@p_9766_:

R 🕸️
R 🕸️
Open In TikTok:
Region: US
Friday 30 October 2026 04:33:04 GMT
93
0
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @p_9766_, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

#በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ጥቅምት 21 እመቤታችን ድንግል ማርያም እስረኞችን የምትፈታበት ቀን                   #እግዝእትነ  #ማርያም እመቤታችን ድንግል ማርያም   የኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ናትና ሁሉን ማድረግ ትችላለች።  👉 ልጇን ከሃሊ (ሁሉን ቻይ ) ካልን   እመቤታችንን ደግሞ
#በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ጥቅምት 21 እመቤታችን ድንግል ማርያም እስረኞችን የምትፈታበት ቀን #እግዝእትነ #ማርያም እመቤታችን ድንግል ማርያም የኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ናትና ሁሉን ማድረግ ትችላለች። 👉 ልጇን ከሃሊ (ሁሉን ቻይ ) ካልን እመቤታችንን ደግሞ "ከሃሊት" ልንላት ይገባል! ልክ እንደ ልጇ ሁሉን ማድረግ እየቻለ በትእግስት ዝም እንደሚለው እመ ብርሃንም ስንት ነገር እየተደረገ አልፎ ተርፎ እርሷን አንዳንዶች ሲናገሩ ሰምታ እንዳልሰማች ዝም ትላቸዋለች። 👉እኛ ኋጥአን ንስሃ እስክንገባም ድረስ"ልጄ! የዛሬን ታገሳቸው? እያለች ትለምንልናለች"። ቸሩ ልጇም ሊምረን እንጂ ሊያጠፋን አይፈልግምና "እሺ እናቴ!" እያለ ይኸው እስከዛሬ ክፋታችንን ሳያይ የእናቱን ልመና እየሰማ አላጠፋንም ቸር ነው፣ ታጋሽ ነው፣ መሐሪ ነው፣ሕርሕሩ ነው ቂምም የለውም.....!! ዓጢያታችንን የተለማመደውና የረሳልን እየመሰለን ንስሃ መግባቱን ቸል ካልነው ግን እንደ ትእግስቱ ብዛት ፍርዱም በእጁ ነውና ይፈርድብናል!!! 👉ወገኖቼ ያ ትላንት በዓጢያት የተመላለስንበት ክፉ የሕይወት ጎዳናችንን በመተው ንስሃ በመግባት ከአባታችን ከነፍሳችን ቤዛ ጋር እንታረቅ አዲስ ውል እንፈራረም ንስሃ በመግባት!! ወደ እርሱ እንቅረብ። 👉ይህ ዕለት እመቤታችን እስረኞችን የምትፈታበት ቀን እንደ መሆኑ መጠን የሰው ልጆች በ3 ወገን እስረኞች ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ በስጋዊ አጥፍቶም ይሁን ሳያጠፋ ሊታሰር ይችላል "በመንፈሳዊው ግን ሰው በዓጢአት ማሰሪያ የሚታሰረው በጥፋቱ ብቻ ነው"። ሌላኛው ማሰሪያ ደግሞ ማዕሠረ ደዌ(በደዌ ዳኝነት) መታሰር ነው ~ መታመም የዓጢአተኝነት መገለጫ አይደለም ምክንያቱም ከቅዱሳን ወገን ከ80%በላይ ድውያን ነበሩና። ታዲያ በዚህ ዕለት #ወላዲተ #አምላክ 3ስቱንም ማሠሪያዎች እንደምትፈታ እናምናለን!! 👉በእስር ቤትም በዓጢአትም ሆነ በደዌ ማሠሪያ የታሠርን ሁላችን በዚህ ዕለት እንድንፈታ የጌታችንን እናት እንለምናት!!! 👉በሦስቱም ማሠሪያዎች የታሠሩ ወገኖቻችንን እያሠብን" የእስረኞች ጩኸት ወደ አንተ ይድረስ እያልን(መዝ78:18) እያልን ልንፀልይ ይገባናል!!!!! 👉ድንግል ማርያምንም እንደ ሊቃውንቱ"እማ እሰረ ጌጋይ ፍትሕኒ ወላዲተ ክርስቶስ አምላከ እምነ ሙቃሔ ፅኑዕ ወእ ማዕሠር ድሩክ ከመ ፈታሕኪዮ ዮም ለማትያስ ላዕክ"እንበላት!!! *እርሷም እንደ ልጇ ሁሉን ማድረግ ትችላለችና* ~ጥቅምት21 የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት~ 1.እግዝእትነ ማርያም 2.ቅ.አልዓዛር ሐዋርያ 3.አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም 4.ቅ.ኢዪኤል ነቢይ 5.ቅ.ማትያስ ረድእ 🙏ወላዲተ አምላክ የአንድዬ እናት ከታሠርንበት የዓጢያት ማሰሪያ በምልጃዋ ታስፈታን*!!!! አገራችን ኢትዮጲያን ህዝቦቿን ፍፁም ሰላም ትስጥልን! በልዩ ልዩ ችግር ውስጥ ያለነውን ልጆቿን ትመልከተን ከልጇ ከወዳጇ ታማልደን!!! አሜን አሜን አሜን ወስበሐት ለእግዚአብሔር ✥✥✥ 🙏 ✥✥✥🙏 ✥✥✥ 🙏 ✥✥✥ ድንግል ሆይ ከሚያስብ ሁሉን ከማይረሳ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢ። ✥✥✥ 🙏 ✥✥✥🙏 ✥✥✥ 🙏 ✥✥✥ ድንግል ሆይ በቤተልሔም ካንቺ የተወለደውን መወለድ በጨርቅ የተጠቀለለውንም አድግ እና ላህም በብርድ ወራት እስትንፋሳቸውን ያሟሟቁትንም አሳስቢ። ✥✥✥ 🙏 ✥✥✥ ✥✥✥ 🙏 ✥✥✥ ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከእርሱ ጋር ከሃገር ወደ ሃገር ስትሸሺ ካንቺ ጋራ መሰደዱን አሳስቢ። ✥✥✥ 🙏 ✥✥✥ ✥✥✥ 🙏 ✥✥✥ ድንግል ሆይ ከዓይኖችሽ የፈሰሰውን እና በተወደደው ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር ዕንባ አሳስቢ። ✥✥✥ 🙏 ✥✥✥ ✥✥✥ 🙏 ✥✥✥ ድንግል ሆይ ረሃብ እና ጥሙን፤ ችግሩን እና ኃዘኑን ከእርሱ ጋራ የደረሰብሽን ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ። ✥✥✥ 🙏 ✥✥✥ ✥✥✥ 🙏 ✥✥✥ ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ፤ ✥✥✥ 🙏 ✥✥✥ መዓትን ያይደለ ምሕረትን አሳስቢ፤ ✥✥✥ 🙏 ✥✥✥ ለጻድቃን ያይደለ ለኃጥኣን አሳስቢ፤ ✥✥✥ 🙏 ✥✥✥ ለንጹሐን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ፤ ✥✥✥ 🙏 ✥✥✥ እመቤቴ ሆይ እምዬ ኢትዮጵያን በዘርፋፋ ቀሚስሽ ከክፉዎች ከልያት አሜን ፫ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር

About