@afbn255: #ሰበር ዜና! የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና ምክር ቤት ስድስተኛ መደበኛ ስብሰባውን አጠናቀቀ፤ አገዛዙ የሕዝቦች የህልውና ጠንቅ መሆኑን ገልጾ የመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ አጸደቀ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና (ትብብር ለሕልውና) ምክር ቤት ስድስተኛ መደበኛ ስብሰባውን ከጥቅምት 20 እስከ 21 ቀን 2019 ዓ.ም ማካሄዱን አስታወቀ። ትብብሩ መመስረቱ በይፋ ከታወጀ በኋላ ባካሄደው በዚህ የመጀመሪያ ስብሰባው፤ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ፣ ቀጣናዊ እና ሀገራዊ የኃይል አሰላለፍ ሁኔታዎችን በጥልቀት በመገምገም የትብብሩን የመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ አጽድቋል። በምክር ቤቱ ግምገማ መሠረት፣ ኢትዮጵያ በአምባገነናዊና ዘረ-ፈጅ አገዛዝ ሥር በመውደቋ የዜጎች መፈናቀልና የከፋ ድህነት መገለጫ ሆናለች። አገዛዙ በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎች አካባቢዎች ባወጀው ጦርነት ምክንያት ዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ተገፈፈው ሕልውናቸው አደጋ ውስጥ መውደቁ ተገልጿል። በተጨማሪም በሞያሌ፣ በአርሲ፣ በወለጋ፣ በጋምቤላ፣ በሶማሌ፣ በአፋር እና በሲዳማ የህዝብን እርስ በርስ ግጭቶች በመቀስቀስ ከፍተኛ ውድመት መፈጸሙ በመግለጫው ተመልክቷል። ምክር ቤቱ ከገመገማቸው መሠረታዊ መርሆዎች መካከል፦ የብልጽግና አገዛዝ የሁሉም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ጠላት መሆኑ፣ የትብብሩ መሠረታዊ ዓላማ አገዛዙን ከሥልጣን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን የሕዝቦችን ሕልውና የሚያረጋግጥ ስትራቴጂካዊ ትብብር መሆን መቻሉ፣ የአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ትብብር ለቀጣናው ልማት ወሳኝ መሆኑ ተረጋግጧል። ከዚህም በተጨማሪ ትብብሩ ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ሕልውና የሚደረገውን ትግል ማጠናከር፣ ህዝባዊና ዲፕሎማሲያዊ ትግሎችን ማቀናጀት፣ እንዲሁም ከአፍሪካ ቀንድ ሕዝቦች ጋር ወዳጅነትን ማጠናከርን ጨምሮ 6 አበይት የመካከለኛ ጊዜ የተግባራት ዕቅዶችን አጽድቋል። በመጨረሻም ምክር ቤቱ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከህዝባዊ ኃይሎች ጋር በመሆን ትግሉን እንዲያጠናክሩ፣ ለአባል ድርጅቶች ሰራዊት በጋራ በመተሳሰር የጠላትን አከርካሪ እንዲሰብሩ፣ እንዲሁም ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ አገዛዙ በቀጣናው ላይ እያደረሰ ያለውን አፍራሽ ሚና ተገንዝቦ ከህዝቡ ጎን እንዲቆም ጥሪ አስተላልፏል።
አፋብን/AFBN/ሚዲያ
Region: ET
Saturday 31 October 2026 15:38:23 GMT
Music
Download
Comments
Ayele man city :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-11-01 08:56:13
0
ሚካኤል አባቴ 12✝️ :
2026-11-01 05:46:39
0
AmAN የቲሊሊው🇬🇭🇬🇭🇪🇹 :
👍👍
2026-10-31 18:33:53
0
የነአጀሬአገረጎጃምነው :
💪💪💪
2026-10-31 17:25:45
0
@gebre❤ :
💪💪💪
2026-10-31 16:37:39
0
ሠላም ለሁሉም :
[Power][Power][Power][Power][Power][Power][Power][Power][Power][Power][Power][Power][Power]
2026-10-31 17:37:43
0
To see more videos from user @afbn255, please go to the Tikwm
homepage.