@muhiboneqrm: FF Core #foryou #growmyaccount #plesesupport

Brazil Free Fire
Brazil Free Fire
Open In TikTok:
Region: MX
Monday 02 November 2026 21:58:33 GMT
3954
85
1
3

Music

Download

Comments

diegomora58261
Diego Mora :
😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂
2026-11-02 23:45:40
0
To see more videos from user @muhiboneqrm, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

አሜን አልበም 🫠 ✍️ውልደቱ በደቡብ ኦሞ ዞን በሀመር ባኮ ነው። ሙዚቃን 'ራስ አንዳርጌ' የሀይስኩል ትምህርትቤት ትምህርቱን ሲከታተል በነበረበት ወቅት እንደጀመረው ይነገራል። ለትምህርት ቤቱ የሙዚቃ ባንድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል። ለሙዚቃ ካለው ፍቅር የተነሳ በትምህርት ቤት ቆይታው በባንድ ውስጥ የነበረውን  ልምድ እና በሙዚቃ ሊደርስበት የሚፈልገውን ደረጃ በማሰብ ለተሻለ የሙዚቃ ስራ ከሀመር ወደ መዲናችን አዲስ አበባም መጥቷል። ወደ አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ 'አምባሳደር ቲያትርን
አሜን አልበም 🫠 ✍️ውልደቱ በደቡብ ኦሞ ዞን በሀመር ባኮ ነው። ሙዚቃን 'ራስ አንዳርጌ' የሀይስኩል ትምህርትቤት ትምህርቱን ሲከታተል በነበረበት ወቅት እንደጀመረው ይነገራል። ለትምህርት ቤቱ የሙዚቃ ባንድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል። ለሙዚቃ ካለው ፍቅር የተነሳ በትምህርት ቤት ቆይታው በባንድ ውስጥ የነበረውን ልምድ እና በሙዚቃ ሊደርስበት የሚፈልገውን ደረጃ በማሰብ ለተሻለ የሙዚቃ ስራ ከሀመር ወደ መዲናችን አዲስ አበባም መጥቷል። ወደ አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ 'አምባሳደር ቲያትርን" ተቀላቅሎ ሲሰራ ቆይታ ያደረገ ሲሆን። ከዛም ከወጣ በኃላ የ "ራስ ቲያትር" ባህላዊ ባንድን ተቀላቅሎ ሰርቷል። ከ70ቹ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለረዥም አመታት በሙዚቃ ላይ ቆይታ ያደረገ ሲሆን ስድስት አልበሞችንም ለሙዚቃ አፍቃሪያን ከማድረሱም በላይ ከተለያዩ የሱ ዘመን ሙዚቀኞች ጋር በጋራ በመሆን የጋራ አልበም እና የኮሌክሽን ስራዎችን ሰርቷል። የመጀመርያ "የጥቅምት አበባ" አልበሙን በ1976 ከሮሃ ባንድ ጋር በመሆን በታንጎ የሙዚቃ መሸጫ በኩል ለህዝብ ጆሮ አድርሷል። ቀጥሎም "ማዕበል ነው" በ 1979፣ "መብረቅ" በ1980 ፣ "የክብሬ መመኪያ" በ 1982፣ "የጅማ ልጅ" በ1985 ፣ "ሀገሬን አልረሳም" በ1990 እና ዛሬ ይዤላቹ የመጣሁትን "አሜን" በ 1995 ለሙዚቃ አፍቃሪያን ያደረሳቸው አልበሞች ሲሆኑ ቀደም ያሉ ስራዎቹን ከእደገና remix አድርጎ በመስራት በ1999 ዓ.ም ወደ ሚሊኒየሙ መዳረሻ ያወጣው አልበምም የመጨረሻ ተጠቃሽ ነው። ስድስት የግል አልበሞቹ በተጨማሪ ሶስት የጋራ አልበም ከሀመልማል ፣ከፋንትሽ እና ከስዩም ጋር በ1981 ; ከ አረጋሀኝ ወራሽ፣ከፀጋዬ እሸቱ ጋር ' መተባበር ቢኖር' እና ሌሎች ሙዚቃዎችን እንዲሁም በድጋሚ በ1984 ከእነ አረጋሀኝ ጋር ተጨማሪ የኮሌክሽን አልበም ሰርቷል። የዛሬው ተመስጋኝ ባለታሪካችን አንጋፋው ተወዳጁ ጨዋታ አዋቂው የዜማ እና ግጥም ደራሲ ድምፃዊ ነዋይ ደበበ🙌🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ ለዛሬ በቁ.57 የሚጣል ዘፈን የሌላቸው አልበሞች ዳሰሳችን ይዤላቹ የመጣሁት ይህ 10 እንከን አልባ ሙዚቃዋችን በ90ዎቹ አጋማሽ የወጣሁ ይህ እንደ "ሀገሬን አልረሳም" አልበሙ ሁሉ ሙሉ በሙሉ በታላቁ አበጋዙ የተበጀው የነዋይ ደበበ "አሜን" አልበም ነው👌 ታዲያ ነዋይ በውብ ድምፁ የሚታወቀውን ያህል በተጨማሪ ጎበዝ የግጥምና ዜማ ደራሲ መሆኑ እሙኑ ነው ልክ እንደዚህ እና ሌሎች አልበሞቹ ሙዚቃዎቹን እራሱ ይደርሳል ከርሱም አልፎ ተርፎ ለታላላቅ ድምፃዊያን ጭምርም ግጥምና ዜማ ሰጥቷል። ለጋሽ ጥላሁን ከተወዳጇ አለምፀሀይ ወዳጆ ጋር በመሆን "ወገን አለኝ" ፣ ለፀሃዬ ዮሀንስ "አባይ ነው አሉኝ ቤቷን" እና "ቅያሜ እንኳን ቢኖር" ፣ ለሀመልማል አባተ "የትዳሬ ማገር" ፣ " አቤት አቤት" ካሴት ላይ 8 ዘፈኖች ፣ የፋንትሽን " ፍቅር ተዋጣልኝ አንተ ልጅ ወድጄህ ነው " ን ጨምሮ ለአስቴር ከበደ ከ"ፍቅር እንዳሰቡት እና "አማሌሌ" ውጪ ለሙሉ አልበሟ ፣ ለደረጄ ደገፉ የሠርግ ዜማ "አየሁት ምኞቴን" እና "አትደርቢብብኝ" ፣ ትዕግስት ይልማ (ሸጋ ልጅ ጉብል ባይኔን) ጨምሮ በርካታ ስራዎቿን ። ለመስፍን በቀለ ( ጨከነ ልቤ) ለሂቦንጎ ( የፍቅር ጥሪ ) ለሰለሞን ተካ (ልቤ መዋተቱ " አራዳ) ለአስናቀ ገብረየስ ( የክፉ ቀን ደራሽ ) እና ሌሎችም ለኩኩ ሰብስቤ፣ ለኤልያስ ተባበል ፣ለመስፍን አበበ እና ለሌሎች ብዙ ድምፃዊያን ግጥምና ዜማ በመስጠት ችሎታውን አሳይቷል ነዋይ ከዚህም በተጨማሪ ማህበራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በሙያው አስተዋፅኦ ያደረገ ሲሆን ለ1977ቱ ድርቅ እርዳታ ለማሰባሰብ በተሰራ "የብሩህ ተስፋ እሸት" ኮሌክሽን እንዲሁም ለHIV በተሰራው "እንኖራለን ገና" አልበም ላይ "እንኖራለን ገና" የሚለውን ሙዚቃ ግጥምና ዜማ በመስራት እና በድምፅ በመጫወት ተሳትፎ አድርጓል🙏 📌በመጨረሻም እስቲ ጥቂት ስለ እጀ... ወርቁ አበጋዙ ጥቂት ብዬ ላብቃ እሱ የተወዳጁን ድምፃዊ የሙሉቀን መለሰን የቆዩ ዘፈኖች የነበረ ድምፅን ብቻ ወስዶ ለዛው ሳይለቅ ሙዚቃውን ብቻ አቀናብሮ ለአድማጭ ያቀረበ ጊዜ የብዙዎቻችን ደስታ ልዩ ነበር !! የቴዲ ታደሰ " ዝምታ " አልበም ላይም ቅንብሩ አስደምሞናል! እያንዳንዳችን በምንወዳቸው ዘፋኞች ስራዎች ውስጥ የሱ ወርቅ ጣቶች ልዩ ቅመም ሆነው ስናዳምጣቸው እርካታን ያላብሱናል ! ለምሳሌ እንደኔ ስሜት ነዋይ ከሮሀ ባንድ ወዲህ ያወጣቸውን "ሀገሬን አልረሳምና " እና " አሜንን " አልበሞች ላይ የዜማዎቹን ስሜቶች ቅንብሮቹ ላይም ስላማገኘው በልዩ ፍቅር ነው የማጣጥማቸው ! የአሜን ዘፈን ኢንትሮው ላይ ሙዚቃው ውስጥ " አሜን " የሚለውን ቃል ከነዋይ ድምፅ በፊት አናገኘዋለው ! " አልዋሽም " ዘፈን ላይ የሙዚቃው ፍሰት ከዜማው ውበት ጋር በመንፈስ ይዞ ጭልጥ የሚያደርግ ነው!! "አልበለጥም " ገና ሙዚቃው ሲጀምር የመድረክ ላይ ስሜቱ ሸነጥ ያደርጋል !! ብቻ በአጭሩ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ገፀ በረከት የሆነው አበጋዙ ሁሌም እንደምላቹ ከምስጋናም በላይ ይገባዋል እያልኩኝ ለዛሬወ አበቃሁ🙌🙏 🗣ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 musictube 🇪🇹 #fyp #ነዋይደበበ #አሜንአልበም #ethiopianmusic #musictube369

About