@mekdiwalt: መሶበ ወርቅ ንጹሕ ንጹሕ የወርቅ መሶብ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በውዳሴ ማርያም ዘሰንበተ ክርስቲያን(የእሁድ) ላይ በግእዙ፦ "አንቲ ውእቱ መሶበ ወርቅ ንጹሕ እንተ ውስቴታ መና ኅቡዕ ኅብስት ዘወረደ እም ሰማያት ወሃቤ ሕይወት ለኩሉ ዓለም" ወደ አማርኛ ሲመለስም፦ "የተሰወረ መና ያለብሽ ንጹሕ የወርቅ መሶብ አንቺ ነሽ።መናም ከሰማይ የወረደውና ለዓለም ሁሉ ሕይወትን የሚያድለው ኅብስት ነው። ቁ.4 በማለት እመቤታችንን አወድሷታል። ትርጓሜው(ምሥጢሩም)፦ መሶበ ወርቅ የእመቤታችን ምሣሌ ሲሆን፤ ወርቁም የንጽሕናዋ የቅድስናዋ ምሣሌ ነው።ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን ማለትም፦ ከንጹሐን ይልቅ የነጻች፤ ከተለዩትም የተለየች እንደሆነች ይታወቃል፣ ይታመናልም። ከሰማይ የወረደ ኅብስት(መና) የተባለውም ምግበ ነፍስ ማለትም፦ ዘለዓለማዊ የነፍስ ምግብ የሆነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህንንም ራሱ ጌታ በማይሻረው ቃሉ፣ በቅዱስ ወንጌሉ እንዲህ ሲል አስተምሮናል። "የእግዚአብሔር እንጀራ ከሰማይ የሚወርድ ለዓለምም ሕይወትን የሚሰጥ ነውና" ዮሐ.6፥33 አያይዞም በቁጥር 35 ላይ "የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ።ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም።በእኔ የሚያምንም ሁል ጊዜ ከቶ አይጠማም። ዮሐ. 6፥ 35 ሲል ተናግሯል። ዝቅ ብሎ በዚሁ የወንጌል ክፍል ላይ "የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ። አባቶቻችሁ በምድረ በዳ መና በሉ ሞቱም ።ሰው ከእርሱ በልቶ እንዳይሞት ከሰማይ አሁን የወረደ እንጀራ ይህ ነው። ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ።ሰው ከዚህ እነጀራ ቢበላ ለዘለዓለም ይኖራል። ዮሐ.6፥ 48-51። አምላካችን ለእኛ ለልጆቹ በሁለት መልክ ነው የነፍስ ምግብ የሆነን፦ ፩ኛው "ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ኹሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም" ማቴ.4፥4 በማለት ሕይወት የሆነውን ቅዱስ ቃሉን በመስጠት ሲሆን ፪ኛም፦ "እኔ ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው። እውነት እውነት እላችኋለው የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችኹ ደሙንም ካልጠጣችኹ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው።እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለው። ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል።እኔም በእርሱ እኖራለሁ"። 51-56 በማለት በልተነው ዳግም የማያስርበንን ጠጥተነውሞ ዳግም የማያስጠማንን የዘለዓለም ምግብ የሆነውን ቅዱስ ሥጋውን እንዲሁም የሕይወት መጠጥ የሆነውን ክቡር ደሙንም በመስጠት ነው። ይህንን ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚገኝበትን ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን ጌታ ይዞት የመጣው ከሰማይ ሳይሆን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ፣ ከደምዋ ደምን በመንሳት(በመውሰድ) ስለሆነ እርስዋ የኅብስት ማኖርያ በሆነው በንጹሕ መሶበ ወርቅ ተመስላለች። @eyasu waltengues @Tibebe yiheyis @Eden Israel @Mekdes dejene Zena @Ermi_art #መሶበወርቅ
Ephani
Region: ET
Sunday 01 November 2026 14:18:37 GMT
Music
Download
Comments
ዝብርቅርቅ ሕይወት :
ሰላምሽ ይብዛ መሰቦወርቄ
2026-11-01 14:30:56
49
Fiseha Hailu :
ቀጥሉበት ጥሩ ነው
2026-11-01 17:14:21
15
ዲ/ን ፈቀደ @1221 :
ኧረ ተው
2026-11-02 07:04:18
3
wondemnew :
በፅናፅል
2026-11-02 03:53:42
4
Elu :
እናመሰግናለን መሶበወርቅ የስምሽ ስያሜ በጣም አስደንቆኝል የአባቶቻችን አምላክ የተመሰገነ ይሁን
2026-11-01 18:45:06
6
IMMANUEL :
እግዚአብሔር ይመስገን
2026-11-01 15:26:08
6
, Nigat🔏 :
2026-11-02 02:29:35
0
mame :
🙏🙏🙏👑👑👑👑👑❤️❤️❤️🤲🤲🤲🤲🎁🎁🌹🌹🌹🌹🌹አሜንንን
2026-11-01 18:28:45
1
አንቲ ውዕቱ ተስፍሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እገነት :
ቀጥሉበት በጣም ደስ ብሎናል ተዋህዶወች❤
2026-11-02 11:28:29
0
@BOSS🙏 :
ቃለ ህይወት ያሰማልን
2026-11-01 17:09:59
4
🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬 :
አረ ተው
2026-11-02 04:36:27
1
Ethiopia Teferi መኮንን🏳️ 🕊️🤲 :
🥰🥰🥰
2026-11-01 14:27:14
2
𝖉𝖆𝖌𝖒𝖆𝖜𝖎 :
የደንብ ቀጥሉበት አያቋርጡ፣ እንደ አገልግሎት አድርገው አስቡት፣ ደሞም ነው፣ በጣም መልካም ሥራ ነው። ንዋየ ቅድስትን ብቻ ሳይሆን፣ ሌሎችንም ከመፅሐፍ ቅዱስ፣ ከሌሎች መፃሕፍትም ወስዳቹ ስሩ።
2026-11-02 09:34:14
0
dawit Asirat :
🥰🥰🥰🥰
2026-11-01 17:19:45
2
kena Ethiopia :
❤️❤️❤️❤️❤️🙏🙏🙏🙏
2026-11-02 08:31:38
0
Geni :
አናመሰግናለን 🙏🙏🙏
2026-11-02 09:39:04
0
የኪትሞራዎማረያም :
እግዛብሔርይመስገን
2026-11-01 20:23:32
0
የሰማእቱ የቅድስ ጊዬርጊስ ባሪያ ነኝ :
🥰🥰🥰
2026-11-01 15:55:40
1
makriana16(maki) :
በርታ
2026-11-02 13:07:48
0
ብርቱካን :
እውነትነው
2026-11-01 16:15:32
1
roba 47 :
በቤተ ክርስቲያን ጠርዝ የሚንጠለጠሉት ሿሿቴወች ትርጉም ምንድን ነው
2026-11-01 17:49:27
1
E¥oብ የ ፲፪ :
ይሄኮ ምስጢር ነው😔 ኧረ ተዉ ግን
2026-11-02 05:54:21
1
🎧Yoniana🎧 :
🥰🥰🥰
2026-11-02 03:48:25
1
Beki 🎼🎵 :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🙏
2026-11-02 05:04:30
1
ኪዳነ ምህረት እናቴ :
🙏🙏🙏
2026-11-02 05:22:39
1
To see more videos from user @mekdiwalt, please go to the Tikwm
homepage.