@abel_abuna7: የፍርድ ቤት ውሎ እንግዲህ አቤል አቡና የገቢ ጉተማን ሃሳዊነት ለማጋለጥ "አፖ ካድሬ" የሚል ቪዲዮ ሰርቶ እንደ ነበር የሚታወስ ነው። ይህንንም ተከትሎ ገቢ አቤልን አሳግቶ ሞጆ ድረስ ወስዶ ሰውሮት እንደከረመ ፣ ኋላም በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እና በህግ አካላት ርብርብ አቤል ከታገተበት ተለቅቆ እንደ ነበረም እንዲሁም በዚህ ምክንያት ገቢ ለሁለት ሳምንት ያህል እንደታሰረም የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። አቤልን በማገት ግቡን መምታት ያልቻለው ገቢም በስም ማጥፋት ክስ ከፍቶበታል። ታዲያ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከትናንት በስቲያ አቤል የፍርድ ቤት ቀጠሮ ነበረውና ቀርቦ ነበር። ችሎቱ ለህዝብ ክፍት ስለነበር እኔም ተገኝቼ የመታዘብ ዕድሉ ነበረኝ። ከሳሽ እንግዲህ አቶ ገቢ ጉተማ ነው። እዩ ጩፋም በራሱ ፋይል ከሳሽ ነበር። ነገር ግን የእዩ ጩፋ ሁለት ምስክሮች ተገኝተው ዋናው መስካሪ (እዩ ጩፋ) ባለመገኘቱ ምክንያት ፍርድ ቤቱ የእርሱን ምስክሮች አሰናብቶ ወደ ገቢ እና አቤል ጉዳይ ገባ። የገቢ ጉተማ ክስ በአጭሩ "አቤል በሬቻ የተባለው ሰው በ8/11/18 ዓ.ም መስቀል ሚዲያ በተባለ ዩቱብ ገፅ ላይ 'አፖ ካድሬ' በማለት ስሜን አጥፍቷሎ ፣ ስለ መንግስት በየሚዲያው እየተናገረ መሬት ተቀብሏል በማለት ስሜን አጥፍቷል" ወዘተ የሚል ነው። የዕለቱም የፍርድ ቤቱ ቀጠሮ ዓላማ ምስክር የመስማት ነበርና ከላይ ለተጠቀሰው የክስ ጭብጥ ገቢ ጉተማ ከባለቤቱ ጋር ምስክር ሆነው ቀርበዋል። በምስክርነቱ ወቅት በአቤል ላይ ለመመስከር የመጡት ገቢና ሚስቱ ከአንድ ቤት በአንድ መኪና መጥተው እርስ በራሱ የሚጋጭ ነገር ተናግረው ቢያስደንቁኝም (ዝርዝሩን ላለመናገር ነው)። ዳኛው ላቀረቡት መሠረታዊ ጥያቄ ሁለቱም የሰጡት መላሽ ግን አስደስቶኛል። ዳኛው ይጠይቃሉ:- "አቶ ገቢ ስሜ ጠፍቷል ብለዋል በዚህ ምክንያት ደረሰብኝ የሚሉት ጉዳት ምንድነው?" ገቢም በምላሹ:- "ግማሽ ያህል የቤተክርስቲያናችን አባላት ቀንሰውብናል" ብሏል። የገቢ ባለቤት ደግሞ በተራዋ ቀረባ ከዳኛው ለቀረበላት ተመሳሳይ ጥያቄ "አቤል በገቢ ላይ ሃሰተኛ ነው ብሎ ቪዲዮ ከሰራ በኋላ በቸርች ውስጥ ብዙ ወንበሮች ባዶ ሆነዋል ... እንዲሁም ሰዎች ገቢን እንደ ሃሰተኛ ነብይ እየተመለከቱት አክብሮታቸው ቀንሷል" ብላለች። ይህ የምር ሆኖ ከሆነ በጣም ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው። የሃሰተኞች አዳራሽ ባዶ እንዲሆን ለሚሰሩ ሰዎችም በጣም መልካም ዜና ነው። በአጭሩ ከትናንት በስቲያ በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ በዐቃቤ ህጎቹም ሆነ በጠበቃዋ እንዲሁም በአቤል በኩል ለምስክሮቹ (ለገቢ እና ባለቤቱ) በርካታ ጥያቄዎች ከቀረቡ በኋላ ፍርድ ቤቱ የእዩ ጩፋን ምስክርነት ለመስማት ሌላ ቀጠሮ ሰጥቶ ችሎቱ ተፈትቷል። በዚህ አጋጣሚ አቤልን እያገዘችው የምትገኘውን ጠበቃ ተወዳጅን ጉዳዩን በትጋት እና በብቃት ስለያዘችው ምስጋና ይገባታል። ቴዎድሮስ ተጫን
Abel Abuna
Region: ET
Saturday 31 October 2026 07:45:53 GMT
Music
Download
Comments
Dani Show media📖🎼✍️🇨🇦 :
😁 ያይሃል ለማን ነው?
2026-10-31 09:17:30
2
XODUS :
https://www.tiktok.com/t/ZTfc4veWL/
2026-10-31 12:29:36
0
bariche :
100% በሚባል ደረጃ የአቤል አቡና ትምህርት ወይም ጥቆማ ገብቶዋቸው የቸርቿ አባላት ከቀሩ እንደመረጃ ፍርድ ቤቱ ተመልክቶ አቤል አቡናን በነጻ መሸኘት እና ገቢ ጉተማን እንደ መጠሪያ ሥሙ ፖሊሥ ገቢ ማድረግ ነበረበት ያኔ"ሥምን መላዕክ ያወጣዋል" የሚለውን አባባል ግቡን ይመታል ።
2026-10-31 14:53:45
13
እውነት ያዉራ@Official✝️🇪🇹 :
ገና ይዋረዳሉ ባዶ ቤታቸው አቅፎ ይቀራሉ ።
2026-10-31 08:23:16
44
Firatol Getahun :
Gena yikenisal
2026-10-31 09:12:47
0
NATNAEL✝️ 🇪🇹 :
በኢየሱስ እመኑ ከዘላለም ሞት አምልጡ 🛐🤝
2026-10-31 09:02:06
12
toye abe :
ባክህ ገቢን አታንቀሳቅሰውም ሀያት 49 ያለውን ቸርቹን አይተከዋል? ዙሪያውን ከ40 ብርድ የተከራዩ ሱቆች አሉት ምን ይፈልጋል ሌላ?
2026-10-31 09:21:32
2
ዘመኑ አስጨናቂ ነውና እራሳቹህን መርምሩ :
አቤል ጨዋ ኢትዮጵያዊ 🥰🥰🥰
2026-11-01 02:44:06
2
ኤልፋዝ 𝙚𝙡𝙛𝙖𝙯 :
አቡላ ጌታ ይባርክህ
አይዞህ በአደባባይ የታገልክለት ጌታ በአደባባይ ይክስሀል ያነግስሀል ሞገስ ይሆንሀል
የእምነት ልዩነታችን እንደተጠበቀ ሆኖ....😊
እንወድድሀለን
2026-10-31 08:12:17
13
፩ አንዱ 1 :
ይመችህ አቤል አቡና ለእውነት ተሟጋች
2026-10-31 14:52:42
5
sam_cat23 :
አቤላ ፀጋንያብዛልዘመንህበቤቱ ይልቅ ተባረክ
2026-10-31 09:52:01
5
Girma Habte :
አቤል አቡና ተባረክ ፈጣሪ ከክፉ ሁሉ የሰይጣን ስራ ይጠብቅህ🥰🥰🥰🥰
2026-10-31 10:48:20
3
MulaRoba :
abel Berta gets kante gar new
2026-10-31 17:20:54
2
Mekdi bekele :
endate ayenetun yabezalen yemer🙏🙏
2026-10-31 07:55:56
4
Dire Dire :
Abel በሚሰራው በሐሰተኞችና አጭበርባሪዎች ነብዮች ማጋለጥ በሚሰራው ገብዬ ጥቅሜ አነሰብኝ በሚል ይስተካከል 😃
2026-10-31 17:15:51
1
Tibex sol :
አግቶ እንዲሰቃይ ስላደረገው ነገር ፍ/ቤት ምንም አላለም
2026-10-31 09:21:02
4
zegesha man :
አግዚአብሔር ይመስገን አቤል ስለ አንተ ደስ ብሎኛል 🙏🥰🙏
2026-10-31 15:37:58
1
suraj :
abel egzabher yebarkeh 🥰
2026-10-31 19:54:03
0
FIRAOL GRACE :
ስቶ እንኳን ከሆነ ከተፈጠረው ነገር መማር ትክክል እንዳልሆነ ይረዳል ብዬ አስባለሁ። ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ
2026-10-31 16:59:26
1
Tamirat H :
አቤላ ለምንድነዉ በሰዉ ቢዝነስ ምገባዉ? 🫣🫣👍
2026-10-31 15:49:37
1
Jiji :
ተፅዕኖ እየፈጠርክ ነው ክብሩን ጌታ ይዉሰድ 🙌🙌
2026-10-31 11:21:52
1
koኒ :
berta abela ewenet tesasalech enji atebetesem geta bertat yehunh🥰🥰🥰
2026-10-31 08:01:18
1
Abenezer Dejene :
ychlal Abel ychlal
2026-10-31 08:28:42
1
Amtataw Ashko :
you are doing well ...
2026-11-01 06:04:12
0
senat.123456789 :
አዎ እውነት ነው
2026-10-31 23:06:52
0
To see more videos from user @abel_abuna7, please go to the Tikwm
homepage.