@melakufekadu1: አመለካከት (Attitude) ምን ማለት ነው? ********* ብዙ ጊዜ አመለካከት ማለት የስሜት መግለጫ ይመስለናል። ነገር ግን እውነተኛው የአመለካከት ትርጉም ከዚህ በላይ ነው። አመለካከት የሚፈጠረው ሶስት ወሳኝ ነገሮች ሲደመሩ ነው፡- ? ሀሳብ (Thoughts)፣ ስሜት (Emotions) እና ድርጊት (Actions)። የምንፈጥራቸው ሀሳቦች፣ የሚሰሙን ስሜቶች እና የምናደርጋቸው ተግባራት በአንድነት ተደምረው ማንነታችንን ይመሰርታሉ። ሀሳብህን ተመልከት፣ ቃል ይሆናልና። ቃልህን ተመልከት፣ ድርጊት ይሆናልናል። ድርጊትህን ተመልከት፣ ልማድ ይሆናልና። ልማድህን ተመልከት፣ እምነትህ ይሆናልና። እምነትህን ተመልከት፣ ማንነትህን ይቀርጻሉና። ማንነትህን ተመልከት፣ ፓራዳይምህ ይሆናልና። አመለካከት የሶስቱ ድምር ውጤት ነው •ሀሳብ (Thoughts):- ሁሉም ነገር የሚጀምረው በአስተሳሰባችን ነው። የምናስባቸው ነገሮች የአመለካከት ዘር ናቸው። •ስሜት (Emotions):- የምናስበው ነገር በውስጣችን ስሜትን ይፈጥራል። ስሜቶች የሀሳብ ጉልበት ናቸው። •ድርጊት (Actions):- ሀሳብና ስሜት በእኛ ውስጥ ሲቀመጡ ድርጊት ይሆናሉ። የምንሠራው ተግባር የአመለካከት ውጤት ነው። አመለካከት (Attitude)፣ ባህሪ (Behavior) እና ማንነት (Character) ✓ ባህሪ (Behavior): የአመለካከትህ ውጫዊ ገጽታ ነው። ባህሪህ የአመለካከትህ ነፀብራቅ ነው። ✓ ማንነት (Character): ደግሞ የባህሪህ ጥልቅ መሰረት ነው። ተከታታይ የሆኑ ሀሳቦች፣ ስሜቶች እና ድርጊቶች ለረጅም ጊዜ ሲደጋገሙ፣ ማንነትን ይገነባሉ። ማንነትህ የሚታየው በችግር ጊዜ በምታሳየው ባህሪ ነው። በአጭሩ፣ አመለካከት የውስጥ ዝንባሌና ቅድመ-ውሳኔ ነው። ባህሪ ደግሞ የዚያ ዝንባሌ ውጫዊ መግለጫና የምንወስደው ተጨባጭ እርምጃ ነው። ማንነት ደግሞ በዛ ምርጫ ምክንያት የምንሆነው ማንነት ነው። ለውጥን ከፈለግክ፣ከውጫዊ ባህሪህ ሳይሆን ከውስጣዊ ሀሳብህ ጀምር። በየዕለቱ የምታስባቸውን ነገሮች ምረጥ አድርግ። የአንተ ምርጫዎች አመለካከትህን ይፈጥራሉ፤ አመለካከትህ ባህሪህን ይመሰርታል፤ ባህሪህ ደግሞ ማንነትህን ይገነባል። 👉 ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን የቴሌግራም ገጻችንን ተቀላቀሉ 👇👇👇 https://t.me/melakufek https://www.facebook.com/share/ https://www.tiktok.com/@melakufekadu1?_r=1&_t=ZS-99aqd4Xta3c
መላኩ ፍቃዱ - Melaku Fekadu
Region: ET
Monday 02 November 2026 02:48:46 GMT
Music
Download
Comments
ጠባቂየ ብርቱ ነው!! :
great
2026-11-07 12:54:05
0
2222 :
yes
2026-11-02 23:55:39
0
kassa :
🥰🥰🥰
2026-11-02 10:41:27
0
To see more videos from user @melakufekadu1, please go to the Tikwm
homepage.