@aahdabofficial: የሰው ተኮር ልማት በተግባር የተረጋገጠበት የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ ነዋሪዎች መንደር! ዛሬ የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ ነዋሪዎች መንደርን ለአካባቢው የልማት ተነሺዎች አስረክበናል። የከተማ ልማት ዋነኛ ዓላማ መሠረተ ልማትን መገንባት ብቻ ሳይሆን የዜጎችን ኑሮ ማሻሻል፣ መብትና ጥቅም ማስጠበቅ እና የተሻለ የኑሮ ዕድል መፍጠር ነው። በአዲስ አበባ እየተገነባ የሚገኘው የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ የሀገራችንን የቴክኖሎጂና የኢኮኖሚ እድገት የሚያፋጥን ትልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው። ሆኖም ፕሮጀክቱ ቀደም ሲል መሬቱን ለእርሻ፣ ለግጦሽና ለመኖሪያነት ሲጠቀሙ የነበሩ አርሶ አደሮችን ሕይወት የሚነካ በመሆኑ፣ የልማቱ ተጠቃሚ እንጂ ተጎጂ እንዳይሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥተናል። በዚህም መሠረት ለሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ የልማት ከእርሻና መኖሪያ ቦታቸዉ ተነሺ ለሆኑ የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ አርሶ አደሮች የተቀናጀ መኖሪያ መንደር ገንብተን፣ የኑሮና የገቢ ምንጮቻቸውን የሚያሳድጉ አቅርቦቶችንም አካተናል። ይህም የነዋሪዎቹን ማኅበራዊ ትስስር ጠብቆ ወደ ተሻለ የአኗኗር ሁኔታ የሚያሸጋግር ሰው ተኮር የልማት አሠራር ነው። ከመኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ መንደሩ የሚከተሉትን አቅርቦቶች ይዟል፦ * የወተት ላሞችን የሚይዙ የከብት ሼዶችና የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ። * የንግድ ሱቆች፣ የምርት ማከፋፈያና መሸጫ መጋዘን እንዲሁም ወፍጮዎች። * የስፖርት ማዘውተሪያ፣ የሕፃናት መጫወቻና ማቆያ ማዕከል። * የስብሰባ አዳራሽ። እነዚህ አቅርቦቶች ነዋሪዎቹ የተሻለ መኖሪያ እንዲኖራቸው፣ የወተት ልማትና ሌሎች የገቢ ምንጮቻቸውን እንዲያሳድጉ፣ ማኅበራዊ ትስስራቸውን እንዲጠብቁ እና ልጆቻቸው ምቹ አካባቢ እንዲያገኙ የተዘጋጁ ናቸው። ልማት ማለት ሰውን ከነበረበት ቦታ ማንሳት ብቻ ሳይሆን የኑሮ ደረጃውን ማሻሻል፣ የኢኮኖሚ አቅሙን ማጠናከርና የነገ ተስፋውን ማለምለም ጭምር ነው። የአካባቢው ነዋሪዎች ቦታው ለታላቅ ሀገራዊ ፋይዳ እንደሚውል ስናስረዳቸው፣ ዩንቨርቲዉ ለልጆቻቸው የመማር ዕድልና ሀገርን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የመሆን አቅም እንደሚፈጥር በመገንዘብ በፈቃደኝነት ትብብራቸውን አድርገዋል። ለዚህ ከልብ እናመሰግናለን፤ ትልቅ ክብርም ይገባቸዋል። ይህ ተግባር በመደመርና በትብብር ስንሰራ ሁሉንም ወገኖች ተጠቃሚ ማድረግና ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ እንደምንችል ማሳያ ነው። የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ ነዋሪዎች መንደር ይህንኑ ሰው ተኮር የልማት አቅጣጫችንን በተግባር የሚያሳይ ምሳሌ ነው። የምንገነባት አዲስ አበባ የሁሉም ነዋሪዎቿን ክብር፣ መብትና ጥቅም የምታስጠብቅ፣ ሁሉንም በእኩል የልማት ተጠቃሚ የምታደርግ ከተማ እንድትሆን ቁርጠኛ ነን። የቦሌ ክፍለከተማ አመራሮችና በስራዉ ሂደት አስተዋፅኦ ላደረጋችሁ ሁለ ከለብ አመሰግናለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ
A.A Housing
Region: ET
Sunday 01 November 2026 14:02:56 GMT
Music
Download
Comments
ወይንሸትመኮንንይማም :
እበካችሁግበኙንቤት
2026-11-01 16:21:21
0
user16288502066542 :
ያሳዝናል 14 አመት ቤት ቆጣቢዎች እያለን በብልፅግና ስካር ተበደልን ተገፋን ተቃጠልን የ2005 እና 1997 የቤት ቆጣቢዎች ጉዳይ ችላ አትበሉ እባካቹሁ እውነት ለመናገር አገሬን እጅግ በጣም የምወድ ሰው ነበርኩ
2026-11-02 12:16:13
1
ሄኖክ :
ቃል እና ተግባር ተለያዩ ፍትህ ሀገር እና መንግስት አምነን ገንዘባችን ቆጥበን ለከሰርነዉ 😥
2026-11-05 20:09:11
1
EthioJobs Vacancy የስራ ማስታወቂያ :
የመምህራን በአመቱ ቁፋሮ ያልተጀመረ አለ እባካችሁ 🙏
2026-11-02 22:11:10
0
putin :
ፍትህ ሀገር እና መንግስት አምነን ገንዘባችን ቆጥበን ለከሰርነዉ 😥
2026-11-02 16:27:04
0
ከ/ማ :
2005 አስቡን
2026-11-03 06:24:48
0
user7344739781171 :
የሚገርማቹ የ2005 ተመዝጋቢ ነኝ ብዞች የቤት ባለቤት ሆኑ ሲባል እሰማለሁ እኛ የ2005 ተመዝጋቢዎች በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ መመዝገባችን ይሆን ሀጥያታችን
2026-11-02 07:45:18
0
Tedo Rufali :
ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት
ጉዳዩ፡- የ2005 ዓ.ም. የኮንዶሚኒየም ቤት ምዝገባ ተጠቃሚ ያልሆኑ የአዲስ አበባ ተወላጅ የቤተሰብ አባላት እና ቋሚ ነዋሪዎች ቅሬታን ይመለከታል
ክቡር/ክቡር የከተማችን ከንቲባ፣
እኛ በዛሬው ዕለት ይህንን ጥያቄ እና መልዕክት የምናቀርብልዎ፤ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በከተማችን በኪራይ ውድነት እና መኖሪያ ቤት እጦት እየተማረርን የምንገኝ፣ በ2005 ዓ.ም. የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ ምዝገባ ስርዓት ላይ በህጋዊ መንገድ ተመዝግበን እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት መፍትሄ ያላገኘን የአዲስ አበባ ከተማ ተወላጆች እና ቋሚ ነዋሪዎች ነን።
በወቅቱ—እኤአ በ2005 ዓ.ም.—ከፍተኛ ትምህርታችንን አጠናቀን ወደ ስራው ዓለም ስንቀላቀል፣ ገና ወጣቶች እና ኑሯችንን ለመመስረት በሂደት ላይ የነበርን ነበርን። ዛሬ ላይ ደግሞ የቤተሰብ ሃላፊነት ተሸክመን፣ የልጆች አባት ሁነን፣ ለዓመታት ያለማቋረጥ ቁጠባችንን ሳንቋረጥ ስንከውን ብንኖርም፤ ከቤት ኪራይ ጭማሪ እና ካልተረጋጋ የኑሮ ሁኔታ ጋር እየታገልን እንገኛለን።
የአዲስ አበባ ልጆች መሠረታዊ ጥያቄዎች እና የሚነሱ እውነታዎች
የትውልድ እና የማህበራዊ ትስስር እውነታ፡- እኛም ሆንን አባቶቻችን እና አያቶቻችን የዚህች ከተማ የዕድገት እና የውረድ ባለታሪኮች የሆንን የአዲስ አበባ ተወላጆች ነን። ይሁን እንጂ፣ የቀድሞ አባቶቻችን የመኖሪያ ቤት ባለቤት የመሆን እድል ሳያገኙ በማለፋቸው ምክንያት፣ ዛሬ ላይ እኛም የራሳችን መኖሪያ ቤት አጥተን በከተማችን ውስጥ ስደተኛ መስለን በውድ ኪራይ እንድንኖር ተገደናል። አዲስ አበባ የሁላችንም ማዕከል ስትሆን፣ የዚህች ከተማ ልጆች ግን በራሳቸው ከተማ ውስጥ የቤት ባለቤት ለመሆን ሲቸገሩ ማየት ከባድ የስነ-ልቦና እና የኑሮ ጫና ፈጥሮብናል።
የጊዜ እና የሂደት መጓተት፡- ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ ባለፉት ዓመታት ውስጥ በርካታ ዜጎች ከተለያዩ አካባቢዎች መጥተው የቤቶች ባለቤት ሲሆኑ ስንመለከት፣ እኛ ዕድሉን በጊዜው ጠብቀን በቁጠባ እና በህጋዊ መንገድ የተመዘገብን የአዲስ አበባ ልጆች ግን እስካሁን አለመታደላችን ፍትሃዊነትን የሚያሳጣ እና ጥያቄ የሚያስነሳ ነው።
የፍትህ እና የቅድሚያ መብት ጥያቄ፡- በሌሎች ክልሎች የሚገኙ ዜጎች በራሳቸው አካባቢዎች ቅድሚያ ተጠቃሚ ሲሆኑ፣ የአዲስ አበባ ተወላጆች ግን በከተማችን ውስጥ ከሌሎች ቀድመን ተመዝግበን ሳለን ላልተወሰነ ጊዜ መዘግየታችን አግባብ አይደለም። በከተማ አስተዳደራችሁ እየተወሰዱ ያሉ አበይት የልማት እና የዕድሳት ስራዎች የተወላጆችን እና የቆዩ ተመዝጋቢዎችን መብት በማስጠበቅ ረገድ እንዲስተካከሉ ከፍተኛ ፍላጎት አለን።
ለአስተዳደሩ የሚቀርብ የመፍትሄ ሃሳብ ጥሪ
ክቡር ከንቲባ ሆይ፣
እርስዎ የከተማችንን ኑሮ ለማሻሻል እና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት እያደረጉት ላለው ጥረት ያለን አድናቆት ከፍተኛ ነው። ይሁን እንጂ፣ ከዚህ ቀደም ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ ሲቆጥቡ የቆዩ፣ ቤተሰብ መስርተው በኪራይ ውድነት እየተማረሩ ያሉ እና የከተማው ተወላጅ የሆኑ ወገኖችን ልዩ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚከተሉት እርምጃዎች እንዲወሰዱልን አበክረን እንጠይቃለን፡
ልዩ ትኩረት እና ፍትሃዊ ድልድል፡- ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ ሲቆጥቡ የቆዩ እና እስካሁን ዕድል ያላገኙ የከተማው ተወላጆች እና ቋሚ ነዋሪዎች በልዩ ማዕቀፍ ውስጥ ታይተው መፍትሄ እንዲያገኙልን።
የኪራይ ጫና ማስታገሻ ጊዜያዊ እግዶች እና ዘላቂ ምላሽ፡- ቤቶች እስኪደርሱን ድረስ አሁን ባለው የከፋ የኑሮ ውድነት እና የቤት ኪራይ ግፊት ውስጥ የወደቁትን ቤተሰቦች የሚታደግ የፍጥነት ቤት የማስተላለፍ ስራ እንዲከናወን።
የከተማችን አስተዳደር የህዝብን እንባ በመረዳት ለዚህ የረጅም ጊዜ ጥያቄያችን አዎንታዊ ምላሽ ይሰጠናል ብለን በጥልቅ እናነባለን።
አክባሪዎ / አቤቱታ አቅራቢው፡
የ2005 ዓ.ም. የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች እና የአዲስ አበባ ተወላጆች ስም
2026-11-01 21:54:44
0
birhanu agafari :
@🥰🥰🥰🥰
2026-11-02 13:05:03
0
To see more videos from user @aahdabofficial, please go to the Tikwm
homepage.