Language
English
عربي
Tiếng Việt
русский
français
español
日本語
한글
Deutsch
हिन्दी
简体中文
繁體中文
API
Home
How To Use
Language
English
عربي
Tiếng Việt
русский
français
español
日本語
한글
Deutsch
हिन्दी
简体中文
繁體中文
Home
Detail
@jnu_924: #4u
🙎🏻♀️
Open In TikTok:
Region: SA
Thursday 29 October 2026 19:18:44 GMT
40325
2307
0
267
Music
Download
No Watermark .mp4 (
0MB
)
No Watermark(HD) .mp4 (
0MB
)
Watermark .mp4 (
0MB
)
Music .mp3
Comments
There are no more comments for this video.
To see more videos from user @jnu_924, please go to the Tikwm homepage.
Other Videos
@Katerina Lioliou x @Sakis Rouvas 🤝 #sakisrouvas #lioliou
#ወተምዐ_ውእቱ_አርዌ_ላዕለ_ይእቲ_ብእሲት... #ወቆመ_ኆጻ_ባሕር ( ያም አውሬው በሴቲቱ ላይ ተቆጥቶ በባሕር አሸዋ ቆመ " ራዕ 13:17 ✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔✔ በዘመነ ጽጌ 4ኛ ሰንበት ላይ ከሚነበበው ምንባብ ክፍል የተወሰደ ርእስ ነው። ትምህርቱ የቅዱሳንን ስደት መንስኤ በተመለከት ሲሆን በተለይም ከወቅቱ አንጻር ካየነው ደግሞ የእመቤታችን ስደት በሊቃውንት አባቶቻችን በምን መልኩ እንደተነገረ፤ የደረሰባት መከራ ሲነገር እንኳን ለሚያዳምጠው ሰው ይቅርና ድንጋዮች ቢሰሙ እንደሚያስለቅስ { ዘበጽሑኪ ምንዳቤያተ ሶበ ይሰምእ በእዝን፣ ሰብእ አኮ እምበከየ ዕብን" እንዲል የምንመለከትበትም ትምህርት ነው። ሊቁ ርቱዓ ሃይማኖት የክርስቶስን ስደትና የሔሮድስን ሐሳብ አለመሳካት አስመልክቶ "የዲያብሎስ ማኅደር የሆነው ሔሮድስ በአላዋቂነት ነፋስን አስሮ ለማስቀረት ቀንን ለመመለስ ሞከረ" ይላል። ራዕ 12:7 ላይ በተገለጸው ቃል መሠረት በቅዱሳን መላእክት ድል አድራጊነት ውርደቱን የተከናነበው ዲያብሎስ ከሰማይ ወደምድር እንደተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት ይለናል። ወሶበ ርእየ ዝንቱ አርዌ ከመ ወድቀ ውስተ ምድር ዴገና ለእንታክቲ ብእሲት እንተ ወለደት ሕፃነ ተባዕተ {ወደዚህ ዓለም እንደ ወረደ ባየ ጊዜ አንድም ድል እንደ ተነሣ ወይም ድል እንደተደረገ ባየጊዜ ወንድ ልጅ የወለደች ያችን ሴት ተከተላት። ምሥጢሩ ግን በሐሣዌ መሢሕ (ሐሰተኛ ክርስቶስ) አድሮ ምእመናንን በትምህርት የወለዱ መምህራንን አሳደዳቸው። አንድም፦ ምግባር ሃይማኖትን ገንዘብ ያደረጉ ምእመናንን ተከትሎ አሳደዳቸው። በመከራ አሳቃያቸው። አንድም፦ በሄሮድስ አድሮ ኃያል ወልድን የወለደች እመቤታችንን ወደግብፅ በምትሰደድበት ጊዜ ተከተላት። ከኋላዋ በሠራዊተ ሔሮድስ እያደረ መከተሉን፣ በምዕመናን ልቡና አድሮ የሚዘከራት አጥታ በራብና ጥም እንድትሰቃይ፣ እንባዋ እንዲፈስስ፣ ብዙ ጸዋትወ መከራ እንድትቀበል፣ የልጇ ጫማ እንዲሠረቅና እንድታለቅስ፣ ደስተኛይቱ ሆይ ደስ ይበልሽ የተባለች እመቤታችን እንድታዝን፣ "አይቴኑ መልአክ ዘአብሠረኒ፣ ብካይየ ይርዓይ ወይርድአኒ" እስከምትል መሰቃየቷን፣ ሰይጣን በኮቲባና ትዕማን ልቡና አድሮ ልብ በሚሠብር ቃል መሰደቧን መናገር ነው። ሰዎች በሃይማኖታቸው ምክንያት ስደት ቢያገኛቸውም በመጨረሻ የሚያስደስተው ነገር እግዚአብሔር የስደተኞች መጠጊያ በመሆኑ ነውና "ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን፣ ኢየሱስ ግፉዕ ምስካዮሙ ለግፉአን" እንዲል ከዘንዶው የሞት ወጥመድ እየበረረች የምታመልጥበት ሁለት ክንፍ ለሴቲቱ እንደተሰጣት ሲያጠይቅ ቁ 14 ላይ "ወተውህባ ለይእቲ ብእሲት ክልኤ ክንፍ ከመ ዘዐቢይ ንስር (ለዚያች ሴት እንደ ታላቅ ንስር ያለ ሁለት ክንፍ ተሰጣት) እንዲል። በሃይማኖት ምክንያት የሚሰደዱ ሰዎች የሚያመልጡበትን ሁለት ክንፍ እግዚአብሔር ያዘጋጅላቸዋል። ሁለት ክንፍ የተባለው ምግባርና ሃይማኖት ናቸው። ይኸውም ለመምህራን ለምእመናን እንደ አብርሃም ያለ ምግባርና ሃይማኖት ተሰጣቸው ማለቱ ነው። እንደሚታወቀው አበ ብዙኃን አብርሃም በሃይማኖት የጸና በምግባሩ የቀና ( ሃይማኖትንና ምግባርን አስተባብሮ የያዘ) ነውና ቅድስት ሥላሴን በቤቱ ያስተናገደ ባለ ሁለት ክንፍ አባታችን ነው። ሃይማኖት ምግባር ከሌለበት ብቻውን ምዉት ነውና:: ያዕ 2 #አንድም:- ለመቤታችን ሁለት ክንፍ ተሰጣት ሲል የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያው ናትና እንደ ታላቅ ንስር ያለ ንጽሐ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ ተሰጣት፡፡ ንጽሐ ሥጋንና ንጽሐ ነፍስን ገንዘብ ያደረጉ ሰዎች ከዲያብሎስ የሚመጣባቸውን መከራና ፈተና ሳይሰቀቁ እንደሙሉ ደስታ እየቆጠሩ በነፍሳቸው ይከብራሉና ነው። ከመ ትሥርር ውስተ ገዳም ወውስተ መካን ከመ ትትዐቀብ በኵሉ መዋዕል ዘመነ ወአዝማነ ወመንፈቀ ዘመን (ወደ ገዳም ሸሽታ ትሄድ ዘንድ ) ይላል። መምህራነ ወንጌል እንዲሁም ምእመናን ከዓለም፣ ከመከራ፣ ከክህደት ሸሽተው መከራ ወደሚቀበሉበት በረሃ ይሄዱ ዘንድ #አንድም እመቤታችን ወደ ግብፅ ሂዳ ለ3 ዓመት ከ6 ወር ጊዜ ተጠብቃ ትኖር ዘንድ ነው። ዘመነ ሲል አንዱን ዘመን፣ ወአዝማነሲል ሁለቱን ዘመን ወመንፈቀ ዘመን ሲል የዓመቱን ግማሽ ወይም ስድስቱን ወራት ማለቱ ነው። እመቤታችን በስደት የቆየችው ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ነውና ነው። አንድም፦ ዘመነ ወዘመነ ዘመን ወመንፈቀ ዘመን ይላል። አንድም፡ ዘመነ ወዘመነ ወዘመነ ወመንፈቀ ዘመን። ቢል ትርጓሜው ግን ኣንድ ነው:: በሁት ክንፍ እየበረሩ ማምለጥ የሚያስፈልገው ከአውሬው ፊት ነውና "እምቅድመ፡ ገጹ ለውእቱ አርዌ እንዲል ከሐሳዌ መሢሕ ፊት መሆኑን ተገልጿል። "በልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል፥ የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል፥ ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፤ እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም በእጁ ይሰጣሉ" ዳን 7:25 እንዲል። በሁለት ክንፎቿ በርራ ስታመልጠው፤ መምህራንና ምዕመናንም በሃይማኖትና ምግባር ሲያመልጡት ተስፋ ቆርጦ እነሱን የሚያስቀርበትን የቻለውን ሁሉ በአማራጭ ሊጠቀም ይችላል። ዛሬም አውሬው ተስፋ ቆርጦ ሃይማኖታቸውን የጠበቁ ምዕመናንና መምህራን ላይ የቻለውን ሁሉ መከራ እያደረሰ መሆኑን ልብ ይሏል። እርሱም በቻለው ፍጥነት እየበረረ ተከተላት። "ወሠረረ ወዴገና ውእቱ አርዌ" እንዲል በሐሣዌ መሢሕ አድሮ መምህራንን ምእመናንን ይከተላቸዋልና ነው። በሄሮድስና በሠራዊቱ እያደረ አድሮ እመቤታችነን ተከተላት ማለቱ ነው። በዚህ ጊዜ ግን "ወእውፅእ እምነ አፉሁ ውእቱ ኣርዌ ማየ ብዙኀ እንተ ድኅሬሃ ለይእቲ ብእሲት ከመ ፈለግ ዐቢይ ከመ ይንሥኣ ውሒዙ" እንዲል ፈሳሹ ይዞ ያስቀራት ዘንድ እንደ ወንዝ ያለ ብዙ ውኃ ከአፉ አውጥቶ በዚያች ሴት ኋላ አፈሰሰ። ወረድአታ ምድር ይኽንንም፦ በሐሣዌ መሢሕ አድሮ በቃሉ ጦር አዝዞ ሰደደ። አንድም በሄሮድስ አድሮ ጦሩ ምእመናንን መምህራንን እመቤታችነን ያስቀራቸው ዘንድ ቢያዝዝም ምድር ግን ረዳቻት ማለት ርኅቀተ ሀገር (የሀገር ርቀት) ርኅቀተ ፍኖት (የመንገድ ርቀት) ሞተ ሰማዕታት (የሰማዕታት ሞት) ን አስቀረላቸው ማለቱ ነው። የምንጸልየው ጸሎት ሁሉ የሚያርገው በእመቤታችን ምልጃ አማካይነት እንደሆነ ራዕ 8:2 በተገለጸው መሠረት ቅዱሳን መላእክት ጸሎት የሚያሳርጉት በእርሷ በተመሰለው ማዕጠንተ ወርቅ እንደሆነ ቅዱስ ያሬድ "ናስተማስለኪ ኦ እግዝእትየ በማዕጠንት ዘወርቅ... ከማሁ በስዕለተ ስምኪ ያዕርጉ ጸሎተ ኩሉ ደቂቀ ፍጡራን" እንዲል ጸሎታችንን ሁሉ አምላከ አበው ይቀበልና ከስደት መልሶ ለክብር ያበቃን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን ። ሀገሬ ኢትዮጵያ!!! ልጆችሽ ይውለዱሽ!!! ይሟገቱልሽ እንጂ አይሞግቱሽ!!! ያሉ ልጆችሽ በበረከት ይመለሱልሽ!!! እሳት መሀልሽን ገነት አድርጐ የዓለም ማረፍያ ያድርግሽ አሜን !!! 21/02/2019ዓ.ም#viral
👁 #####################keşfetteyizzz #keşfet #tutdaala🥴🌹
#tiktoklive #kaze #live
Vão dizer que é IA 👀🤣🔥 #lulapresidente #ia #aiart #viral
Aimons nous vivant, cultivons l'amour. Faisons du bien autour de nous car la vie est imprévisible. La mort frappe sans prévenir. #fyp #Burkinafaso #aimonsnousvivant @Harouna F5 le Créateur 🇧🇫
About
Robot
API
Legal
Privacy Policy