@maleda_zena: መሬትን የቧጠጠ የሴት ጉልበት፦ የወይዘሮ Senait Gashaw ህያው አሻራ በኮምቦልቻ አንድ አካባቢ ወይም ከተማ በታሪክ ሲታወስ በህንፃዎቹ ብዛት አሊያም በኢንዱስትሪዎቹ ግርግር ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም መሬቱን አልምተው፣ አካባቢውን ለውጠው ትውልድ የሚያስመሰግን አሻራ በተከሉ ጠንካራ ባለታሪኮችም ጭምር እንጂ። በኢንዱስትሪዎቿ የምትታወቀው የኮምቦልቻ ከተማ ዛሬ ውብና ንጹህ አየር፣ ለነዋሪዎቿም የመንፈስ እፎይታን የሰጠ ድቅዳቅ አረንጓዴ ስፍራ አላት። የዚህ ድቅዳቅ አረንጓዴ ገነት ጀርባ ደግሞ መሬትን በቆራጥነት የቧጠጠ፣ ጥረትንና ትጋትን ያስመሰከረ የወይዘሮ ሰናይት ጋሻው የሴት ጉልበት አለ። የወይዘሮ ሰናይት ታሪክ የጽናትና የትጋት ፍጹም ማሳያ ነው። ታሪኩ የሚጀምረው በሰኔ ወር 2004 ዓ.ም ከተማ አስተዳደሩ በሰጣቸው 20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ነበር። በወቅቱ ይሄ ቦታ ውበት የሌለው፣ በቦርከና ወንዝ ዳርቻ የሚገኝና የከተማዋ የቆሻሻ መጣያ የነበረ ገደላማና ቦረቦር ስፍራ ነበር። ብዙዎች እንደ ቆሻሻ አይተው የተዉትን ቦታ ወይዘሮ ሰናይትና ባለቤታቸው ግን በሌላ ዕይታ ተመለከቱት። በበጋና በክረምት ሳያረፉ በተደረገ ዘመናት የተሻገረ ተጋድሎ፣ ያንን የቆሻሻ ቦታ ቀስ በቀስ ወደ አረንጓዴ ገነትነት ለወጡት። ዛሬ በኮምቦልቻ ከተማ (በሸሻቢር አወስኮድ መገንጠያ ገባ ብሎ) የሚገኘው "የሰናይት መናፈሻ" ከመዝናኛ ስፍራነት ባለፈ የብዙዎች ህይወት ማረፊያና የመልካም ስራ ማሳያ ሆኗል፦ መናፈሻው ሀገር በቀልና የውጭ ሀገር ዛፎችን ብቻ የያዘ ሳይሆን፣ አቮካዶ፣ ቡና፣ ፓፓያና ልዩ ልዩ አትክልቶችን አካቶ የያዘ ምርታማ ስፍራ ነው። ስፍራው ለከተማዋ ነዋሪዎች ንጹህ አየር የመሳቢያ፣ ለተማሪዎች የማንበቢያ፣ ለልጆች መጫወቻና ለበዓላት ማክበሪያ ሆኖ ያገለግላል። እንዲያውም በአንድ ጊዜ እስከ 15 ጥንድ ሙሽሮችን ከአድምተኞቻቸው ጋር ማስተናገድ የሚችል ውብ የሰርግ ስፍራ ነው። ወይዘሮ ሰናይት መናፈሻውን በማልማት ብቻ አላቆሙም፤ ለአካባቢው ወጣቶች በቋሚነትና በጊዜያዊነት የስራ ዕድል ፈጥረዋል። በተጨማሪም የችግኝ ማፍያ ጣቢያ በማቋቋም ለአካባቢው ህብረተሰብ በቅናሽ ዋጋ ችግኞችን በማቅረብ ለሀገራዊው "የአረንጓዴ አሻራ" ጥሪ ግንባር ቀደም አጋር ሆነዋል (ለዚህም በ2024 በዳጉ መጽሔት የአመቱ ምርጥ ስፍራ ተብለው የተመረጡ ሲሆን፣ በከተማ አስተዳደሩም የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል)። ይህ ቦታ ከሩቅ ሲዩት የአውሮፓ ወይም የሌላ የዳበረ ሀገር ምድር ይመስላል። ነገር ግን ይሄ ውበት በከተማችን ኮምቦልቻ በቦርከና ራስጌ ላይ በሴት ልጅ ትጋትና ወዝ የተቀረጸ ህያው ምስክር ነው። ወይዘሮ ሰናይት ጋሻው "የኮምቦልቻ ከተማ የአረንጓዴ ልማት አርበኛ" ናቸው። ስራቸው በተግባር የሚታይ፣ ለሴቶችም ሆነ ለመላው ማህበረሰብ ትልቅ የጽናት ትምህርት የሚሰጥ በመሆኑ ልንኮራባቸውና ልንማርባቸው የሚገቡ ህያው ጀግናችን ናቸው። ቆሻሻን ወደ ገነት፣ ቦረቦርን ወደ ለምለም ምድር ለወጡት ለወይዘሮ ሰናይትና ለጠንካራ እጆቻቸው ምስጋና ይግባ! #ኮምቦልቻ #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #fyp #maleda #ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ማለዳ ዜና / Maleda News
ማለዳ ዜና / Maleda News
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 10 November 2026 05:05:04 GMT
233
18
1
0

Music

Download

Comments

user086845687
king haroon :
proud of you brother Kemal, what an incredible vision and excution ?
2026-11-10 05:21:20
0
To see more videos from user @maleda_zena, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About