@lolapxt2:

lola
lola
Open In TikTok:
Region: FR
Thursday 29 October 2026 18:33:34 GMT
221
28
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @lolapxt2, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

አንድ ጠቢብ ሰው በጉዞ ላይ እያለ መኪናው ከአንድ መንደር አቅራቢያ ሲደርስ ተበላሸበት። እርዳታ ለመጠየቅ ወደ መንደሩ ሰዎች ቀረበ።  ወደ መንደሩ ሲገባ አንድ ሽማግሌ ሰው ከጎጆው አጠገብ ተቀምጦ ዶሮዎችም በዙሪያው እህል ሲለቅሙ ተመለከተ። ጠቢቡ ሰው ከዶሮዎቹ መካከል አንድ ያልተለመደ ነገር አስተዋለ—አንድ የጭልፊት ጫጩት እንደ ዶሮዎቹ አብሮ እህል ይለቅም ነበር።  ጠቢቡ ተገረመና ስለ መኪናው መበላሸት ሙሉ በሙሉ ረስቶ ወደ አዛውንቱ ሰውየ ቀርቦ፣ “አንድ ጭልፊት እንደ ዶሮ  መሬት ላይ እህል እንዴት ሊለቅም ይችላል?” ሲል ጠየቀው።  አዛውንቱ ሰውም መለሰለት፣ “ይህ የጭልፊት ጫጩት ከተወለደ  አንድ ቀን ሳይሞላው ነው በተራራው አቅራቢያ ቆስሎ ያገኘሁት። ወደ ቤት አምጥቼ ቁስሉን አሰርኩለትና በዶሮዎች መካከል አስቀመጥኩት። ለመጀመሪያ ጊዜ ዓይኖቹን ሲከፍት፣ በዶሮዎች ጫጩቶች ተከቦ ራሱን አገኘው፣ ስለዚህ እሱ ራሱ ዶሮ እንደሆነ ማሰብ ጀመረ። ልክ እንደነሱ እህል መለቀም ተማረ።”  ጠቢቡ ሰው አዛውንቱን ሰውዬ፣ “እባክህ ይህን ጭልፊት ስጠኝ—እንደ ስጦታ ወይም በገንዘብ። ላጠናው እፈልጋለሁ” ሲል ጠየቀው።  አዛውንቱም የጭልፊቱን ጫጩት በስጦታ ሰጠው።  ጠቢቡ ሰውም መኪናውን ካስተካከለ በኋላ፣ ወደ ቤቱ ተመለሰና ሙከራውን ጀመረ።  በየቀኑ፣ ጭልፊቱን ከቤቱ ጣራ ላይ ይወረውረዋል፣ ነገር ግን ጭልፊቱ ክንፎቹን ይሰበስባል፣ እንደ ዶሮ ራሱን ያንደፋድፋል፣ እና መሬት ላይ ይወድቃል።  በየቀኑ፣ ያለ ምንም መታከት፣ ጠቢቡ ሰው ጭልፊቱን ከፊቱ ባለ ጠረጴዛ ላይ ያስቀምጠውና፣ “አንተ ጭልፊት ነህ እንጂ ዶሮ አይደለህም። ማንነትህን እወቅ” ይለው ነበር።  ሰውየው በሚችለው በማንኛውም ቋንቋ ይህን ይለው ነበር— “አንተ ጭልፊት ነህ እንጂ ዶሮ አይደለህም። እውነተኛ ማንነትህን ለመገንዘብ ሞክር!”።  ይህንን ልምምድ ለብዙ ቀናት ቀጠለ።  በመጨረሻም፣ አንድ ቀን፣ ጠቢቡ ሰው ጭልፊቱን ወደ ከፍተኛው የተራራ ጫፍ ወሰደው።  “ራሰህን እወቅ። አንተ ጭልፊት ነህ” ሲል ለጭልፊቱ አንድ ጊዜ ደገመለት። በእነዚህ ቃላትም፣ ከገደሉ ወረወረው።  ጭልፊቱ በፍርሃት ክንፎቹን ሰበሰበ፣ ራሱን እንደ ዶሮ አጎንብሶ፣ ዓይኖቹን ጨፈነ።  ነገር ግን ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ፣ ዓይኖቹን ከፈተ እና አየ መሬቱ አሁንም ሩቅ ነው።  ክንፎቹን በስሜት አፈራረቀ—ልክ እንደ አንድ ሰው መዋኘት እንደማይችል ወንዝ ውስጥ ሲወረወር አይነት።  ብዙም ሳይቆይ፣ በአየር ውስጥ የራሱን ሚዛን መጠበቅ ጀመረ።  ምክንያቱም የመብረር ችሎታው አስቀድሞ በፈጣሪው ውስጡ ተቀምጦ ነበርና።  ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ ከፍ ብሎ መብረር ጀመረ።  ከፍ ከፍ እያለ በደስታ መጮህ ጀመረ።  በአጭር ጊዜ ውስጥ፣ በጠቢቡ ሰው ከፍ ብሎ በረረ፣ እና ወደ ታች ሲመለከት፣ ጥልቅ ደስታ ተሰማው።  ጠቢቡ ሰውም እንዲህ አለ፣ “አንተ ጭልፊት፣ የራሴን ምንም አልሰጠሁህም እኔ የረዳሁህ ማንነትህን እንድትገነዘብ ነው። ታላቁ ችሎታህ አስቀድሞ በውስጥህ ነበር፤ አንተ ግን አላወቅህም ነበር”።  ይህ በትክክል የኛ የሰዎች ሁኔታ የሚገልጽ ነው።  👉በውስጥህ ያሉትን የተደበቁ ችሎታዎች እወቅ።  👉ችሎታህን ማግኘት ያን ያህል ትልቅ ነገር አይደለም። የሚያስፈልገው፡ ችሎታህን እንዴት እንደምትጠቀምክበት እና እንዴት ማንነትህን ቀረጸህ ማዳበር እንዳለብህ ነው።  👉ብረት ብረትን እንደሚሞረደው ሁሉ፣ ሰውም ሌላ ሰውን እንዲሁ ያሰለጥነዋል። በትክክል የሚረዳህን ሰው ፈልግ።

About