@bethlehem.kassu: (ዘ-ሐበሻ ዜና) የሱማሊላንድ መንግስት ‹‹በኢትዮጵያዊያን ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት አወግዛለሁ›› አለ፡፡ የሱማሊላንድ መንግስት ማስታወቂያ ሚኒስትርና የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት ቡርሀን ጃማ ቡቱን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በአገሪቱ ቦራማ የተሰኘ አካባቢ የኢትዮጵያ ዜጎችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት እየተካሄደ መሆኑን ገልፀው ድርጊቱን አጥብቀው እንደሚያወግዙት አስታውቀዋል፡፡ ለዚህ ድርጊት ተጠያቂ የሆኑትን ለህግ እንደሚያቀርቡም ቃል ገብተዋል፡፡ ቃል አቀባዩ ሲናገሩ ‹‹የቦራማ ሲቪል ማህበረሰብና ፖለቲካ መሪዎችም ይህንን ድርጊት አውግዘዋል፡፡ ብሄርን ተገን ያደረገ ጥቃት፣ መድልኦና ድንበር ዘለል ውጥረቶችን ለማቀጣጠል የሚደረገውን ሙከራ ተቃውመው በክልሉ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር ጥሪ አቅርበዋል›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹የሲቪል ማህበረሰብና የፖለቲካ መሪዎቹ ማንም ሰው በዜግነቱ ወይንም በብሄሩ ምክንያት ኢላማ መሆን የለበትም በሚል ያስተላለፉትን መልእክት የሱማሊላንድ መንግስትም ይጋራል፡፡ የሱማሊላንድ እንግዳ ተቀባይነትና ሰላማዊ አብሮ የመኖር እሴቶች ለሁሉም የሰው ልጅ ሊሰራ ይገባዋል፡፡ የኦሮሞ ወንድምና እህቶቻችን በህግ መሰረት ክብር፣ ደህንነትና እኩል ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ብሄርን ተገን ያደረገ አመፅ ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም›› በማለት አስረድተዋል፡፡ አክለውም ‹‹እንደመንግስት የውጭ ዜጎችን ኢላማ ያደረጉ ድርጊቶች የሱማሊላንድን ስምና መረጋጋትን የሚጎዳ የተደራጀ ዘመቻ አድርገን እንቆጥረዋለን›› በማለት አስጠንቅቀዋል፡፡ ቃል አቀባዩ የውጭ ዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ሀላፊነት በመንግስትና በተቋማቱ ስር እንደሚወድቅ ገልፀው ይህም ደህንነታቸውን ማረጋገጥ፣ ክብራቸውን መጠበቅና ህጋዊ መብቶቻቸውን ማስከበርን እንደሚያካትት አስረድተዋል፡፡ ማንኛውም ግለሰብ የውጭ ዜጋን በሱማሊላንድ አስተዳደር ስር ካሉ አካባቢዎች በሀይል ማስወጣት፣ ጥቃት የመፈፀምና ንብረታቸውን የማውደም ስልጣን እንደሌለውም አስታውቀዋል፡፡ የውጭ ዜጎችን የመኖሪያ ፈቃድና የደህንነት ጉዳዮች የሚመለከቱ ጉዳዮች በህግ በተቋቋሙ አካላት በኩል ማለፍ እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡
Zena Bethel
Region: US
Sunday 01 November 2026 15:24:55 GMT
Music
Download
Comments
Ethiopia 🇪🇹 :
Congratulations
2026-11-01 16:19:21
0
To see more videos from user @bethlehem.kassu, please go to the Tikwm
homepage.