@.cookie.ttj: #cat #fyp #real #macdemarco

trent
trent
Open In TikTok:
Region: US
Thursday 29 October 2026 23:47:58 GMT
32266
7965
34
726

Music

Download

Comments

s.l.a918
S.L.A :
My girlfirend says i am like a cat.
2026-11-10 23:56:57
0
loluxd8970
🐾†» * . ロロクスド . * «†🫀 :
I'm only alive because of my cat
2026-11-09 23:00:38
0
potato.jjs
potato :
extraño a mi goldito 😔
2026-11-08 07:18:13
15
agente412.nz
412 :
mi gato acaba de morir ....
2026-11-08 07:20:46
12
ivan_franc
𝓲𝓿𝓪𝓃 𝔁𝓾 :
y Dani
2026-11-09 02:19:29
2
m4xi271
Kiosco :
mi gato es igual
2026-11-01 14:47:27
13
nice.person429
Ok :
My cat ran away
2026-11-09 03:34:19
1
zombieboy09857
🦊Zombieboy0985🦊 :
real
2026-10-31 01:10:16
0
bale.fras
𝘽 𝘼 𝙇 𝙀 ୨ৎ :
I love cats 🤍
2026-11-05 13:10:22
4
enzo.rodrigues086
Enzo Rodrigues :
isso é tão tranquilo...
2026-10-30 12:26:42
3
07xk_naoseis
Mich? :
Organizando a fy
2026-11-01 09:10:40
2
sergio.ff835
. :
2026-11-07 20:58:29
3
brandonweedy
brandon-weed¥ :
ŕeal
2026-11-06 17:53:33
1
salatiel21x
saxi :
lindo
2026-11-06 03:55:05
3
yioweon
★nai* :
2026-11-07 06:06:38
1
4vemp
esther :
2026-10-30 00:37:39
3
davidkld1
david-kld1 :
Cute
2026-10-30 15:46:46
1
cx_2.2
☸︎ :
real
2026-10-30 01:56:58
3
yujira81
iphon :
а как называется музыка подскажите пожалуйста 🙏🏼🙏🏼🙏🏼
2026-11-06 00:16:22
0
daniel.79259
Daniel :
2026-11-10 02:11:35
0
linowss4
linowss :
Real
2026-11-04 17:29:34
0
amanate_da_lua_a
JINX 🍓 :
2026-11-09 23:44:08
0
linowss4
linowss :
https://vt.tiktok.com/ZSpNaJhnq/
2026-11-04 17:29:28
0
tristan13230
Tristán.. :
2026-10-31 21:57:18
0
carlosortiz7776
CEO :
2026-11-10 08:13:25
0
To see more videos from user @.cookie.ttj, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

ስለ ቢክራ ስናወራ  በወንድም አቡ ሱፍያን ቴሌግራም ቻናል ላይ የተቀቀ post ነው ስለ ቢክራ ስናወራ... -- ድንግልናን ጠብቆ ለሐላል የትዳር አጋር መድረስ ጥርጥር የሌለው የክብር ዘውድ ነው። በወጣትነት ማዕበል ውስጥ ራስን ለጌታ ብሎ ማቀብ፣ ፍላጎትን ለሐላል ማቆየት ትልቅ ጀግንነት፣ የማይደበዝዝ ጌጥም ነው። ይህ በማንም የማይናቅ፣ ዘመናት የማይቀይሩት የኢስላም ውብ መርህ ነው። ነገር ግን ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያው የምንመለከተው ጽንፍ የረገጠ ንትርክ፤ ድንበር የሳተ እና ልብ የሚሰብር ሆኗል። ስህተትን ከማረም ይልቅ ተስፋ የሚያስቆርጥ፣ በተውበት የተመለሱትን ወደ ባሰ የጥፋት አዘቅት የሚገፋ እና የትዳርን በር የሚዘጋ ዘመቻ መሆን የለበትም። ዲናችን ሚዛን ነው፤ ንጽሕናን እያወደሰ፣ ወደ ጌታቸው የሚመለሱትን ደግሞ አላህ በእዝነቱ እንደሚቀበላቸው ያስተምራል። የሰው ልጅ በተፈጥሮው ደካማ ነው። ይንሸራተታል፣ ይወድቃል። ዋናው ጥፋት ግን መውደቁ ሳይሆን፣ ከወደቁ በኋላ «እኔ አልረባም» በሚል ራስን ለባሰ ጨለማ አሳልፎ መስጠት ነው። ተውበት ማለት ያረጀውንና የቆሸሸውን የሕይዎት ገጽ ቀዶ፣ በአላህ ምሕረት በአዲስ ነጭ ወረቀት መጀመር ማለት ነው።  አንዲት እህት በስሜት ተሸንፋ ክብረ-ንጽሕናዋን ብታጣም፣ በእንባ ታጥባ  ወደ ጌታዋ ከተመለሰች እርሷ የተዋረደች ሳትሆን፣ በአላህ ዘንድ የተወደደች አዲስ ባሪያ ናት። «ከወንጀሉ የተመለሰ ልክ ወንጀል እንደሌለበት ነው» ተብሏልና። ውድ እህቴ! ትላንት የተሰበረው ማንነትሽ ዛሬሽን እንዲያጨልመው፣ ነገሽን እንዲነጥቅሽ አትፍቀጂ። አላህ ያዘነልሽንና የሸፈነልሽን ያለፈ ስህተት ለሰው ልጅ የመዘርዘር ግዴታ የለብሽም። አላህ ከሰወረው አንቺም ደብቂው፤ ተውበትሽ በአንቺና በፈጣሪሽ መካከል ብቻ የቀረ ሚስጥር ይሁን። በትዳር መድረክ ላይ ዋጋሽ የሚለካው በትላንት ስህተትሽ ሳይሆን፣ በዛሬው ዲንሽ፣ በሒጃብሽ ጥንካሬ እና በልብሽ ንጽሕና ነው። ተስፋ አትቁረጪ፤ አላህ የሰረዘውን ታሪክ ማንም መልሶ ሊያነበው አይችልም። ውድ ወንድሜ! ትዳር የሁለት ፍጹማን ሰዎች ውል ሳይሆን፣ አንዱ የሌላውን ጉድለት የሚሞላበት የመተሳሰብ ድንኳን ነው። የምትፈልገው የዱንያን ቅርፊት ብቻ ሳይሆን የአኼራ አጋርህን ከሆነ፣ የትላንት ማንነቷን መርማሪ አትሁን። ሰለፎችና ታላላቅ ሶሐቦች ያገቡት ድንግሎችን ብቻ አልነበረም፤በተውበት የበቀሉ አማኞችንም ጭምር ነበር። አንዲት ሴት ተፀፅታ፣ ወደ አላህ ተመልሳ ንጹሕ ሕይወት እየኖረች ባለችበት ወቅት ያለፈ ታሪኳን እየቆፈሩ ማሸማቀቅ የጨዋ ሙስሊም ምግባር አይደለም። የተሰበረን ልብ መጠገን፣ የታረዘችን ነፍስ በመልካም ትዳር መሸፈን አላህ ዘንድ ትልቅ አጅር አለው። በ አጭሩ ድንበር አንለፍ!! ንጽሕናን ከመጠበቅ አኳያ ድንበር አንሸርሽር፣ ወጣቶቻችን ክብራቸውን እንዲጠብቁ እንምከር። በሌላ በኩል ደግሞ በእዝነትና በተውበት በኩል ድንበር አናጥብ፤ የተሰበሩትን ተስፋ አናስቆርጥ። ቢክራዋን ተነጥቃ ወደ አላህ የተጠጋች ሴት፣ ክብሯን ይዛ ከጌታዋ ከራቀችው እጅግ ትበልጣለች። t.me/AbuSufiyan_Albenan t.me/AbuSufiyan_Albenan

About