@dromer2025: ☑️የወር አበባ ቀን መቁጠሪያ ዘዴ ✍️ የወር አበባ ዑደትን በመመዝገብ ሴቷ እርግዝና ልትፀንስባቸው የምትችላቸውን ቀናት በግምት ለመለየት የሚጠቅም ተፈጥሯዊ የቤተሰብ ምጣኔ ዘዴ ነው። ➊ባህላዊው የቀን ቆጠራ ዘዴ ✍️ በተመዘገቡት አጭርና ረጅም የወር አበባ ዑደቶች መሠረት የመፀነስ እድል ያላቸውን ቀናት ለመወሰን ይጠቀማል። ✍️የመጀመሪያውን የመፀነስ እድል ያለበት ቀን ለማግኘት ከአጭሩ የወር አበባ ዑደት 18 ይቀነሳል። ✍️የመጨረሻውን የመፀነስ እድል ያለበት ቀን ለማግኘት ከረጅሙ የወር አበባ ዑደት 11 ይቀነሳል። ✍️ባልና ሚስቱ በተሰላው የመፀነስ እድል ባለበት ጊዜ ያለ መከላከያ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከማድረግ መቆጠብ አለባቸው። ➋የመደበኛ ቀናት ዘዴ ✍️ የወር አበባ ዑደታቸው በቋሚነት ከ26 እስከ 32 ቀናት ለሆነ ሴቶች የሚመከር ቀለል ያለ የቀን ቆጠራ ዘዴ ነው። ✍️በዚህ ዘዴ ከ8ኛው እስከ 19ኛው ቀን ድረስ ያሉት ቀናት የመፀነስ እድል ያላቸው ቀናት ተብለው ይቆጠራሉ። ✍️ምንም እንኳን ይህ የመከላከያ ዘዴ የሚጠቅመው ለልተዛባ የወር ኣበባ ያላት እናት ሲሆን ፣100 እናቶች ለኣመት ቢጠቀሙት 13 እናቶች ላይ እርግዝና የመፈጠር እድል ኣለው ። ✍️ስለዚ በተለያየ ምክንያት ባህል ሃይማኖት ፣በሽታ ዘመናዊ መከላከያ መጠቀም ያልቻሉ ፣እርግዝና እንዳይከሰት በጥብቅ ያልተከለከሉ እናቶች የወር ኣበባዎ 26 -32 ባለው ግዜ የሚመጣ ከሆነ 8ኛ እስከ 19ኛ ያለ መከላከያ ግንኝነት ባለመፈፀም እርግዝና መከላከል ይችላሉ ። #fyp #tiktok #ማህፀንናፅንስህክምና #dromer #gynecologist
Dr Omer.M Gynecologist &OB
Region: ET
Sunday 08 November 2026 06:51:02 GMT
Music
Download
Comments
Tilsh :
ovulation date +/- 5 is pregnancy period
2026-11-12 12:35:58
0
tilsh abe :
አልገባኝም መጀመሪያ የወር አበባ ማለት ዝግጁ የሆነ እንቁላል የወንድ ዘር ሲያጣ ቡኖ ፈርሶ ከማህጸን በ7ቱ ቀኖች ተወገደ ከዛ በ8ኛው ቀን ዝግጁ እንቁላል የታለና ነው ጽንስ የሚፈጠር
2026-11-12 11:21:32
0
A@2018 :
ጥቅምት 16 የታየስ
2026-11-12 03:31:34
1
Haymanot Haymi :
ደኩተር የኔዉ 1የመጣ
2026-11-11 08:43:00
0
@haymi የኪዳናምህረት ልጅ :
ዶክተር እባክህን ጥቅምት 29 ነው የመጣው እና እባክህ አሰረዳኚ
2026-11-09 22:20:25
0
Exodus :
be 23 kayechis ?
2026-11-10 04:26:31
0
temesgen :
🥰🥰🥰
2026-11-12 14:24:15
0
T. Y :
👍
2026-11-12 02:56:27
0
ቢኒያም :
😩😩😩
2026-11-12 19:00:04
0
To see more videos from user @dromer2025, please go to the Tikwm
homepage.