@daer033: #ከመቅደስ አገልጋይነት እስከ #ናሳ ተመራማሪነት የደረሰው ተተኪ ያልተገኘለት #ካፋ ያፈራችው #ዲያቆን_ኢንጅነር_ቅጣው_እጅጉ ... *** የዛሬ 18 ዓመት ገደማ ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ፖሊ ካምፓስ ተመድቤ ስገባ ዩኒቨርስቲው ቅጣው ብሎክ /Block D/ የሚባል ህንፃ ላይ ዶርም ሰጠን። "ቅጣው" የሚል ስምን ለመጀመርያ ጊዜ የሰማውት ያኔ ነው። ይህ ስም ሲነር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለፉገራ ያወጡት የግቢ መግባቢያ ስያሜ እንጅ የአንድ ምትክ አልባ ሰው ስም እንደሆነ የገባኝ ዘግይቶ ነበር። ስለ እዚህ ምትክ አልባ ሰው ትንሸ መረጃ ካገኘው በኋላ ይበልጥ አብዝቼ ማወቅ ፈልጌ የሄድኩበት ርቀት በስተመጨረሻው ለባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ማኅበረሰብ በሚታተመው ዓመታዊ መጽሔት በሆነው " ግዮን " ቅጽ 4 ላይ ግለ ታሪኩን አዘጋጅ በመሆን ደመደምኩኝ። ዲያቆን ኢንጅነር ቅጣው እጅጉ እኛ ባረፍንበት ብሎክ ላይ በመመደብ የመጀመርያ የምህንድስና ትምህርቱን ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመቀበሉ ምክንያት ብሎኩ በእርሱ ስም እንደተሰየም /Informally /በግድምዳሜ አወቅን። ደቡባዊቷ ካፋ ከቡናዋ እኩሌታ ቅጣው በሚል ስም ትታወቃለች። ከቡናዋ በላይ ቅጣው በሚል ስምም ትኮራለች። ይገባታል። ይህ ምትክ አልባ ምሁር ..." አአትብ ገጽየ " ብሎ ፊደል ከመቁጠር ጀምሮ Aerospace Engineering እና propulsion system science ላይ አዲስ ነገር እስከ መፍጠር ድረስ የደረሰ ታምራዊ ሰው ነበር። propulsion systems ሲባል ቀለል ያለ ሳይንስ እንዳይመስልህ ወዳጄ። ፕሌኖች፣ሮኬቶች፣መኪናዎች ወይም ማንኛውም በኃይል ግፊት ያሚሰሩ ተንቀሳቃሾች ወደ ፊት እንዲገፉ እና ፍጥነታቸውን እንዲጨምር የሚያደርግ በኒውተን 3ኛ ህግ ላይ የተመሰረተ ምድር ቀያሪ ውስብስብ ቴክኖሎጂ ነው። የቅጣው እጅጉ propulsion systems ቴክኖሎጂ ማሻሻያዎችን ዛሬ ናሳ በሚያመጥቃቸው ሮኬቶች እና የቦይንግ ካንፓኒ በሚጠቀማቸው የአውሮፕላን ኢንጅኖች ላይ በሥራ ላይ ውለው ይገኛል። ይህ ሰው Aerospace Engineering ላይ የፈጠረውን የላቀ ተጽዕኖ የምታውቀው ናሳ ከሞቱ በኋላ ለጥቂት ምሁራን የሚሰጠውን posthumously professional recognition ስያሜ ያገኘ ታላቅ መሃንዲስ ነው። ስለቅጣው እልፍ ነገር ሌላ ጊዜ እንጽፋለን። ነገር ግን ይህ ሰው በናሳ ብቻ ሳይሆን በመቅደስ ህይወቱም ዲያቆን የነበረ አገልጋይ ነው። ቤተ ክርስቲያን በጎ ተጽእኖ በዓለም ላይ ያሳድሩ ዘንድ ኮትኩታ ከሰጠቻቸው ውድ ልጇ መካከል አንዱ እርሱ ነው። እግዚአብሔር ነፍሱን በሠላም ያሳርፍ!!! @fb ከታሪክ ማህደር #ethiopian_tik_tok 💚💛❤️
daer33
Region: ET
Friday 06 November 2026 12:45:44 GMT
Music
Download
Comments
Abera_Bek :
ሳይንቲስት ቅጣዉ እጅጉ አልሞትም ምክንያቱም ሰራዉ ህያዉ ነዉና ለቤተሰቦቹ ጤናዉን ና እድሜ ይስጣቸዉ በአካል ለመገናኝትና ለመተያየት ያብቃን:!!!
2026-11-06 19:33:53
3
kiberet Amarech 21 :
አቤት አንተ ብትኖር ኖሮ ሀገሬ የት በደረሰች ???
2026-11-08 05:34:03
2
user9741839720286 :
ሰው እደገና በህይወት ቢኖር እግዚአብሔር ይህንን ትሁት ሰው አንግሳ ቢያኖረውሕ
2026-11-06 21:05:42
2
adu 👗💚💛❤❤❤❤❤❤❤❤ :
ቅጣውን ግን ማን ገደለው? ሁሌ ጥዬቄ ይሆንብኛል ጀግና ሰው አሳጡን🥺🥺🥺🥺🥺
2026-11-07 06:11:30
2
Abebaw :
ታላቁ የጥበብ ሰው
2026-11-09 15:45:22
1
mule :
ተተኪ።።።።።።።።።።።።።አለ ማን ያውጣው።
2026-11-07 10:33:57
1
snaatak :
ይሕን መልካም ነገር ያብዛልን
2026-11-08 03:20:43
1
temesgenegetayneg :
Blessed,Amazing, Brilliant, generous, hero, and Honest Ethiopiawe .we miss you May LORD JESUS rest your Soul in Heaven🙏🙏🙏. we love you❤️❤️❤️
2026-11-07 20:15:04
1
Daniel1919 :
19 19 19
2026-11-06 19:00:45
2
tariqwa :
ሙቶአል??
2026-11-07 17:41:52
1
user1011720748069 :
wow
2026-11-07 16:22:41
1
BIR/NEG :
ዲገሜ ተወለድ እስኪ ሳይንትስተችን።
2026-11-07 05:54:14
1
Tersa :
ሀውሎት 4ኪሎ ይቁምለት ባይ ነኝ
2026-11-08 14:02:58
0
Alxo assayehagn :
❤️❤️❤️
2026-11-07 17:27:43
1
Mesfin Afedaraw :
❤️❤️❤️
2026-11-06 17:33:58
1
genetamare51 :
😳😳😳
2026-11-07 03:47:18
1
To see more videos from user @daer033, please go to the Tikwm
homepage.