@begood.com0: ከዘመን ተሻጋሪዉ የኤርምያስ አስፋዉ ሙዚቃ ጀርባ ያለዉ አሳዛኝ ታሪክ‼️ "ልረሳሽ አልቻልኩም" (✍️Jah MC እንደፃፈው) የድምፃዊ ኤርሚያስ አስፋው “ልረሳሽ አልቻልኩም” የተሰኘው ዘፈን ከብዙዎች ልብ ያልጠፋ ሙዚቃ ነው። ከዘፈኑ ጀርባ ያለው የፍቅር ታሪክ ግን እጅግ አሳዛኝ ነው። ኤርሚያስ ከልጅነቱ ጀምሮ እጅግ የሚወዳት እሷም ትወደው የነበረ የፍቅር ጓደኛ ነበረችዉ። ፍቅራቸው ከልጅነት እስከ ጉልምስና ዘልቆ ነበር። ሆኖም የሙዚቃ ሕልሙን ለማሳካት የነበረው ፍላጎት የጋብቻ ጉዳያቸውን አዘገየው። እሷ መቼ እንደሚጋቡ ስትጠይቀው፣ እሱ ግን “ትንሽ ጠብቂኝ፤ ዘፈን አውጥቼ እንጋባለን” የሚል ምላሽ ይሰጣት ነበር። ይህ መልስ ሲደጋገም ዉሳኔዋን ወደ ሌላ ጋብቻ እንድትወሰን አደረጋት። ይህ ክስተት በኤርሚያስ ላይ ከባድ የልብ ስብራት ፈጠረ። የሚወዳትን ሴት ማጣቱን መቀበል አቃተው፤ ትዝታዋን ለመርሳትም ቢሞክር አልቻለም። ሌሎች ሰዎች ወደ ሱስ እንዳይገቡ ይመክር የነበረው ኤርሚያስ ራሱ ግን ቀስ በቀስ ወደ ሱስ አዘነበለ። ከዚያ በኋላ የሙዚቃ ሥራውን ለማሳካት ከፕሮዲውሰሮች ጋር በቅርበት ለመስራት ከናዝሬት ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በክለቦች መሥራት ጀመረ። በቀጣይም 12 ዘፈኖችን ያካተተ “አንግሶኛል” የተሰኘ አልበም ሠራ። ከአልበሙ ውስጥ ለቀድሞ ፍቅረኛዉ የሠራው “ልረሳሽ አልቻልኩም” የተሰኘው ዘፈን ይገኝበታል። ዘፈኑን ከአልበሙ በፊት በነጠላ ሙዚቃ መልክ አውጥቶ ነበር። በወቅቱም በከፊል ተደምጦ ለአልበሙ መጠሪያ የሚሆን ስም እንዳገኘ አስቦ ነበር። ነገር ግን አልበሙን ለሕዝብ ሲያቀርብ ያልጠበቀው ችግር ገጠመው። ካሴቱ እንዳሰበው አልተደመጠም። ይህም ስሜቱን እንደጎዳዉ እና ሱሱንም እንዳባባሰበት ይነገራል። ካሴቶቹንም ሰብስቦ ሽንት ቤት ውስጥ እንደጣላቸዉ ተገልጿል። ቀናት እየተተኩ በሔዱ ቁጥር በጤና እክል ምክንያት የደም ቧንቧ መጥበብ የጤና ችግር ገጥሞት ሕይወቱ አለፈ። ኤርሚያስ ከራሱ ሕይወት ጋር የተያያዘ “ልረሳሽ አልቻልኩም” የተሰኘው ነጠላ ስራ ዛሬም ድረስ በብዙዎች ዘንድ በተለየ ስሜት የሚደመጥ ዘፈን ሆኖ ቀጥሏል። “ምን ተክቼ ልርሳ መውደዴን በምኔ፣ ሰው በሰው መተኪያ አላገኘም ጎኔ።” 👉አንዳንድ ዘፈኖች በጆሮ ብቻ አይሰሙም፤ በልብ ይሰማሉ። የኤርሚያስ አስፋው “ልረሳሽ አልቻልኩም” ከእነዚህ ዘፈኖች አንዱ ነው የሚሉ አስተያየቶችም በተደጋጋሚ ተሰጥተዋል። *የሙዚቃዉ ርዕስ- ልረሳሽ አልቻልኩም ግጥም፦ ዳዊት ጌታቸው ዜማ፦ ኤርሚያስ አስፋው እና ሳሙኤል አስፋው ቅንብር፦ ጂግሳ ታደሰ 👉 በዚህ ሙዚቃ ያላችሁን ገጠመኝ (ትዝታ) አጋሩን።

Liyu መረጃ
Liyu መረጃ
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 31 October 2026 09:01:57 GMT
25142
537
18
113

Music

Download

Comments

appleuser59756379
appleuser59756379 :
Peace and rest
2026-10-31 17:16:22
1
zolla316
Zelalembefekadu :
ቡታጅራ የነዳንኤል ካናል መኖሪያ ቤታቸው ሁሌ ትዝ ይለኛል
2026-10-31 19:05:36
0
haniyemaryamlij2
ሀና :
ነፍሱ በሰላም ትረፍ
2026-10-31 18:26:37
1
user83603553361443
user83603553361443 :
ኤርሚ የናዝሬቱ እንወደዋለን ነፍሱን በገነት ያኑረው
2026-10-31 22:05:07
0
biniyam.feyissa
Biniyam Feyissa :
በአንድ ሰው የተነሳ በጣም ነው የምወደው
2026-10-31 20:16:59
0
lulitasresabay2
Lulit :
እናውቃለን ግን ...?😭
2026-10-31 20:54:01
0
11dagnachew
God is Good all the Time :
ለኔም የተለየ ትዝታ ነበር ጥሩ ጌዜ ጥሩ ዘመን
2026-10-31 19:21:52
0
foggf1228
rut :
2026-10-31 20:56:51
0
best19993t.g
best :
ነብስ ይማር
2026-10-31 21:12:57
0
tizazu.ahmed519
ፎቶየ አሳሰረኝ ahmed :
በጣም ነው የምወደው
2026-10-31 18:57:11
0
seiflk0
S.L :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-10-31 20:32:46
0
4757z
4757z :
አንድክፍል ተምረናል ወንድሜ ነብስ ይማር 🙏
2026-10-31 17:47:45
0
etalnamroud
Mame Melese :
ነፍስ ይማር 🙏🙏🙏
2026-10-31 16:50:10
1
senayit.seni35
Senayit Seni :
😭😭😭😭
2026-10-31 17:54:28
0
hzbeud5
tsfey kbede :
🥰🥰🥰
2026-10-31 17:07:10
0
derejemeshesha1
derejemeshesha3 :
😭😭😭
2026-10-31 10:02:18
0
0944445764ts
0944445764ts@ :
😂😂😂
2026-10-31 21:17:36
0
To see more videos from user @begood.com0, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About