@melakuberhanu82: በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ተረጋግቶ መኖር የላቀ ጥበብን እና የስሜት ልዕልናን ይጠይቃል። የተረጋጋ ሰው ለመሆን ግን ምስጢሩ ከባድ አይደለም። ዴዜዴራታ "በዚህች ጫጫታና ሁካታ በበዛባት ዓለም ለነፍስህ ሰላምን አትንፈጋት" ይላል። ተረጋጋ!! አብዛኛው ሰዉ "ተረጋግቶ መኖር" ማለት ሰላማዊ ሕይወት መምራት፣ አስቸጋሪ ሰዎችን ማስወገድ ወይም ስሜትን መቆጣጠር መቻል ይመስለዋል ። ግን አይደለም !! እውነተኛ መረጋጋት የሚገነባው በዙሪያህ ያሉ ነገሮች ሁሉ ከስሜትህ ጋር እንድትታገል አንዳንዴም ከቁጥጥር ውጪ እንድትሆን በቂ ምክንያት በሚሰጡህ ጊዜ ነው። መረጋጋት ማለት ክብርን በማጣት ፣ በተስፋ መቁረጥ፣ ባለመስማማት እና በከፍተኛ ጫና ውስጥ ሆነህ፣ ሁኔታው አንተ በተቃራኒው መልስ እንድትሰጥ ሲወስንብህ አንተ ግን ይህንን ሳትፈቅድ ቀጥ ብለህ የመቆም ችሎታ ማዳበር ማለት ነው። አንዴ ይህንን ጥበብ ካዳበርክ በኋላ፣ ቀደም ሲል ሰላምህን ይነሱህ የነበሩ ነገሮች ሁሉ በአንተ ላይ ያላቸው ኃይል ያከትማል።እነዚህን ከታች የፃፍኳቸውን ነገሮች ተለማመዳቸው ፣ ያኔ ከራስህም ከሰውም ሳትጋጭ ራስህን ሆነህ ትኖራለህ። ለነፍስህም ሰላም ትሰጣታለህ። * በፍጹም በስሜትህ ፍጥነት አትስራ፣ ፀፀትን ለማስቀረት ለሚገጥምህ ምንም ነገር ምላሽ ከመስጠትህ በፊት ጥቂት ሰከንዶች ታገስ። * ልትቆጣጠረው የማትችለውን ነገር ለመቆጣጠር መሞከርህን አቁም፣ የሰዎችን ባህሪ እና የተከሰቱ ነገሮችን ለመቀየር አትልፋ፤ ትኩረትህ በራስህ ምርጫ ላይ ብቻ ይሁን። * የሌላ ሰው ባህሪ ያንተን ባህሪ እንዲወስን በፍጹም አትፍቀድ፣ የሰዎች መጥፎ ባህሪ የራስህን ስነ-ምግባርና መረጋጋት እንዳያሳጣህ ተጠንቀቅ ። * ከዝምታ ጋር መላመድን ተማር፣ ሁሉንም ክርክር ለማሸነፍ ከመልፋት ይልቅ አላስፈላጊ ሁከትን በዝምታ ማለፍን ምረጥ። * እያንዳንዱን ችግር ምላሽ እንደሚፈልግ እንደ አስቸኳይ አደጋ መመልከትህን አቁም፣ አእምሮህ እንዳይዝል ጊዜያዊ ምቾት ማጣትን ከእውነተኛ ችግር ለይተህ እይ። * ስሜትህ በገነፈለበት ወቅት በፍጹም ከባድ ውሳኔ አትወስን፣ ጊዜያዊ ስሜት ዘላቂ ጉዳት እንዳያደርስ ማንኛውንም ትልቅ ውሳኔ በሰከነ አእምሮ ወስን። * ሰዎች አንዳንዴ እንደማይረዱህ ተቀበል፣ አንተን አለመረዳት መብታቸው ነው። የሰዎችን አስተያየት መቀየር ስለማትችል ሰላምህን በሰዎች መረዳት ላይ አታንጠልጥለው ። * አእምሮህ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እንዲጠብቅ አሰልጥነው፣ ችግር ሲገጥምህ ከማማረር ይልቅ መፍትሄ በሚያመጣው ቀጣይ እርምጃህ ላይ አተኩር። * በእቅድህ ላይ ብቻ የማይመሰረት ህይወት ገንባ፣ ውጫዊ ሁኔታዎች ስለሚቀያየሩ ደስታህን በውስጣዊ መርሆዎችህ ላይ ብቻ መስርት። * ከነዚህ መካከል የሚጠቅምህን ውሰድና ተረጋግተህ ኑር!! (የቱን ትመርጣለህ? )
melaku berhanu
Region: ET
Sunday 08 November 2026 12:34:14 GMT
Music
Download
Comments
mesfin :
No comment
2026-11-24 08:20:30
0
Melaku :
መልካም ስብእና ሲኖር እይታው ለሁሉም ይደርሳል እናመሰግናለን
2026-11-14 09:00:27
2
Yohannes Kebede :
ለዚህ ነው ከመቁረጥህ በፊት 10 ጊዜ ለካ የሚባለው መረጋጋት ከስህተት ከፀፀት ሰለሚያድነ ነው እናመሰግናለን ።
2026-11-18 16:59:59
1
Rahela Akalu ✍️ :
እራስን እንደመግዛት እንደማሸነፍ ያለ ምን ትልቅ ስኬት አለ ብለህ ነው ይህ መረጋጋትን ይለግሳል ይመስለኛለል እናመሠግናለን መሌ
2026-11-09 12:18:18
1
user1793601152209 :
ጥሩ እና ትክክለኛ ነገር እናመሰግናለን
2026-11-10 03:20:02
1
user7608557933841 :
ሁሌም አክባሪህ ነኝ።
እምታነሳቸውን ገንቢ ሀሳቦች በአንክሮ እከታተላለሁ ።
አመሰግናለሁ !!!
2026-11-12 09:02:05
0
Eliana Bahiru Hewi :
ምናለ ሁሉም እንዳንተ መልካም ስብእና በተላበስን
2026-11-08 13:57:11
1
AbebMa :
ምኑ ይመረጣል!!!!! አምላኬ ሆይ እርዳኝ
2026-11-10 04:17:42
1
Yosef Tsegaye :
ፈጣሪ ረጅም ዕድሜን ከጤና ጋር ይስጥህ! ይህ ፅሁፍ ጥልቅ አስተሳሰብ ካላቸው የሚመነጭ ነው በርታ🙏🙏🙏
2026-11-10 16:55:39
0
Lulsegde አቡሼ :
እውነት ረጋበል
2026-11-14 16:38:27
0
bini man :
Amesegnalewu
2026-11-18 11:30:12
0
@abrham :
ይመችህ
2026-11-21 12:44:06
0
Arsenal Noleta :
Hi Mele tebarek mitre mitre neger takerblinaleh
2026-11-14 14:52:37
0
yonas Asrat :
2026-11-14 18:43:39
0
ሳራይቱ የአብርሃም ሚስት🌸 :
100%
2026-11-09 07:03:11
1
የሸዋው መኳንንት :
2026-11-08 13:08:33
0
የሚካኤል :
ሁሌም ክላስካል ምርቻዎችህ ለምን ያ አሸንፉኛል?
2026-11-08 18:57:35
1
kidistamsalu :
[Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming]
2026-11-09 08:58:42
1
Eleni Aron :
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2026-11-09 05:20:22
1
sheto getaneh :
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2026-11-08 12:47:24
1
Choke total care solution :
🥰🥰🥰
2026-11-15 19:31:27
0
Alemtsehay Hailu :
[Like][Like][Like]
2026-11-17 07:41:30
0
To see more videos from user @melakuberhanu82, please go to the Tikwm
homepage.