@drveskincare_1: DRVE hadir untuk menemani hari-hari kecantikanmu 🧴 #SkincareDRVE #Skincare #SkincareRoutine #SkincareIndonesia #Beauty care #PerawatanKulit #KulitSehat #KulitGlowing #GlowUp #CantikAlami #DRVE #5IN1

Drve Official Store
Drve Official Store
Open In TikTok:
Region: ID
Tuesday 10 November 2026 13:26:56 GMT
10911
6
0
1

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @drveskincare_1, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

በትምህርት ስኬታማ ለመሆን ጠንክሮ ማጥናት ብቻ በቂ አይደለም - በብልሃት ማጥናት ነው። ከፍተኛ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች የሚያመሳስላቸው አንድ ነገር አለ፡- ጥረትን ወደ ውጤት የሚቀይሩ ውጤታማ የአጠናን ስልቶችን ይጠቀማሉ። ደስ የሚለው ነገር- ማንኛውም ተማሪ እነዚህን ስልቶች መማር እና ተግባራዊ ማድረግ ይችላል። የአጠናን ስልቶቹ የሚከተሉት ናቸው:-  🌟 1. ስታጠኑ ግልጽ የሆነ ዓላማ  ይኑራችሁ የምታጠኑትን መጽሐፍ ወይም ደብተር እንዲሁ አትግለጡት- መጀመሪያ ለምን እንደምታጠኑ እወቁ። እራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁ፡- በዚህ የጥናት ጊዜዬ ምን መረዳት ወይም ማሳካት እፈልጋለሁ? በዓላማ የሚያጠና ተማሪ በትኩረት ያነባል፣ የተሻለ ያስታውሳል፣ ጊዜውን አያባክንም። 👉 ምሳሌ፡- “ሳይንስ ወይም ባዮሎጂ አጠናለሁ” ከማለት ይልቅ “የሰው ልጅ ልብ እንዴት እንደሚሰራ ••• እረዳለሁ” በሉ። 🧠 2. ተግባራዊ የንባብ ስልትን ተጠቀሙ፣ እንዲሁ ለማንበብ አትሞክሩ ማንበብ ብቻውን በቂ አይደለም። አእምሮ በንቃት ሲሳተፍ አንድን ነገር በተሻለ ሁኔታ መረዳት ትችላላችሁ።  ለምሳሌ ይህንን ሞክሩ፦ 👉 ያነበባችሁትን ነገር በራሳችሁ አገላለጽ ወይም ቃላት ከልሱት።  👉 ፅንሰ-ሀሳቡን ለጓደኞቻችሁ አስረዱ።   👉 በምታጠኑበት ጊዜ ለራሳችሁ ጥያቄዎችን ጠይቁ። 📌 አንድን ፅንሰ-ሀሳብ በቀላሉ ማስረዳት ከቻላችሁ፣ በትክክል ተረድታችሁታል ማለት ነው። ⏰ 3. ጊዜያችሁን በጥበብ አስተዳድሩ ጊዜ ትልቁ ሀብት ነው። ስኬታማ ተማሪዎች ተነሳሽነትን አይጠብቁም - የራሳቸውን የጥናት መርሃ ግብር አዘጋጅተው በዚያ ይመራሉ። 📌 ጊዜያችሁን በጥበብ ለመጠቀም የሚከተሉትን ቴክኒኮች/ዘዴዎች ተጠቀሙ፦ 👉 አእምሮአችሁን ሰብሰብ አድርጋችሁ ከ25–50 ደቂቃዎች ያህል በትኩረት አጥኑ። 👉 በመካከል አጭር እረፍት ውሰዱ። 👉 ከባድ ለሆኑ ትምህርቶች ቅድሚያ ስጡ አስተውሉ: በየቀኑ የሚደረጉ ትናንሽ ነገር ግን ወጥ የሆኑ ጥረቶች በመጨረሻ ሰአት ላይ የሚኖር መጨናነቅን ይበልጣሉ። 📅 4. አስቀድማችሁ በማቀድ በተደራጀ ሁኔታ አጥኑ ግልጽ የሆነ እቅድ ጭንቀትን ይቀንሳል፤ በራስ መተማመንንም ይጨምራል። 👉 ማስታወሻ ደብተር ወይም እቅድ ማውጫ ተጠቀሙ። 👉 ትላልቅ የጥናት ተግባራትን ወደ ትናንሽ ደረጃዎች ከፋፍሏቸው። 👉 ዕለታዊ እና ሳምንታዊ የጥናት ግቦችን አዘጋጁ። 📌 ጊዜያችሁን ስታቅዱ፣ የወደፊት ሕይወታችሁን ትቆጣጠራላችሁ። 🔁 5. አዘውትራችሁ ከልሱ መርሳት ተፈጥሯዊ ነው—ነገር ግን ክለሳ መርሳትን ይፋለመዋል። 👉 በጥናት ወቅት የምታዘጋጇቸውን ማስታወሻዎቻችሁን ምንጊዜም በ24 ሰዓታት ውስጥ ከልሱ። 👉 ከዚህ በፊት የተጠኑ የተለያዩ ርዕሶችን በየሳምንቱ እንደገና ለማየት ሞክሩ። 👉 ያለፉ ጥያቄዎችን በመስራት ተለማመዱ አስተውሉ:  አንድን ነገር መደጋገም ችሎታን ይገነባል። 🧩 6. ማንበብ ብቻ ሳይሆን ለልምምድ ትኩረት ስጡ በተለይ እንደ ሂሳብ፣ ፊዚክስ ወይም ኬሚስትሪ ላሉ ትምህርቶች ልምምድ ሁሉም ነገር ነው። 👉  ኘሮብሌሞችን ለመፍታት ጥረት አድርጉ Solve Problems 👉 ማስታወሻዎችን (notes) ሳትመለከቱ እራሳችሁን ፈትሹ 👉 ከስህተቶቻችሁ ተማሩ 📌 ስህተቶች ውድቀቶች አይደሉም—ምርጥ አስተማሪዎች ናቸው። 📵 7. ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮችን አስወግዱ አካባቢያችሁ ስኬታችሁን ይቀርፃል። 👉 ስልካችሁን ከአጠገባችሁ አርቁ ወይም ድምፁን አጥፉት። 👉 ጸጥ ያለ የጥናት ቦታ ምረጡ። 👉 በአንዴ ብዙ ነገሮችን ከማከናወን ተቆጠቡ። 📌  ባለንበት ሃሳብን በሚከፋፍል ዓለም ውስጥ #ትኩረት ማድረግ ሃይልን የሚያጎናፅፍ ልማድ ነው።  💪 8. ሰውነታችሁን እና እምሮዎአችሁን ተንከባከቡ የደከመ አእምሮ ውጤታማ በሆነ መንገድ መማር አይችልም።  👉 በቂ እንቅልፍ አግኙ 👉 ጤናማ ምግብ ተመገቡ 👉 በየጊዜው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርጉ 📌 ጠንካራ ሰውነት ጠንካራ አእምሮን ይፈጥራል። 🚀 9. በየጊዜው አቅማችሁን ማሻሻል እንደምትችሉ እምነት ይኑራችሁ ብዙ ተማሪዎች የሚወድቁት ከሌሎች ያነሰ የማሰብ ችሎታ ስላላቸው ሳይሆን በራሳቸው እምነት ስለሌላቸው ነው። #አስታውሱ፡- 👉 ብልህነት (የማሰብ/የመማር አቅም) በጥረት ያድጋል። 👉 እያንዳንዱ ስኬታማ የሆነ ባለሙያ በአንድ ወቅት ጀማሪ ነበር። 👉 ያለፈው ውጤታችሁ የወደፊቱን አይገልጽም።   👉 ለራሳችሁ እንዲህ በሉ፡- “ማንኛውንም ትምህርት መማር እችላለሁ። አሻሽላለሁ።” 🔥 የማጠቃለያ መልእክት በትምህርት ውስጥ ስኬት የእድል ጉዳይ አይደለም - የአጠናን ስልት፣ የዲሲፕሊን እና ስለራሳችሁ ያላችሁ እምነት ጉዳይ ነው። ስታጠኑ በትንሹ ጀምሩ። ወጥነት ይኑራችሁ። ወዲያው ሳይሆን ሂደትን ጠብቆ በሚመጣ ውጤት/ስኬት እመኑ። #መምህራን #ወላጆች  ይህን መልእክት ለተማሪዎቻችሁ (ለልጆቻችሁ) አድርሱልን🙏  በትምህርት ውጤታማ ሊያደርጓችሁ የሚችሉ በርካታ ሃሳቦች ይደርሷችሁ ዘንድ ይህን ገፅ ተከተሉት

About