@y4u.a:

nguyên.b❤️..
nguyên.b❤️..
Open In TikTok:
Region: VN
Saturday 07 November 2026 11:04:29 GMT
26
10
0
4

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @y4u.a, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

...የቀጠለ  በክርስትና ብስለት ማደግ እንዴት ነው በመንፈስ እየበሰልን የምናድገው? 2. መንፈሳዊ ምግብ  •አንድ ሕጻን ያለበቂ ምግብ ማደግ አይችልም። እንዲሁ ያለ እግዚአብሔር ቃል መንፈሳዊ ሕይወታችን ሊያድግ አይችልም።  •ማቴ. 4፡4
...የቀጠለ በክርስትና ብስለት ማደግ እንዴት ነው በመንፈስ እየበሰልን የምናድገው? 2. መንፈሳዊ ምግብ •አንድ ሕጻን ያለበቂ ምግብ ማደግ አይችልም። እንዲሁ ያለ እግዚአብሔር ቃል መንፈሳዊ ሕይወታችን ሊያድግ አይችልም። •ማቴ. 4፡4 "ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም…" •1ጴጥ. 2፡2-3 "…ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።" • መዝ. 1፡1-2 "ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል።" •2ጢሞ. 3፡16-17 "የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት  በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።" •ኤፌ. 6፡17 "የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።" • ቆላ. 3፡16 "የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ።" •ይህን ምግብ በበቂ ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት እና በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ መገኘት ያስፈልጋል:: ለእግዚአብሔር ቃል ያለህን አፕታይት/ፍላጎት ለመለካት የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ •በዚህ ሳምንት ምን ያህሉን ሰአት ቲቪ በማየት አጠፋህ? •ምን ያህሉን ጊዜ አዝናኝ ጋዜጣዎችን ወይም መጽሔቶችን በማንበብ አጠፋህ? •ምን ያህሉን ጊዜ ሶሻል ሚዲያዎችን በመጠቀም፣ ከሰው ጋር የባጥ የቆጡን ስታወራ አሳለፍክ? •ምን ያህል ሰአት መጽሐፍ ቅዱስህን ለማጥናት ተጠቀምክ? 3. ልምምድ •አትሌቶችና ልምምድ ያለውን ትልቅ ዋጋ ጠንቅቀው ያውቃሉ። •ክህሎትን ለማዳበር ያልተቁዋረጠ ልምምድ ማድረግ የግድ ነው። ምሳሌ፣ ባስኬት ቦል •ሕጻናት ለመቆም አበክረው መለማመድ ይኖርባቸዋል። •ልምምድ ለመንፈሳዊ እደገት ወሳኝ ነው። •1ጢሞ. 4፡7-8 "ነገር ግን ለዚህ ዓለም ከሚመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ  ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ። ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።" • ዕብ. 5፡14 (አ.መ.ት.) "ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ከክፉውን ለመለየት ራሳቸውን ላስለመዱ፣ ለበሰሉ ሰዎች ነው።" • ለማስተማር፣ ለመዘመር፣ መጽሐፍ ቅዱስን በአግባቡ ለመረዳት፣ ለመጸለይ፣ ወዘተ ልምምድ ይጠይቃል። 4. ጊዜ እና ትዕግስት •እድገት ጊዜን ይጠይቃል፣ ሂደት ነውና። የሂደት ጉዞ ደግሞ ያለ ትዕግስት የሚሞከር ጉዞ አይደለም:: •ግብህ ላይ በአንድ ለሊት ለመድረስ አትመኝ። ሕጻናት በአንድ ለሊት ሙሉ ሰው አይሆኑምና። ግብ የብዙ ልምምድ እና ትዕግስት ድምር ውጤት ነው። •ያዕ. 1፡4 (አ.መ.ት.) "ምንም የማይጎድላችሁ ፍጹማንና ምሉዓን እንድትሆኑ ትዕግሥት ሥራውን  ይፈጽም።" • ዕብ. 10፡36 "የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና።" • መክ. 3፡1 "ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።" • መክ. 3፡11 "ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው …።" ይቀጥላል... ምንጭ:- tsegaewnet.files.wordpress.com ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures#ኢየሱስ_ያድናል_ይታደግማል።

About