። እነርሱንስ እኛ ቀበርን እኛን የሚቀብር ማን ይሆን ? የሚል ጥርጣሬ እየወዘወዘን ነው ። አዎ ሙታን እንዴት ናችሁ  እኛ እያነቡ እስክስታ አድክሞናል ። በአንድ ዓይን እያለቀሱ በአንድ ዓይን መሳቅ አስክሮናል ። ሙታን እንዴት ናችሁ ? ስለ ስሙ የተገደላችሁ ፣ ያንን ዋጋ ከፋይ ጌታ አገኛችሁት  እናንተስ አምናችሁ ሞታችሁ ፣ እኛ ክደን እንዳንኖር እንፈራለን ። ለሃይማኖት መሞት ሳይሆን መኖር አቅቶናል ። የእናንተ መከራ ለሰዓታት ነው ፣ የገዳያችሁ ስቃይ ግን ለዘመናት ነው ። ግድያ ምን ስም ይሰጠው ፣ በሕግ ወንጀል ፣ በባሕል ነውር ፣ በሃይማኖት ኃጢአት ነው ። ትክክለኛ ገዳይ ፣ ትክክለኛ ሟች የለም ። የሕይወት ባለቤት እግዚአብሔር ነው ። ዝማሬዎቻችን ማደንዘዣ ፣ ስብከቶቻችን ማፍዘዣ እንዳይሆኑ ማሰብ ያስፈልገናል ። እየሞትን “አለን…ሁሉን አልፈን” እያልን መዘመር ፣ “ሲገድሉን እንበዛለን” እያልን በመቀነሳችን ላይ ካፌዝን ተገቢ አይደለም ። በዚህ ዘመን ላይ ሰው ስለ እምነቱ መሞት አይገባውም የሚል የአሳብ ልዕልናን መያዝ አለብን ። እግዚአብሔር ፈቅዶ ስለ ሰጠው ማንነቱ ሰው የሞት ዕጩ መሆን አይገባውም ። ይህ ሥልጣኔን ፣ ሰውነትንና ሃይማኖትን የሚጋፋ ነው ። ያልተወለደ ፣ የዜግነት ድርሻ የሌለው ንብረት ማፍራት ይችላል እያልን ዜጋው መኖሪያ ካጣ ያልሠራነው ብዙ ሥራ እንዳለ ማሳያ ነው ። ስለ ሞቱት ሰማዕታት ብለን ዘምረናል ። በሞታቸው ላይ ሌላ ሞት እየመጣ እንጂ ሞታቸው ሲያፈራ እያየን አይደለም ። ሀገረ እግዚአብሔር በተባለች ምድር ላይ ካህን በመንበሩ ላይ ሲገደል እንደ መስማት የሚያስፈራ ነገር የለም ። የአንድም ሐዋርያ ደም ባልፈሰሰባት ምድር ላይ የክርስቲያን ደም ዕለታዊ ግብር ሲሆንባት ሊቆጨን ይገባል ። አብርሃም ሊንከን፡- “በሌላው ሰው ጀርባ ላይ ጅራፍ ሲያርፍ ለማይሰማው ሰው አዝንለታለሁ ብሏል ። ከሞቱት በላይ የሚያሳዝን ሰው በሌላው መከራ ስሜት አልባ የሚሆን ሰው ነው ። ግድያ እንደ ወረርሽኝ ነው ፣ ጥበትም ማለቂያ የለውም ። ዳር የሚሰማው ችግር አንድ ቀን ቸልተኛው በር ላይ ይቆማል ። አለሁ እያሉ ተበልተው ያለቁትን ፣ የክርስቲያን አገር የነበሩትን ማሰብ አስፈላጊ ነው ። የጥንትዋ ኑቢያ ፣ ግብጽ ፣ ቱኒዝያ ፣ ሊቢያ ፣ አልጀርስ የክርስቲያን መዲና ፣ የቀኖናት መፍለቂያ ፣ የሊቃውንት መገኛ ፣ የክርስትና ዋልታ ነበሩ ። እንደ ጋንግሪን እያደገ መጥቶ ጥፋት ጨረሳቸው ። ኢትዮጵያ ከእነዚያ እንደ አንዱ የማትሆንበት ምንም ምክንያት የለም ። ኢትዮጵያ የምትድነው እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ስትዘረጋ ብቻ ነው ። ዛሬ እጆችዋን የዘረጋችው ወደ ኃያላን አገራት ነው ። የተረከብናት ይህች የከበረች ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አደጋ ላይ ናት ። ከውጭ አደጋ በላይ በውስጥዋ ያለው መከፋፈልና የእረኛና የመንጋ ረሀብ ሊጎዳት ተቃርቧል ። እረኛም መንጋም እንዳታጣ ትልቅ ስጋት ውስጥ ገብታለች ። ይህ ቀን እንደሚመጣ የተናገሩና ያሳሰቡ አባቶች ነበሩ ፣ ሁሉም ተገፍተው አልፈዋል ። እነርሱ ዐርፈዋል እኛ እየተወዘወዝን ነው ። ያመንኩትን አውቀዋለሁ የሚል አማኝ የለንም ። በእኛ እውቀት ዐርፎ ፣ በበዓላት ድምቀት ተስቦ የሚመጣ አማኝ እያበዛን ነው ። ወጣቱን የት ነህ ? ብለን አልፈለግነውም ፣ ሲመጣም አዋክበው የሚያስወጡ አጋፋሪዎችን አቁመናል ። እንኳን የካደውን ልናሳምን ያመነውንም ለማስካድ ዳር አድርሰነዋል ። ቤተ ክርስቲያኑን ሳይጠላ እኛን እየጠላ የራቀን ብዙ ነው ። የእኛ መልከ ጥፉነት የቤተ ክርስቲያንን ውበት ሸፈነው ። ቤተ ክርስቲያን ትልቅ የምጥ ዘመን ላይ ናት ። ለማልቀስም ቀኑ የረዳን አይመስልም ። “ጦጣ ታስራ ትዘፍናለች” እንዲሉ ሆታችንና እልልታችን ቀኑን ያየ አይደለም ። ሁላችንም እንሞታለን ፣ ታሪክን ፣ ሃይማኖትን ፣ ባሕልን ፣ ቅንነትን ፣ አንድነትን ገድለን መሞት ግን የሞት ድራቢ ነው ። የፍቅር ተቃራኒው ጥላቻ ይመስለናል ፣ የፍቅር ተቃራኒው ግን ግዴለሽነት ነው ። በአካል ከሚሞቱት በላይ ርኅራኄ በእኛ ልብ ውስጥ ሲሞት ዘላለማዊ ሞት ነው ። ራስን በሌላው ሰው ቦታ አድርጎ አለማስቀመጥ ከሰውነት ማኅበር በፈቃደኝነት መልቀቅ ነው ። ምድሪቱ ሟች ጠግባለች ፣ የሚሞተው ሰው ይብቃ ! ለፈጠርከው የምትራራ ና ምነው ፣ ና ምነው !!! ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም. $&

የዳዊት  ልጅ ሆይ ማረን🙏
የዳዊት ልጅ ሆይ ማረን🙏
Open In TikTok:
Region: SA
Tuesday 27 October 2026 19:19:51 GMT
1469
314
86
44

Music

Download

Comments

saraayvv043
sara :
በስማማም😭😭😭😭😭😭
2026-10-30 09:27:32
1
user17351494593818
ለምለም ለምለም :
የሞቱት አንዱን ይዘዋል የቁሙት ግን በቁም የሞቱ ናቸው እነሱ ናቸው የሚያስጨርሱን የበጉ እረኞች ሞተዋል😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2026-10-29 11:19:57
1
ema193778
ሩሀማ :
2026-10-29 23:53:04
1
tsediya.ejare
T _E_ G_ M_ S _N🥰 :
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭ፍትህ ለአርስ ኦርቶዶክስ 😭😭😭😭😭😭
2026-10-28 18:10:53
1
cell15015
ንግስት :
እኛስ ደህናነ ይሆን😭😭😭😭😭😭አቤቱ ማርን የዳዊት ልጂ ሆይ ማርኝ
2026-10-29 11:14:10
1
user7869351933134
በዝምታሽ አወዛግቢአቸዉ በስኬትሽአስደምሚቸዉ :
ነፍስ ይማር
2026-10-30 08:34:59
1
kal27633
እርግቧ🕊🕊 (ሙሉ ሸዋ🇨🇬🇨🇬🇨🇬) :
😢😢😢😢
2026-10-30 08:59:15
1
kidst.mmmm
ልጅ Zድ ይፋቴዋ ♥️ :
ኡፍፍፍፍፍፍፍፍ😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2026-10-27 21:42:35
0
zola866
እረኛዬ ነክ አባቴ😍 :
😭😭😭😭
2026-10-30 00:32:36
1
tsinukalcom2
Tsinukal :
egzabeir maren
2026-10-28 15:39:15
1
user4167685844098
እቱዬ የማርያም ልጅ 🙏 :
😭😭😭
2026-10-28 16:24:29
1
derartu.girma217
derartu👌👌 :
faradii Attii waqayoo 😥😥😥😥😥😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭🤦🤦🤦🤦🤦🤦🤦🤦🤦
2026-10-29 10:25:49
0
user11425744132231
ሩ🕊ሃ🕊ማ🕊 :
ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ
2026-10-27 21:36:31
0
user6744394558498
እግዚአብሔር ፍቅር ነው :
እፍፍፍፍፍፍ😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2026-10-29 04:59:08
0
yara59025
ሲያልፋ እናወራዋል :
አይይይይይይይይይይይ ያዳምልጂ እህህህህህህህህህ
2026-10-28 08:43:35
0
elsebtfekedu
@19ኤልደነ19@@// :
2026-10-28 17:43:52
0
lamrot1288
Lamrot :
2026-10-29 12:30:23
1
americaadane
✝️እመ ብርሀን እናቴ አደራሽን⛪️🛐🇪🇹 :
😭😭😭😭😭😭💔
2026-10-27 19:38:12
0
user7128428679753
እታግ ነኝ የኤፍሬም ሸጋ እናት :
እፍፍፍፍፍ🥺🥺😢😢😢😢😢
2026-10-27 22:59:17
0
user212033864
ዛሬም ተመስገን :
2026-10-30 18:27:59
0
bizunesh79
የልጅነት ኀጢያትና መተላለፍ አታስብብኝ :
አቤቱ ስለ ስምህ ብለህ ታደገን😥😥😥😥😥
2026-10-28 11:54:12
0
user2501987232126
የኔ❤❤❤ :
ፍርድንፈጣሪላተነውአባቴ፣😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2026-10-28 02:34:54
0
poiuytghjklm87
✟ቅን ልቧ ✟ የወግድዋ🤘ባለመሀተቧ✟◉⓳◉ :
😭😭😭😭😭😭😭
2026-10-27 21:33:00
0
To see more videos from user @godwillprovide2116, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About