@southjersey.sidequests: We tried Ruchi Indian Cuisine and had a great experience! 🇮🇳 The butter chicken was super flavorful and tender, with a rich, creamy sauce that was perfect with the garlic naan. The naan was fresh, warm, and honestly one of the highlights of the meal 🤤 The staff were really friendly and polite, and everything came out fresh. The prices were also very reasonable compared to some other Indian restaurants we’ve tried in the area. Great food, friendly service, and a solid value overall. Definitely a spot we’d come back to when we’re craving Indian food! 🇮🇳🍛 #mtlaurelnj #southjersey #sjfoodie #indianfood #mountlaurelnj

South Jersey Sidequests
South Jersey Sidequests
Open In TikTok:
Region: US
Sunday 01 November 2026 20:41:21 GMT
1490
211
0
4

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @southjersey.sidequests, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

ፍቅር አገረሸብኝ 🤕 ✍️አንድ ዘፋኝ ዘመን ተሻጋሪ ስራ ከሰራ በቀጣዮ ትውልድ መወደዱ፣ መከበሩ መሰማቱ ሲኖር የነበረ እና ወደ ፊትም የሚኖር እውነታ ነው።  አንዳችን ጥላሁን ገሰሰ፣ ሌላችን መሐሙድ አህመድ፣ ፀሃዬ ዮሃንስ፣ ቴዎድሮስ ታደሰ፣ ሙሉቀን መለሰ፣ ነዋይ ደበበ፣ አስቴር አወቀ በአጭሩ ሁሉም ሰው በውስጡ ልዮ ቦታ የሚሰጠው ዘፋኝ አለው። አሁን እያወራሁ ያለሁት ስለ ዘፈን ችሎታ ሳይሆን በውስጣችን ተወዳጅ ስለሆኑት ዘፋኞቻችን ነው። ታዲያ ጥቂት ለማይባሉ ሰዎች የምንግዜም ምርጥ ድምፃዊ ነው የሱ ሙዚቃዎች በበርካቶች ህይወት ውስጥ ትልቅ ትዝታ እና ታሪክ የያዙ ናቸው እያንዳንዱ ስንኞች አንድን የህይወት ምዕራፍ ያስታውሳሉ ከሙዚቃም በላይ ያለፉትን ዘመን ማሳያ መነፅርም ሆነው ተዛምደዋቸዋል  በትህትናው እና በበሳል ሙዚቃዎቹ የሚታወቀው ምንአልባትም ሙዚቀኛ ባይሆን ኖሮ ስመጥር እግርኳስ ተጫዋች ይሆን እንደነበር የሚመሰከርለት የብዙዎችን ሰርግ ቆሞ ያደመቀው ጥቂት የማይባሉትን ልብ በሚነኩ ውብ ሙዚቃዎቹ ያላቀሰው የዛሬው ተመስጋኝ ባለታሪካችን
ፍቅር አገረሸብኝ 🤕 ✍️አንድ ዘፋኝ ዘመን ተሻጋሪ ስራ ከሰራ በቀጣዮ ትውልድ መወደዱ፣ መከበሩ መሰማቱ ሲኖር የነበረ እና ወደ ፊትም የሚኖር እውነታ ነው። አንዳችን ጥላሁን ገሰሰ፣ ሌላችን መሐሙድ አህመድ፣ ፀሃዬ ዮሃንስ፣ ቴዎድሮስ ታደሰ፣ ሙሉቀን መለሰ፣ ነዋይ ደበበ፣ አስቴር አወቀ በአጭሩ ሁሉም ሰው በውስጡ ልዮ ቦታ የሚሰጠው ዘፋኝ አለው። አሁን እያወራሁ ያለሁት ስለ ዘፈን ችሎታ ሳይሆን በውስጣችን ተወዳጅ ስለሆኑት ዘፋኞቻችን ነው። ታዲያ ጥቂት ለማይባሉ ሰዎች የምንግዜም ምርጥ ድምፃዊ ነው የሱ ሙዚቃዎች በበርካቶች ህይወት ውስጥ ትልቅ ትዝታ እና ታሪክ የያዙ ናቸው እያንዳንዱ ስንኞች አንድን የህይወት ምዕራፍ ያስታውሳሉ ከሙዚቃም በላይ ያለፉትን ዘመን ማሳያ መነፅርም ሆነው ተዛምደዋቸዋል በትህትናው እና በበሳል ሙዚቃዎቹ የሚታወቀው ምንአልባትም ሙዚቀኛ ባይሆን ኖሮ ስመጥር እግርኳስ ተጫዋች ይሆን እንደነበር የሚመሰከርለት የብዙዎችን ሰርግ ቆሞ ያደመቀው ጥቂት የማይባሉትን ልብ በሚነኩ ውብ ሙዚቃዎቹ ያላቀሰው የዛሬው ተመስጋኝ ባለታሪካችን "ዘመን የማይሸረው ድምፀ መረዋው ፀጋዬ እሸቱ🙌🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ እሱ ስራውን አክባሪ፣ ለትዳሩ ታማኝ፣ እንደበርካታ ኢትዬጲያዊያን ለእናቱ ልዮ ፍቅር ያለው፣ ዝናውን መሸከም የሚችል ጫንቃ ያለው፤ ማህበራዊ ህይወቱ A+የሆነ ተግባቢ ሰው ነው። ስለ ፍቅርም፣ ስለ ትዳርም፣ ስለ እናትም፣ ስለ ሰርግም፣ ስለ ሃገርም፣ ስለ ማጣትም ሲዘፈን፣ ዘፈኖቹ ውስጥህን ሰርሰው ይገባሉ። በዘመን ተሻጋሬ ወርቃማ ድምፁ “እሄዳለሁ ሀረር ባቡር ተሳፍሬ… ያቺ ጉብል ወጣት አያታለሁ ድሬ…” በሚል አይረሴ ዘማው የሀረርን የፍቅር አገርነት፣ ያፈቀሩት ማጣት የሚፈጥረው ህመም ከፍ አድርጎ ባሳየን “ለሰርግዋ ተጠራሁ ለሌላ ሲድሯት…” በተሰኘ አራሪ ሙዚቃው ሁላችን ጋር የማይረሳ ሆኖ ቀቷል፡፡ በትላልቅ ጉዳዮች የተሞሉ ምስል ከሳች በሆኑ ቃላት የተከሸኑ ባማሩ ዜማዎች የተዋዙት ሙዚቃዎቹ ከጆሮ ሲደርሱ ለመስማት ያስገድዳሉ፡፡ በሙዚቃው ዘርፍ ነግሶ፤ የተለያዩ ጉዳዮቻችንን ዳሶ፣ በብዙዎች ዘንድ ተወድሶ ትልቅ ክብርና ዝናና እውቅናን አትረፏል፡፡ በስራዎቹ ክብርን ተቀደጅቷል፡፡ 📍ድምፃዊ ፀጋዬ እሸቱ፡፡ ትውልዱ እዚሁ አዲስ አበባ በተለምዶ ጥይት ቤት ይባል የነበረው (አሁንፓርላማ ያለበት) አካባቢ ነው፡፡በቅሎ ቤት አካባቢ የሚገኘው ሪቼ ወይም መስከረም ማዞሪያ ደግሞ የልጅነት ጊዜውን ያሳለፈበት፡፡ በጠመንጃ ያዥ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በምስራቅ አጠቃላይ ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርን ተከታትሏል፡፡ ከአያቶቹ ጋር ያደገው ፀጋዬ በልጅ አያያዝ ላይ ጥብቅ የነበሩት አያቹ ኢትዮጵያዊ ስነ ምግባር ተላብሶና ትሁት ሆኖ ዛሬ ድረስ እንዲገኝ ምክንያት የሆነውታል፡፡ ገና ልጅ ሆኖ የህይወትን መልካምማ ክፉም ገጠመኝ ያሳለፈው ፀጋዬ አሁን ለተገኘበት ስኬት መነሻው በልጅነቱ ያሳለፈው ውጣ ውረድ ምክንያት ሆነው፡፡ ከሬዲዮ የዘፈን ምርጫ ፕሮግራም ላይ የሚሰማቸው ሙዚቃዎች በፉጨት ያዜም ነበር፡፡ ህይወት ፈቅዳ ከሪቼ ወደ መገናኛ አካባቢ ተዘዋወረ፡፡ እዚያ የሁለተኛ ትምህርቱን እየተማረ ባለበት ወቅት በትምህርት ቤት ወጣቶች የመሰረቱት የኪነ ጥበብ ቡድን ላይ በአጋጣሚ ተገኝቶ የጋሽ ማህሙድን ዜማ በእነጉርሮ አቀረበ ያኔ የተመለከቱት ሙዚቃ እነዲሞከር መንገርና ማበረታታት ያዙ፡፡ የዓለም አቀፍ የላባደሮች ቀን (መይዴይ) ሲከበር ከቀበሌው ተመርጦ በሰልፈኛ መሀል ሆኖ የወቅቱ መዝሙር ሲመራ ይበልጥ ህዝብ ጋር መታወቅ ጀመረ፡፡ ምስራቅ አጠቃላይ ላይ እያለ በተካሄደ የቀበሌ የሙዚቃ ውድድር ተወዳዳሮ ከተመረጡት አንዱ ሆነ፡፡ ከፍተኛ 16 ኪነት የተመሰረተበት ጊዜ ነበር፡፡ ዳዊት መድፈሩ ከተባለ ሌለ ድምፃዊ ጋር ፀጋዬ ተመርጦ ያን ቡድን ተቀላቀለ፡፡ ያኔ በመሰረተ ትምህርት ዘመቻ ወቅት ገነው ከወጡ መዝሙሮች መካከል የፀሐዬ ዮሀንስ “ማንበብና መፃፍ..”ከሚለው ዜማ ጋር የፀጋዬ እሸቱ “አይኖሩም… አይኖሩም የማያነቡ አይኖች…አይኖሩም አይኖሩም የማይፅፉ እጆች” የሚሉት ይገኙበታል፡፡ ለፀጋዬ ይህ ስራ የመጀመሪያውና ወደህዝብ ያቃረበ ስራ ነው፡፡ ፀጋዬን ያስገኘ ልዩ ሰው፤ እኔ እዚህ የመድረሴ መሰረት ብሎ እራሱ ፀጋዬ የሚመሰክርለትና የበዙ ስራዎቹ ደራሲ ደረጄ ተፈራ ነው፡፡ ለእርሱ ስኬት ታላቅ ቦታ እንዳለው ይገልፃል፡፡ ፀጋዬ ሙዚቃ ለመስራት ቀላል ባልነበረበት በዚያ ጊዜ የራሱን ሙዚቃ ሰርቶ ለህዝብ ለማቅረብ ብዙ ውጣውረዶችን አሳፏል፤አሳታሚ ፍለጋ ብዙ ማስኗል፡፡ በመጨረሻም በ1979 ሶልኩኩ የተባለ ሙዚቃ ቤት ባለቤት አቶ ሳህሉ ጋር በአርቲስት ልመንህ ታደሰ አማካኝነት ተገናኝቶ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ሲደመጡ ልዩ ጣዕም ያላቸው ተወዳጅ ሙዚቃዎቹ ወደ ህዝብ መቅረብና የእውቅና መንበር ላይ መገኘት ቻለ፡፡ መንገድ ላይ መፅሀፍ አይቶ ማለፍ የማሆንለት ፀገዬ ማንበብ ያዘወትራል፡፡ እቤቱ በየጊዜው ያነበባቸውና መደርደሪያው ላይ በክብር ያስቀመጣቸው ቁጥራቸው 500 የሚደርሱ መፅሀፎች ይገኛሉ፡፡ሙዚቃ እነደመዝናኛም መጥናት ያዘወትራል፡፡ ለቤተሰቡ ልዩ ፍቅርና ክብርያለው ፀጋዬ ብዙ ጊዜውን ከቤተሰቡ ጋር የእረፍት ሰዓቱን ያሳልፋል፡፡ ኳስ መመልከት ይወዳል፡፡ እስፖርት መስራትን ያዘወትራል፡፡ በማህበራዊ ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳታፊም ነው፡፡ አገራዊና ህዝባዊ ጉዳዮች ላይ ከማንም በላይ የሚያሳስበው የማህበረሰቡን ህይወትና የአገር ለውጥ አጥብቆ የሚመኝ ለዚያም በተቻለው የሚለፍ አገር ወዳድም ነው፡፡ በተለያዩ መድረኮች ላይ ተሰምተው የማይጠገቡ ዘመናትን የተሻገሩ ሙዚቃዎቹን በማቅረብ አዳዲስ ስራዎቹን ማጥናትና ሙዚቃን መመርመር አሁን ድረስ የሚዘወትርበት ድንቅ ስብእና ያለው ትልቅ ሰው ነው፡፡ እኔም ለዛሬ በሶልኩኩ ሙዚቃ ቤት በኩል በ1981 ካሳተመው እጅግ ተወዳጅ አልበሙ በጣም የምወደውን "ፍቅር አገረሸብኝ"ን ለትውስታ ጋበዤያቹ እጅግ ለማከብረው ፀጋዬ እሸቱ እድሜ እና ጤና እየተመኘሁ አበቃሁ🙌🙏 🗣ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 musictube 🇪🇹 #fyp #ፀጋዬእሸቱ #አልዋሽምነበረ❤ #ethiopianmusic #musictube369

About