@abiyahmedali: ለሁለንተናዊ ብልጽግና - ሁለንተናዊ ዝግጁነት ያለው አመራር የኢትዮጵያን ሥልጣኔ ለመገንባት እንችል ዘንድ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ሁለንተናዊ ብልጽግና ማለት ቁሳዊና መንፈሳዊ ብልጽግና፣ ባህላዊና ሞራላዊ ብልጽግና የተሸመኑበት ብልጽግና ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ አመራሩ ሁለንተናዊ ዝግጁነት ያስፈልገዋል፡፡ በአካል የዳበረ፣ በሞራል የጠነከረ፣ በዕውቀት የተሳለ፣ በጥበብ የበሰለ እንዲሆን ይጠበቅበታል፡፡ በተለይም በሀገር ፍቅር ስሜትና በሕዝብ ተቆርቋሪነት መንፈስ ግዴታዎቹን እንዲወጣ የሀገር አደራዋ ጥብቅ ነው፡፡ ወታደራዊ ሳይንስ፣ ልምድ እና ሕይወት የሰውን ልጅ ዓላማና ሰብእና በመቅረጽ ረገድ ተወዳዳሪ የለውም፡፡ የሰው ልጅ በአካልም፣ በመንፈስም፣ በሥነ ምግባርም፣ በአፈጻጸምም ዲሲፕሊናዊ እንዲሆን በማስቻል ለዘመናት ትውልድን ሲያዘጋጅ ኖሯል፡፡ ውጫዊና ውስጣዊ ማንነቱ የሠመሩለት ሰብእና በመቅረጽም ታላላቅ መሪዎችን አፍርቷል፡፡ ግዳጅን በብቃት መፈጸም፣ በዐርበኝነት መንፈስ አገልግሎት መስጠት፤ የሥራ ዲሲፕሊንን መቅረጽ፤ የጋራ ግብን በጋራ ማሳካት፤ ወትሮ ዝግጁነት፤ በተዋረድ አመራርን ማፍራት፤ ኃላፊነትና ተጠያቂነት፤ ከላይ እስከ ታች በመናበብ ዓላማን መፈጸም፣ እና የመሳሰሉት ከወታደራዊ ሳይንስና ልምድ ሊወሰዱ የሚችሉ ዕሴቶች ናቸው፡፡ የመደመር መንግሥት አመራሮች በሁርሶ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ሥልጠና በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡ የመደመር ሥልጣኔ ታላቁ ስትራቴጂን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል፣ ከወታደራዊ ሳይንስና ሕይወት የምንቀስማቸው ዕውቀቶች፣ ክሂሎቶች እና ልምዶች አሉን፡፡ በተለይም ደግሞ በአንድ ሰዋሰው መግባባት፣ ሥነ ምኅዳርን በሚገባ መጠቀም፤ በተከታታይ ሕዝብን ለዓላማና ለተግባር ማነጽ፤ ለሕዝብ የገባነውን ቃል በሚገባ አከናውኖ መጨረስ፤ ከታች እስከ ላይ ያለውን መዋቅር ለሀገራዊ ዓላማ ማሣለጥ፤ ሀገርን በባለ አደራነት መምራት፤ ለምንምና ለማንም የማትበገር ጽኑ ሀገር መገንባት፤ ተተኪ ትውልድን ማፍራት እና የሀገርን ደኅንነት ምንጊዜም ማረጋገጥ የሚሉትን የስትራቴጂውን ሐሳቦች በተገቢው መንገድ ለመረዳትም ሆነ ለማስፈጸም ወታደራዊ ሥልጠናው የማይናቅ ሚና ይጫወታል፡፡ ወታደሮች ዒላማ፤ ሲቪሎች ደግሞ ዓላማ አላቸው፡፡ የሁለቱም ግብ ድልን ማስመዝገብ ነው፡፡ ሁለቱን ዲሲፕሊኖች በማገናዘብ ዒላማውንም የሚመታ፤ ዓላማውንም የሚያሳካ ትውልድ እንፈጥራለን፡፡

AbiyAhmedAli
AbiyAhmedAli
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 31 October 2026 05:47:49 GMT
146508
26276
888
1806

Music

Download

Comments

yordik06
Yordi :
በአካል የዳበረ፣ በሞራል የጠነከረ፣ በዕውቀት የተሳለ፣ በጥበብ የበሰለ አመራር
2026-10-31 05:58:33
410
solomonaklilu250
"𝖑𝖎𝖋𝖊 𝖌𝖔𝖊𝖘 𝖔𝖓" :
ይሄ ነገር እስከ ወረዳ ቢወርድ ባይ ነኝ
2026-10-31 07:32:18
148
goodfellas081
jason bourne :
game of thrones biseru bay negn
2026-10-31 09:53:02
0
mm_t_home
MM-T COLLECTION :
I won’t say much, but this man got the desire.
2026-10-31 09:53:04
0
ugaasmaya6399
SHAM ALI (Maya 12) :
Father of All Africans. I'm proud of you Wallaah
2026-10-31 09:53:49
0
myhomecars
M.y properties :
Sultan abiy Ahmed han
2026-10-31 08:01:56
45
usaabame
Usaa Bame :
Jawaar Mohammed yoo ta.ee malee namni sii caaluu biyya san keessaa hin jiru jabadhuu Abichuu Abba mala
2026-10-31 06:42:11
30
74faya
feysel :
ጀመአው ሌላ ታሪክ ውስጥ ነው👍
2026-10-31 06:20:17
106
abduraman.muzanbi
Abduraman muzanbil. :
Jabaadhuu Aba feetee caaltaa[Perfect score]
2026-10-31 09:57:00
0
metikoo29
Metiko🌸 :
My humble PM long live [Pray]
2026-10-31 08:14:53
0
kibrsewnw12
ቀብራራው⚔️ :
ወንድ ነህ እግዚአብሔርን💪
2026-10-31 05:53:00
202
musherefe.teka
ማክስ ጎማ :
ከወለዱ ፡ አይቀር ፡ የዚህ ፡ አይነት ፡ ጀግና።
2026-10-31 06:09:58
114
cruise8881
ክሩዝ (CRUISE)🇪🇹 :
ሰላም ከፈለግን ጦረኛ መሆን አለብን ። ሰላማችንን ከማንም የምንለምነዉ ሳይሆን በራሳችን የምናረጋግጠዉ መሆን አለበት። 🙏🙏🙏🙏
2026-10-31 06:20:00
55
asmarvrt
Asma W🩵☪️ :
king is on Work ♥️🥰
2026-10-31 05:50:48
79
usernames6434
🇻🇳 MON TPF 🇪🇹 :
we love him till death to our prime minister abiy ahmed 🥰🥰
2026-10-31 06:04:06
30
tekibeke4
tekibeke615 :
i praud with my PM&your team
2026-10-31 09:00:33
1
alex.kifle8
Alex kifle :
ታላቁ መሪይ 💪💪💪💪
2026-10-31 06:38:23
16
abduselam026
እውነተኛ ሠላም በኢስላም :
abiy ahmed ali😎😎😎
2026-10-31 09:17:08
5
bini.yenatulij
5G generetion :
አንተ ካልክ ሁሉም ልክነው
2026-10-31 05:57:45
23
zeray339
Zeray :
አብቹ ተሸከርካሪ ወንበር ላይ ቁጭ ብለው ስብሰባ ነው አያሉ እግራቸውን ጠረቤዛ ላይ ሰቅለው አንድ ስራ ሳይሰሩ የሚውሉትን በየስጋቤቱ vvip አዘግተው የሚውሉትን አደራ በደንብ አሰራልን ብቻህን ሆንክ ምን እናግዝ
2026-10-31 06:34:12
37
unsangroyalfamily
Wondsew S. :
የእኔ አባት ምርጥ ኢትዮጵያዊ in history!
2026-10-31 07:25:35
8
dave.ye.enate
Dave Ye Enate :
አረ የቃላት እጥረት ገጠመኝ ምን ልበል King 🤴
2026-10-31 06:24:19
14
abdurrahmaan435
Abdurrahmaan 🧠 :
ቀጣይ ደሞ ባለስልጣኑም ሰልጥኗል በሚል ህዝባዊ ስልጠና ተብሎ ህዝብ ለቀማ ይጀመራል
2026-10-31 08:31:41
5
hanaabiyahmed
Hana Abiy Ahmed🔵 :
ሰውዬው ጨርሶ ነው የሚያሳየው 💪
2026-10-31 06:13:41
9
tofikkdr
tofik :
ውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩስ ወይስ እሱ ቀጭን ስለሆነ ነው?
2026-10-31 06:31:20
11
To see more videos from user @abiyahmedali, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About