@eyosiase17: ቤተክርስቲያን               ክፍል-8 2. አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ በሁለተኛ ደረጃም ከአማኞች አንድ ወይም ሁለት ከራሱ ጋር በመውሰድ ዳግመኛ ተበዳዩ ወደበዳዩ በመሄድ አብረውት ካሉት ጋር በዳዩ እንደበደለ ለማስረዳት በመጀመሪያ እንዳደረገው በጸጋ ጥረት እንዲደረግ ጌታ አስተምሮናል፡፡ የዚህ ጥረት ዓላማም እንደመጀመሪያው ሁሉ ወንድምን ገንዘብ ለማድረግ ነው፡፡ ሆኖም በዚህም ባይሳካ ወደ ሦስተኛው እርምጃ እንድንገባ ጌታ ፈቅዶልናል፤ ይህም ለቤተክርስቲያን መንገር ነው፡፡ 3. ለቤተክርስቲያን ንገራት   የቤተክርስቲያን ጥረትም እንደቀደሙት ሁሉ በጸጋ ነገሮችን ወደነበሩበት የፍቅርና የወንድማማችነት መንፈስ መመለስን ዓላማው ያደረገ ሊሆን ይገባዋል፤ በተጨማሪም የቤተክርስቲያንን ወቀሳ ለመስማት የሚመጣው በደለኛ ወንድም በግል የተወቀሰና ወቀሳውን ያልሰማ ከመሆኑም ባሻገር በሁለት ወይም በሦስት ወንድሞችም ሊመለስ አለመቻሉ በደለኛነቱን እርግጠኛ ያደርገዋልና ቤተክርስቲያን የመጨረሻውን ወቀሳ ለመስጠት ሕጋዊ መሠረት ይኖራታል ማለት ነው፡፡ እንደሚታወቀው ሁሉ የመጨረሻ ምክርና ተግሣጽ የሚሰጠውና ይህንንም ተግሣጽ በደለኛው ካልሰማ የመጨረሻውን ውሳኔ መስጠት የሚችለው «ከፍተኛ ባለ ሥልጣን» የሆነ አካል ነው፤ ጌታችንም አካሉ የምትሆን ቤተክርስቲያንን ወቀሳ እንድትሰጥና አስፈላጊውን የመጨረሻ ውሳኔ እንድትወስን መመሪያ ሲሰጥ ቤተክርስቲያንን በምድር ላይ ከፍተኛ ባለሥልጣን ማድረጉን እንረዳለን፡፡ ይህም ወቀሳ ምክር አዘል ተግሣጽ እንደሆነ መረዳት አያዳግትም፡፡ ቤተክርስቲያንም በደለኛውን ለመውቀስ የሚያስችላት የእግዚአብሔር መንፈስና የእግዚአብሔር ቃል አላት፤ ዋናው ዓላማም በደለኛው የእግዚአብሔር ቃልና የእግዚአብሔር መንፈስ የሚለውን ሰምቶ በሁሉ እንዲወቀስና እንዲመከር በደለኝነቱን እንዲያምን በንስሐም ወደጌታ እንዲመለስ ማድረግ ነው እንጂ በደለኛውን መበቀል አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ በግልና በጋራ ተወቅሶ ወደ ቤተክርስቲያን የመጣውና ቤተክርስቲያንም የወቀሰችው ሰው የቤተክርስቲያንን መንፈሳዊ ወቀሳ  ባይሰማስ? 4. እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ   ለዚህ የተሰጠው የጌታ መመሪያም፣ «ቤተክርስቲያንን ባይሰማት እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ» የሚል ነው፤ ተበዳዩ አማኝ ከዚህ አልፎ እንዲሄድ አልተፈቀደለትም፤ ንስሐ ሊገባ ባልቻለው በዚያ ሰው ላይ ቤተክርስቲያን በምትወስደው እርምጃ ላይም ግፊት ማድረግ አይኖርበትም፤ ወዳላመኑ ሰዎች ዘንድም ሄዶ «ንስሐ ባልገባው» በደለኛ ላይም ክስ ይመሥርት አልተባለም፤ ሆኖም እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ እንዲቆጥረውና እንዲተወዉ ታዟል፡፡ ቤተክርስቲያን ግን በአማኞች መካከል የሚነሱ በደሎችን እንድትዳኝ ሥልጣን የተሰጣት በመሆኗ በመቀጠል ስለምትወስደው እርምጃ ጌታ ሲናገር «በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል» ሲል ተናገረ፤ ይህም ቤተክርስቲያን በአማኞች መካከል የሚነሡ ችግሮችን በበላይነት የመመልከት ሥልጣን እንዳላት የሚያመለክት ነው፤ ከዚህ አኳያም ማሰሩ በትክክል በዳዩን ሰው ከጉባኤ እንዲገለል ማድረግ ሲሆን መፍታቱ ደግሞ በተጸጸተ ጊዜ በዳዩን ሰው ይቅር ብሎ ወደ ኅብረት መቀበል ማለት ነው፡፡ ይህን የማድረግ ሥልጣንም በሥራ ላይ የሚውለው ሁለት ወይም ሦስት እንኳን በሚሆኑ አማኞች መካከል በሚገኘው ጌታ ኢየሱስ ነው፤ በምድር ላይ ንስሐ አንገባም በሚሉትና ልባቸውን በሚያደነድኑ፣ ወንድሞቻቸውንም በሚበድሉ በደለኞች ላይ ቤተክርስቲያን በምድር የምታስተላልፈው ውሳኔም በሰማይ በጌታ ዘንድ እውቅና አለው፤ በዚህ ዓይነት ቤተክርስቲያን በዳዮችን ከመካከሏ እንድታርቅ ሥልጣን ተሰጥቶአታል፡፡ ሐዋርያው ለቆሮንቶስ ሰዎች በቀዳሚ መልእክቱ በምዕራፍ 6 የተናገረለት ጉድለትም ቤተክርስቲያን ይህን በአማኞች መካከል የሚነሱ የግል በደሎችን በተሰጣት ሥልጣን መዳኘት አለመቻሏ እንደነበር ግልጥ ነው፡፡ ስለዚህም ሐዋርያው የሚከተለውን ለማለት ተገዶ ነበር፤ «ከእናንተ አንዱ ከባልንጀራው ሙግት ቢኖረው በቅዱሳን ፊት በመፋረድ ፋንታ በዓመፀኞች ፊት ሊፋረድ ይደፍራልን? ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን? በዓለምስ ላይ ብትፈርዱ ከሁሉ ይልቅ ትንሽ ስለሚሆን ነገር ልትፈርዱ አትበቁምን? የትዳር ጉዳይ ይቅርና በመላእክት እንኳ እንድንፈርድ አታውቁምን? እንግዲህ ስለ ትዳር ጉዳይ የፍርድ ቤት ቢያስፈልጋችሁ በቤተክርስቲያን የተናቁትን ሰዎች ፈራጆች አድርጋችሁ ታስቀምጣላችሁን? አሳፍራችሁ ዘንድ ይህን እላለሁ፡፡ እንደዚህ ነውን? በወንድሞች መካከል ሽማግሌ ሊሆን የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው በእናንተ ዘንድ አይገኝምን? ነገር ግን ወንድም ወንድሙን ይከሳል ይህም በማያምኑ ፊት ይደረጋልን? እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በእርስ ሙግት እንዳለባችሁ በእናንተ ጉድለት ነው፡፡ ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን? ነገር ግን እናንተ ትበድላላችሁ ታታልሉማላችሁ ያውም ወንድሞቻችሁን» (ቊ.1-8)፡፡ የቆሮንቶስን አማኞች ጉድለት በመከተል የገዛ ወንድምን ወደማያምኑ ፈራጆች መጎተትና በዚህም የአማኞችን የከበረ ማንነት በዓለም ፊት የማስነወሩ ተግባር ሊወገድ የሚችለውም ቤተክርስቲያን ይህን ሥልጣን ስትጠቀም ነው፤ ቤተክርስቲያንም ከጌታ ያገኘችውን ውበት ጠብቃ መኖር የምትችለው በዚህ ሥልጣን ተጠቅማ ክፉዎችን ከመካከሏ ማራቅ ስትችል ነው፡፡ ምንም እንኳን ከአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከዚህ ዘመን ድረስ ሰይጣን በአማኞች መካከል መለያየትን በመፍጠሩ ምክንያት በአንድ ስፍራ አማኞች እንደ ጌታ ፈቃድ ከመካከላቸው ያገለሉት በደለኛ በሌላው ስፍራ ባሉ አማኞች ነን ባዮች እንደ ሰማዕት ተቈጥሮ ተቀባይነት የሚያገኝበት ሁኔታ በእጅጉ የሚታይ ቢሆንም አሁንም ይህ ሥልጣን ሁለት ወይም ሦስት ሆነው በጌታ ስም በሚሰበሰቡ እውነተኛ አማኞች ዘንድ መኖሩ የሚያጠራጥር አይደለምና እውነተኛ አማኞች ይህን ሥልጣን ተጠቅመው ክፉን ከመካከላቸው እንዲያርቁ አለመግባባቶቻቸውንም ወደማያምኑት ከመውሰድ እንዲታቀቡ፣ በነውር የተገለሉትንም በደፈናው ወደኅብረታቸው ከመቀበልም እንዲጠበቁ ይመከራሉ፡፡   አማኞች ይህን ጌታ የሰጣቸውን ሥልጣን ተጠቅመው አንድን በደለኛ ከመካከላቸው ቢያስወግዱና ቆይቶ ኃጢአቱ የተያዘበት ሰውም ልቡ ተነክቶ ወደ ጌታ ኢየሱስና ወደ ቤተክርስቲያን በንስሐ ቢመለስ አማኞች ኃጢአቱ እንዲሰረይለት በመስማማት የሚጸልዩለት ጸሎት በጌታ ዘንድ ፍጹም ተሰሚነት አለውና ጌታም ይቅር ይለዋል፡፡ ያ ሰው አልመለስም በማለት ቢቀጥል ግን ይህ በደሉ በጌታ ዘንድ እንደተያዘበት ይኖራል፤ ይህም ማለት የጌታ የሆኑት በምድር ተሰብስበው እንደ ጌታ ልብ የሚወስኑት ውሳኔ በጌታ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሆኑን እንድናውቅ ያስረዳናል፤ ቤተክርስቲያንም በዚህ ዓይነት የማሰርና የመፍታት ሥልጣኗን ትተገብራለች፡፡ ይቀጥላል... ምንጭ:- www.ewnetone.com ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

𝐸𝑦𝑜𝑠𝑖𝑎𝑠𝑒 ❤️🫰🫆
𝐸𝑦𝑜𝑠𝑖𝑎𝑠𝑒 ❤️🫰🫆
Open In TikTok:
Region: ZA
Saturday 07 November 2026 04:21:55 GMT
26275
2365
102
272

Music

Download

Comments

samrawit.tamire0
kiya🦋🦋🦋ነኝ ተተርው :
amnii
2026-11-11 17:34:55
0
user6366687159933
dani fafi :
Ameni
2026-11-12 10:41:55
0
baraka40369
beki man :
🙏🙏🙏🙏
2026-11-15 09:08:10
0
sintu465
sintu465 :
አሜን አሜን አሜን እግዚአብሔር ይመስገን
2026-11-09 04:37:22
1
stagaye.adamo
Stagaye adamo :
Amen 🙏❤️❤️❤️❤️❤️
2026-11-09 19:20:39
1
zemede30
zemede :
2026-11-12 07:28:00
0
detamo36510
welcome 😘😘 :
amene
2026-11-14 09:24:56
0
.meqid
꧁❵❥𝐌𝕖𝕜𝕚𝕕🧚‍♀️🤍 :
አሜን
2026-11-11 20:13:03
0
mihretualemayewu
143 :
Amen
2026-11-12 18:18:24
0
makidas2
makidas❤️💃 :
amen
2026-11-12 11:49:29
0
user5340704497906
Takile 1995 :
amen
2026-11-13 12:11:51
0
pastere.takalagn
ሸሎም :
ame
2026-11-13 17:52:54
0
betibekele15
𝐛𝐞𝐭𝐢 𝐛𝐞𝐤𝐞𝐥𝐞🦋🌸 :
amen 🙏
2026-11-12 21:59:37
0
yenee250
꧁ ➳yene💞:𝐄ዬ꧁ ➳😘 :
2026-11-11 11:57:10
0
whattiktok.comtashaesiy2
🏥TESHE Jesus is king of King :
🙏
2026-11-14 11:47:52
0
nananana4482
Nana :
amen 🙏
2026-11-11 00:38:44
0
zabo022
zado :
ameni
2026-11-10 18:21:05
0
shi.ta04
Shi Ta :
Ameeen🙏
2026-11-11 07:33:17
0
mitku06563
ganet :
amen
2026-11-11 07:10:49
0
alexanderkabada
አል አልሽ :
2026-11-15 05:53:49
0
nesaneti27
nesaneti :
2026-11-10 19:41:36
0
firee6381
𝐟𝐢𝐫𝐞..m̤y̤..🫰🎵. 🙋‍♀️ :
አሜንንን አሜንንን 🙏
2026-11-07 06:23:23
0
To see more videos from user @eyosiase17, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About