@virginia.rosettin: stavamo morendo dal ridere grazie a @vittox, il meme del gruppo. @simo🌟 @Luigi Salemi🐐

vi
vi
Open In TikTok:
Region: IT
Monday 02 November 2026 17:40:42 GMT
168810
23283
39
160

Music

Download

Comments

zoe47440
~Zoe🌺 :
PRIMAAAA
2026-11-02 17:46:31
349
alessandra.b010
💜•ALE•💜 :
black pink💖
2026-11-02 19:31:55
124
desireeballotta7
Desi🎀 :
Siii vogliamo la parte dueeee
2026-11-02 17:55:50
42
mattysarrr
matty :
il codice di onore dei samurai AHAHAHHA
2026-11-02 21:09:28
90
lalli_18644
🎀Laura🎀 :
codice dei samurai😂😂😂
2026-11-02 20:13:39
103
simona.trozzola
simo🌟 :
non ho mai riso così tanto per registrare un video
2026-11-02 23:22:42
15
anto_ferrara1033
anto_Ferrara :
riassunto del video
2026-11-02 22:25:58
8
sofalascrofa011
❤️✨Sofy✨❤️ :
Raga
2026-11-02 18:48:04
28
spamm._gaia._
gaia🎀🌷 :
non so perché ma mi danno le vibes di aurora e mura e giulia e ergi
2026-11-02 23:56:23
6
jisooforever_24
☆𝘝𝘪𝘵𝘵𝘰ᴷᴾᴼᴾ🇰🇷☆ :
omg le balckpink
2026-11-02 20:27:16
8
cristal.anastasia8
༘♡ Nastea ⋆。˚` :
siiii parte dueeeee plssss
2026-11-02 21:36:55
4
_dero10_
andreadero_💎 :
CUSANO ZONE
2026-11-02 22:00:27
2
__giadaa.f
𝓖𝓲𝓪𝓭𝓪🪷🪽 :
anavrin
2026-11-02 21:35:03
3
fede1043
Fede🫯🧟 :
primo
2026-11-02 17:44:43
1
giuliabucciarelli1
Giulia :
settima🥰
2026-11-02 18:12:16
1
b.e.a.t.r.i.c.e82
~•B E A T R I C E •Ti insegue~ :
ciaoooooooooo
2026-11-02 18:23:01
2
spamm_la.beba
spamm_la.beba :
2026-11-02 17:46:45
4
lla.lodi
𝓛 :
prima
2026-11-02 17:45:18
0
chiara26419
𝓵𝓮𝓸𝓷𝓸𝓻𝓪🐆🌺 :
😂😂😂😂
2026-11-03 06:07:52
0
ggiorgina3
gio🎭 :
mi sto pisciando AHAHAHAH
2026-11-02 22:34:04
0
user6zq6vrvfej
𝓔🎭 :
Cusano menzionato hahaha
2026-11-02 22:19:51
0
agustn.lima81
carlo valentino :
😁😁
2026-11-03 00:11:39
0
dani12.931
daniela :
parte dueww
2026-11-03 08:26:00
0
spamm.ritaaa0
la_ritaaa :
2026-11-02 17:47:58
0
To see more videos from user @virginia.rosettin, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

እመቤቴ ሆይ እንደ ድኃ የዕለት ሲሳይን ለማግኘት ስትባዝኚ፣ ምግብ የሚያቀብልሽ፣ ውኃ የሚያጠጣሽ አጣሽ እንዴት አደርሽ እመቤቴ ከቤትሽ ከወጣሽ ከሀገርሽ ከተሰደድሽ እነሆ ሀያ ስድት ቀን ተቆጠረ ለመሆኑ እንዴት አለሽ እመቤቴ እስኪ አብረን በእግረ ኅሊና እንከተላት ግዕዝ ​በቤተ መቅደስ ዘልህቀት ወለተ ካህናት እንዘ ትሴሰይ ሥሩዓ። ኅብስተ ሰማይ ኅቡዓ ወጽዋዓ ወይን ምሉዓ። እፎ ከመ ነዳይ ሲሳየ ዕለት ኃጢአ። ተአገሠት በብሔረ ባዕድ ረኃበ ወጽምዓ። መኑ ከማሃ ዘረከበ ግፍዓ። ​ ትርጉም ​በክብር ቤተ መቅደስ (በቅድስተ ቅዱሳን) የካህናት ልጅ (ድንግል ማርያም) የተዘጋጀውን መብል ስትመገብ፣ የሰማይ ሕብስት የተሰወረውን የሕይወት እንጀራ እና የተሞላውን የወይን ጽዋ (የእግዚአብሔርን ጸጋ) እየተቀበለች ትኖር የነበረችው ንጽሕት ድንግል፤ እንደምን ያለች ድኃ (እንደ ተራ ሰው) የዕለት ሲሳይን (ምግብን) ለማግኘት በባዕድ ሀገር ረኃብንና ጽምእን የታገሠች? እንደ እርሷ ያለ ግፍና መከራ የተቀበለ ማን አለ? ​ ማብራርያ ​ንጽጻር (ንጽጽራዊ ምልከታ)  በቤተ መቅደስ ሳለች መብልና መጠጧ ከሰማይ በሰማያዊ መላእክት እጅ ይቀርብላት ነበር። የሰማይ ሕብስት የተባለ ክርስቶስን ትመገብ ነበር፤ የምሥጢር ጽዋም ትጠጣ ነበር። ​ስደትና ውርደት ያ የክብር ባለቤት የሆነች ንግሥት፣ በሄሮድስ ስደት ምክንያት ሕፃኑን ጌታ አዝላ በበረሃ ስትዞር እንደ ተራ ድኃ የዕለት እንጀራ አጥታ፣ በባዕድ ሀገር (በግብፅ ምድር) ረኃብንና ጽምእን፣ የፀሐይን ሐልዎ (ሙቀት) እና የእግርን መታከት (ድካም) በታላቅ ትዕግሥት ተቀበለች። ​የግፍ መጠን «መኑ ከማሃ ዘረከበ ግፍዓ» ሲሉ፣ ከእርሷ በላይ ንጹሕ ሆኖ ሳለ መከራን፣ ስደትንና ግፍን የተቀበለ የለም በማለት የእመቤታችንን የድካም ጥልቀትና የሰማዕትነትን ዋጋ ያመለክታሉ።  የድንግል ማርያም ሕይወት በሁለት ታላላቅ ምዕራፎች መካከል ያለፈ ነው አንደኛው በጽርሐ ቤተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ በሰማያዊ ግርማ፣ በመላእክት አገልግሎት እና በንጽሕና የኖረችበት ዘመን ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስን አዝላ በግብፅ በረሃዎች የተሰደደችበት፣ ረኃብንና ጽምእን፣ እሾህና አሜከላን የተቀበለችበት ዘመን ነው። ​ይህንን ታላቅ ምሥጢር በልቦናችን እያሰብን፣ ከቤተ መቅደስ ዘልህቀት አንሥቶ እስከ ግብፅ ስደት ድረስ ያለውን የእመቤታችንን የዕለት ሥቃይና እንባ እንዲህ እንከተለዋለን፦ ​በቤተ መቅደስ የነበረው ሰማያዊው ክብር እና የንጽሕና ኑሮ ​«በቤተ መቅደስ ዘልህቀት ወለተ ካህናት እንዘ ትሴሰይ ሥሩዓ። ኅብስተ ሰማይ ኅቡዓ ወጽዋዓ ወይን ምሉዓ።» ​እመቤቴ ሆይ! በዚያን ዘመን በጽርሐ ቤተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ሳለሽ የነበረው ክብር እንዴት ይታረቃል? የአባትሽ የኢያቄም እና የእናትሽ የሐና ውድ ልጅ፣ የካህኑ የዘካርያስ እጅ የሚጠብቅሽ፣ የሰማይ መላእክተ ሰማይ እየተቀበሉ፣ ሰማያዊ ምግብ እያቀረቡልሽ፣ የሰማይ ኅብስት እየበላሽ፣ የምሥጢር ጽዋ እየጠጣሽ በታላቅ ግርማና መለኮታዊ ሰላም የኖርሽ አንቺ ንግሥት ነሽ ​በዚያች ቅድስት ቦታ ሳለሽ  እግሮችሽ በሐርና በወርቅ የተጠለፈ መሠረት ላይ ነበሩ የሚጠጣ የሕይወት ውኃ፣ የሚበላም ከሰማይ የሚወርድ የምሥጢር መብል ነበር ንግሥተ ሰማያት ወምድር ነሽና መላእክት እንደ ንግሥት አድርገው ያገለግሉሽ ነበር፤ ሱራፌልና ክሩቤል ጥላ ይሆኑልሽ ነበር ​ነገር ግን እመቤቴ ሆይ! ያ የሰማይ ክብርና ግርማ፣ ያ የቤተ መቅደስ ውበትና መረጋጋት ዛሬ ወዴት ሄደ? ​«እፎ ከመ ነዳይ ሲሳየ ዕለት ኃጢአ። ተአገሠት በብሔረ ባዕድ ረኃበ ወጽምዓ። መኑ ከማሃ ዘረከበ ግፍዓ።» ​ እመቤቴ ሆይ! እንዴት አደርሽ? ከናዝሬት ቤትሽ ከወጣሽ፣ ከቀያችሁና ከሀገርሽ ከተሰደድሽ ዛሬ ሀያ ስድተኛ ቀን ሆነሽ በዚያን ጊዜ በቤተ መቅደስ የነበርሽው ንግሥት፣ ዛሬ በበረሃውና በሰደደው ሐሩር መንገድ፣ ጽላሎትና ጥላ በሌለበት፣ የውኃ ጠብታ በሚጠፋበት አሸዋማ ቦታ ላይ ትገኛለሽ ​እንደ ተራ ድኃ የዕለት ሲሳይን ለማግኘት ስትባዝኚ፣ ምግብ የሚያቀብልሽ፣ ውኃ የሚያጠጣሽ አጥተሽ «እመቤቴ፣ በዚህ የድንጋይ ጥላ ሥፍራ ትንሽ አረፍ በይ» የሚልሽ አንዳችም ፍጡር ሳይኖር, የደከመው እግርሽ፣ የተጓዘው የርቀት ጉዞ እጅግ ያስጨንቀኛል፤ ልብንም ያሰንፈዋል፤ እመቤቴ እንዴት ሰነበትሽ? ​በባዕድ ሀገር በረሃዎች ውስጥ ስትዘዋወሪ፣ የደረሱብሽ መከራዎች በምንስ ቃላት ይገለጣሉ? ባንቺ መገኘት ሕዝቡና አህዛቡ ተቀድሰዋል፤ ተባርከዋል፤ የግብፅ አሕዛብም በእግርሽ መረገጥ መቤዠትን አግኝተዋል የአዳም ልጆችም ታላቅ በረከት አግኝተዋል። አንቺ ግን ከመቅደስ ወጥተሻል ዕረፍትም ተነፍጎሻል። ባንቺ መገለጥ ምድርና ሰማይ አበባ ሆነዋል፤ ፍጥረታት ሁሉ በአንቺ ፈክተዋል፤ ነገር ግን አበባይቱ እመቤቴ! ላንቺ ግን ምድር እሾህና አሜከላ አቀረበችልሽ ​የእግርሽ ጫማ አለመኖሩ፣ የለበሽው ልብስ በጊዜ መታመሙና መቅደዱ፣ በክረምትም በበጋም የሕፃኑ የልጅሽ የኢየሱስ ክርስቶስ ማልቀስ፣ ረኃብንና ጽምእን፣ የሌሊቱን ቁርና የቀኑን ሐሩር መቀበሉ ልብን ይሰብራል፣ ነፍስንም ያውካል፤ በዚያች በረሃ በዛፎች ጥላ ሥፍራ ያየሽው መከራ ስንቱ ተነግሮ ያልቃል! ​ወዮ! የዓለም መድኃኒት አዝለሽ፣ የፈጣሪን እናትነት ተሸክመሽ፣ በባዕድ ሀገር በረሃዎች ስትዞሪ የሰማይ መላእክት ዝም ማለታቸው፣ መሬትም በድዳ ዝምታ ማስተናገዷ ያስደንቃል። ሕፃኑ ኢየሱስ በደረቱ ላይ ሲንዠቀዠቅ፣ ጡትሽ ሞልቶ ሲጠማው፣ የሚጎርሰው ሳይኖር ስትባዝን የታየው ጽዋዕ መከራ እጅግ ከባድ ነው ​«መኑ ከማሃ ዘረከበ ግፍዓ» እያሉ ሲያለቅሱ፣ ከእርሷ በላይ ንጹሕ ሆኖ ሳለ መከራን፣ ስደትንና ግፍን የተቀበለ የለም በማለት የእመቤታችንን የድካም ጥልቀትና የሰማዕትነትን ዋጋ ያመለክታሉ ​እንዲህ እያልን የድንግል ማርያምን እና የልጅዋን የኢየሱስ ክርስቶስን ስደትና መከራ በልቦናችን በማሰብ፣ በጸሎትና በዕንባ ከእርሷ ጋር እንኖራለን። ሐዘኗን ሐዘናችን አድርገን፣ እንባዋን እንባችን አድርገን፣ በዚያች በበረሃ ጎዳና ከእርሷ ጋር እንጓዛለን፤ ስደቷንም እናስባለን። ​እመቤቴ ሆይ! በስደትሽ ዘመን የደረሰብንን መከራ እያሰብን ከልብ እናለቅሳለን፤ በጸሎትሽም አስቢን፤ አሜን። ይቀጥላል እግዚአብሔር ሆይ የሚሳንህ ነገር የለምና የራቀውን አቅርበህ የረቀቀውን አጉልተህ እየሰማነው ካለነው መርዶና ሰቀቀን ዕረፍተ ሥጋንና ዕረፍተ ነፍስን አትንሣን ጸልዩ በእንተ ሰላም  ስለ ሰላም እንጸልይ ስለ ሀገራችን እንጸልይ ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንጸልይ  በጭንቅ በመከራ ስላሉት እንጸልይ በረሀብ በስደት ስላሉት እንጸልይ በጽኑ ሕመም ተይዘው ስለሚሰቃዩት እንጸልይ ስለ ሃይማኖት መሪዎች አባቶቻችን እንጸልይ ስለ ሀገር መሪዎች እንጸልይ የሰላም የምህረት የቸርነት ባለቤት እግዚአብሔር ሰላሙን ምህረቱን ቸርነቱን አይንሳን አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ ዘዝዋይ ገዳም ጥቅምት 21/2/2019 ✍️ ⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️#ወርሃ_ፅጌ #ዝክረ_ቅዱሳን #ማርያም_ሆይ_አማልጅን_ልጅሽ_ክርስቶስ #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር

About