@tout.monde3:

TOUT MONDE
TOUT MONDE
Open In TikTok:
Region: CD
Sunday 08 November 2026 20:15:29 GMT
3420
318
5
5

Music

Download

Comments

la.force.ou.rien
la force ou rien :
[Réconfortant][Réconfortant][Réconfortant]
2026-11-08 21:56:59
0
pedro.lp30
PEDRO LP :
🥰🥰🥰
2026-11-08 21:38:30
0
babytigre36
babytigre36 :
🥰🥰🥰
2026-11-08 21:13:33
0
letodrup4
Leto drup :
🔥🔥🔥
2026-11-08 21:08:53
0
user9171178210668
Gazlp :
🥰🥰🥰
2026-11-08 22:01:23
0
To see more videos from user @tout.monde3, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

Har'a moo Boru 🤌☺️ ✍️ሰባት ቋንቋዎችን ይናገራል። በስድስት ቋንቋዎች ማለትም በአፋን ኦሮሞ፣ በሶማልኛ፣ በሐረሪ፣ በአማርኛ፣ በአረብኛ እና በስዊዲሽ ቋንቋዎች ዘፍኗል። አስደናቂ የዜማ ደራሲ እና ሙዚቃ አቀናባሪ ነው።  በዚህ መልክ ተስረቅራቂ ድምፅ ያለው ድምፃዊ፣ የበርካታ የተለያዩ የሙዚቃ መሣሪያዎች ተጫዋች፣ ሙዚቃ አቀናባሪና በስድስት ቋንቋዎች የዘፈነ ምናልባት ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ምናልባትም ብቸኛው አፍሪካዊ ሊሆን ይችላል።  ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለጓዳኞቹ ለአርቲስት ጥለሁን ገሠሠ እና አርቲስት መሐሙድ አህመድ ጭምር ዜማዎችን ደርሷል።  በአገራችን ከፍተኛ የድምፅ ቅላፄ ካላቸው ባለልዩ ተሰጥኦ ምርጥ ድምፃውያን አንዱ ነው።  ለአፔራ አዘፋፈን የሚመች ኦፕራ ድምፅ አለው። መድረክ ላይ ቆሞ ሲዘፍን ሰዉን በፍቅር የመስብ ኃይል (Magnetic attraction)አለዉ። የዛሬው ተመስጋኝ ባለታሪካችን የክብር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ 🙌🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ በመጀመሪያ ቋንቋ ባለማወቅ የሙዚቃውን ግጥም ካሳሳትኩኝ አስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ🙏 ባለፉት ስልሳ ዓመታት በኢትዮጵያ የጥበብ ሰማይ ለይ ነግሶ የትውልድ ተምሳሌት ሆኖ  የኢትዮጵያ ሙዚቃን ወደላቀ ደረጃ በማሸጋገር ረገድ ወሳኝ ድርሻ ከተጫወቱ  ድንቅና አንጋፋ የጥበብ በለሙያዎች አንዱ የሆነው ታላቁ አርቲስት የክብር ዶ/ር አሊ ብራ ከአባቱ አቶ መሐመድ ሙሣ እና ከእናቱ ወ/ሮ ፋጡማ አሊ በ1940 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ገንደ ቆሬ ሠፈር ተወለደ። የልጅነት መጠሪያ ስሙ አሊ መሐመድ  ሙሣ የሆነውና አሊ ብራ በሚል የጥበብ ስሙ የሚታወቀው እና በቅርብ ወዳጆቹ Adeeroo (አጎት) በሚል የፍቅርና የክብር ስም የሚጠራው አሊቢራ በሕይወት ዘመኑ 267 ምርጥ ዘፈኖችን ዘፍኗል። ዘፈኖቹ በሙሉ በሁሉም  የሚወደዱ፣ ሙዚቃ የአለም ቋንቋ ነው የሚባለውን አባባል በተግባር ያሳየ፣ የአገራችን ወጣት ድምፃውያን ወደ ሙያዉ ሲገቡ ሙያቸውን ለማዳበር ከሁሉ በላይ የሚመርጡት፣በትንሽ በትልቁ የሚወደዱ በየትኛውም የሙዚቃ ዝግጅት ላይ የሚዘፈኑ ምርጥ ዘፈኖች ናቸው። ሥራዎቹ ተሰምተው የማይጠገቡ፣ ቋንቋውን ለሚችል ብቻ ላይሆን ሙዚቃን ለሚወድ ሁሉ የሚሰማሙ  የማያረጁና የማይረሱ፣ ከትውልድ ወደ ትወልድ የሚተላለፉ ዘመን ተሻጋሪ የአገር ቅርሶች ናቸው። አርቲስት አሊ ቢራ ያልዘፈነበት የሕይወት ጉዳይ የለም። ፍቅርን፣ እርቅን፣ ሰላምና መተሳስብን አጉልቶ አሳይቷል። አንድነትን ሰብኳል። በአገራችን ፖለቲካ ልዩነትና በተለያዩ መንገዶች መከፋፈልና መናቆር እያቆጠቆጠ በመጣበት በ1960ዎቹ አካባቢ Haati teenya Takkaa Maaltu addaan nu baasee?  እናታችን አንድ ነች ምንድነው የሚያለያየን የሚል ብርቱ ጥያቄን በዘፈን በማንሳት መቻቻልና ተቀራርቦ ችግርን በውይይት መፍታትን፣ ፍቅርንና አንድነትን የሚሰብክ  ጥልቅ መልእክት ያለው ዜማ በማቀንቀን ፈር  ቀዳጅ የህዝቦች የአንድነት ድምፅ ሆኖ አገልግሏል። የአሊ ቢራ  ድምፅ የፍቅርና  የነፃነት ድምፅ ነው። ለኦሮሞ ሕዝብ እና ለመላ ጭቁኖች  መብት፣ ነፃነትና አኩልነት ጠበቃ ሆኖ የዘመረ፣ የቀሰቀስና ሕዝብን  ያንቀሳቀስ ወደር የሌለው ጀግና የሕዝብ ልጅ እና ግንባር ቀደም የነፃነት አርበኛ ነው። በዚህ ሥራውም ተወዳዳሪ የሌለው የመብት ተሟጓች በመሆን በኦሮሞና  በኢትዮጵያ ብሔሮች ልብ ውስጥ ሁሌም ሲታወስ፣ ሲወደስና ሲዘከር የሚኖር የሕዝብ ባለውለታ መሆኑን በተግባር አስመስክሯል፡፡ በዘመን ተሻጋሪ ስራዎቹ የሁሉንም ቀልብ የሚስብ ተፅዕኖ ፈጣሪ የትውልድ ተምሳሌት ለመሆንም በቅቷል፡፡ በአጠቃላዩ ዶ/ር አሊ ቢራ በኦሮሞና በመላ ኢትዮጵያ የሙዚቃ እድገት ላይ ደማቅ አሻራ ያኖረ እና በቀላሉ የማይተካ የዘመን ክስተት ነው። የክብር ዶ/ር አሊ ቢራ በድንቅ የጥበብ  ስራው በቀድሞው መንግሥት ባለመወደዱ በርካታ እንግልት፣ እሥራትና ችግር ደርሶበታል። ይህ አሳሳቢ ሁኔታ እየከፋ በሄደበት በ1977 ዓ.ም የስዊድን ዜጋና በኢትዮጵያ የአገሯ ዲፕሎማት ከነበረችው የቀድሞ ባለቤቱ  ወ/ሮ ብርጊታ አስትሮም ጋር አገሩን ጥሎ ወደ ስዊድን ለመሰደድ ተገደደ።ለተወሰኑ አመታት ስዊድን፣ ሳዑዲ አረቢያና አሜሪካ ኖሯል።ከባለቤቱ ከተለያየ በኋላም ካናዳን የረጅም ጊዜ የመኖሪያ አድራሻው አድርጎ ነበር። በአሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በአውስትራልያና በመካከለኛው ምሥራቅ በመዘዋወር  የአገራችንና የሕዝቦቿ የጥበብ አምባሳደር በመሆን አገልግሏል። በታላላቅ የአለም መድረኮች ላይ ሰርቷል። ኢትዮጵያውን የዲያስፓራ አባላትን በማዝናናት እና በአይነ ህሊናቸው አገራቸውን እንዲያዩና ናፍቆታቸውን በሙዚቃ እንዲወጡ በማድረግ ታላቅ ውለታ ውሏል። ወደ አገሩ ከተመለሰ በኋላ አሊ ቢራ የህፃናት ትምህርት ፈንድ የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በማቋቋም ወገኑን ለማገልገል ከፍተኛ ፍላጎቱን አሳይቷል፡፡ አርቲስት አሊ ቢራ በፀባዩ ሰዉ ወዳድ፣ ትንሽ ትልቁን አክባሪ፣ ቸር እና ለተቸገረ መስጠትና ለህዝብ መስጠትን የታደለ፣  በቀልድ እያዋዛ የማዝናናት ልዩ ተስጥኦ ያለው ሁለገብ የጥበብ ሰው ነዉ።ከልጅነቱ ጀምሮ በዘፋኝነቱና በነፃነት ታጋይነቱ እንደተወደዳ እና እንዳተከበረ የዘለቀው  ታላቁ የሙዚቃ ንጉስ የክብር ዶ/ር አሊ ቢራ ምጥቀት ላለው የሙዚቃ ሥራው ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሸልማቶችን ከአገር ዉስጥና ከውጭ አገራት አግኝቷል። በአለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያላቸው ከ100 በላይ ሸልማቶችንም ወስዷል። ምርጥ የአፍሪካ ዘፋኝ ሆኖ ያገኘዉ ሸልማትም ከእነዚሁ ውስጥ ይገኛል። ታላቁ የሙዚቃ ንጉስና የኦሮሞና የአገራችን የሙዚቃ አባት  የሆነው አርቲስት አሊ ቢራ ከአብራኩ የወጡ ልጆች ባይኖሩትም የትውልድ ተምሳሌት በመሆን በርከታ ዕውቅ አርቲስቶችን አፍርቷል። በምርጥ የሙዚቃ ሥራዎቹ  በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ አስቀምጧል። በኦሮሞ የሞጋሳ ሥርዓት እልሊ ቢራ ተብላ ተሰይማ አሮሞነትን የተቀዳደችው እና  እየተንከባከበች  አብራ ከምትምኖረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሊሊ ማርቆስ ጋር በተወለደበትና ከፍተኛ የህዝብ ፍቅር ባገኘበት አገሩ በሰላምና በፍቅር እየኖረ በተደጋጋሚ ያጋጠመውን የጤና ችግር በውጪ አገርና በአገር ውስጥ እየተከታተለ ወገኑን በሙያዉ እያገለገለ ሰንብቷል። በመጦሪያ ወቅቱ ከፍተኛ ህመም አጋጥሞት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ጥቅምት 27/2015 ዓ.ም ቀን ምሽት በተወለደ በ75 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ስራዎቹ ግን ህያው ሆነው ይኖራሉ ነፍስ ይማር💔🙏 🗣ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡  musictube 🇪🇹  #fyp #haramooboru #alibirra #musictube369 #ethiopianmusic🇪🇹🇪🇹🇪🇹

About