@melkamukassaw148: ከጋራው ሥር ያለችው እመቤት፣ የታሪክ ማኅደር_ወለተ ጴጥሮስ አንድነት ገዳም ቦታው በተፈጥሮው ግርምትን ያጭራል፤ ውስጡም ታሪክን ሰንዶ የያዘ የታሪክ ማኅደር ነው። ተፈጥሮ ይደነቃል፤ የፈጣሪም ተዓምር በተግባር ይታያል በቅድስት ወለተ ጴጥሮስ አንድነት ገዳም። የቅድስት ወለተ ጴጥሮስ አንድነት ገዳም በአማራ ክልል በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በዳንግላ ወረዳ ይገኛል። ከዳንግላ ከተማም በ17 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወንደፋይ በተባለ ቀበሌ ነው የሚገኛው። መነኮሳት ለዘመናት በጽናት የዘለቁበት ጥንታዊ እና ታሪካዊ ሥፍራ ነው። የዳንግላ ወረዳ ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ቦጋለች ፋንታሁን እንደሚገልጹት የጻድቋ ወለተ ጴጥሮስ አንድነት ገዳም በሰንሰለታማ ተራራሮች ተከቦ በሸለቆማ ስፍራ የተመሠረተ ድንቅ ሥፍራ ነው። በርካታ ልዩ ገጽታዎች አሉት ነው የሚሉት። ገዳሙ በአጼ ሱስንዮስ ዘመነ መንግሥት በ1607 ዓ.ም በጻድቋ ወለተ ጴጥሮስ እንደተመሠረተ ይነገራል። ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ከአፋፍ ላይ ወደ ዋሻ የተወወረችበት ትልቅ አለታማ ድንጋይ ለታሪክ ቅርስነት፣ ለአማኞች ፈውስ እና የመንፈስ ማደሻ ኾኖ እያገለገለ ይገኛል። በተለይም ጻድቋ የተወረወረችበትን ምክንያት በማድረግ ገዳሙ እንደተመሠረተ ይነገራል ነው ያሉት። ገዳሙ ውስጥ ለመድረስም ወደ ዋሻው ወደታች መቶ ሜትር በእግር መጓዝ እንደሚያስፈልግም ያስረዳሉ። ገዳሙ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት እና ንዋየ ቅዱሳት ማኅደር ነው። በዙሪያው ሀገር በቀል ዕፅዋት፣ የተለያዩ የዱር እንስሳት እና አዕዋፍ በጋራ ተጋምደው ይገኙበታል። በገዳሙ የገዳማውያንን ጥንካሬ እና ሥራ ወዳድነት የሚያሳይ የግብርና እና የእንሰሳት እርባታም በስፋት አለ። ተስማሚ የአየር ሁኔታ ያለው ውብ ሥፍራም ነው። ከተራራው አፋፍ ወደ ታች ሲታይ ለመውረድ የማይቻል የሚመስል ነገር ግን ሲጓዙ ድንቅ ተፈጥሮን የሚያስቃኝ ማራኪ አቀማመጥ ያለው ነው። ይህ ድንቅ የተፈጥሮ እና የታሪክ ማኅደር አዕምሮ የሚያድስ፣ መንፈስ የሚያረካ፣ በረከትን የሚያስገኝ እና አዲስ ገጽታን መገንባት የሚያስችል ነው። ቦታውን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ፣ ለማስተዋወቅ እና በዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማሳደግ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ። የገዳሙ ዓመታዊ ክብረ በዓል በየዓመቱ ኅዳር 17 ቀን ከተለያዩ አካባቢዎች በሚመጡ የሃይማኖቱ ተከታዮች በድምቀት ይከበራል።
@𝙈𝙚𝙡𝙠𝙖𝙢𝙪✔️
Region: ET
Tuesday 10 November 2026 13:47:42 GMT
Music
Download
Comments
O$ :
ለቤቷ ያብቃሽ በሉኝ አይኔን ታምሜ ወለተ ጴጥሮስገዳም ደርሳ የመጣች ልጅ እምነት ና ፀበሏን ሰጣኝ ተቀብቸ ወዲያውኑ ዳንሁ!!! እግዚአብሔር ይመስገን።
2026-11-11 17:02:09
20
Mathias :
ከ18 ዓመት በፊት አንዴ ሄጃለሁ፣ አሁንም ግን ለቤቷ እንድታበኝ እፀልያለሁ።
2026-11-14 08:43:55
3
ዝብርቅ እርቅ ያለ ሂወት🤦 :
ኦፍፍፍ አገሪ
2026-11-12 07:23:14
3
kalkidan ye Maryam :
🥰🥰🥰🥰🥰 ህዳር 16 ዋዜማ ነው 🥰🥰🥰
2026-11-12 17:46:41
1
ክብር ለወንድ 👶👶 :
Ayyyy enema eko dena eyaleku hije neber ahun gin😭😭😭😭😭
2026-11-13 05:03:53
1
Yebeltal Bizuayehu :
የእኔ እናት የመነኮሰችበት ቅዱስ ስፍራ ❤️❤️❤️
2026-11-12 10:55:14
1
ab :
እንመጣለን
2026-11-14 16:20:18
1
Kidanemihret enate :
እሂንን ገዳም ቦታ ሂዱእዪት የነፍስቁስል ይፈወስበታል በእውነት ሳታዩት እንዳትቀሩ🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-11-14 02:40:20
1
Abere Debas :
ወለተ ጼጥሮስ ድንቅ የሆነች አንነት ገዳም !!
2026-11-13 12:06:50
3
Sነኝ የወድሟ ናፋቂ💔💔😭 :
ህዳር 16ለ17 ደረሰ ቀኑ በጣም ጓጉቻለሁ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-11-13 14:27:45
2
ወርቋ 🚀🚣🚀 :
እናቴ ወለቴ እባክሽ ለሀገሬ አብቂኝ ሠላምን አምጭልን💗💗💓💗💗💓
2026-11-12 06:11:47
6
እሙ የገጠሯ ልጅ :
እረ ኡኡኡኡ እንባዬ መጣ ክርስቶስን
2026-11-13 17:20:48
2
dnki :
ወይ አስታሀወሳችሁኝ ዳግላ 11እና 12ኛ ክፈል ተማሪ እያለሁ ሂጃለሁ እንዴት ደስ እንደሚል
2026-11-11 18:51:48
4
Dokimas :
ይሄን ቦታ አቀዋለሁ እጅግ ደስ የሚል እና ነፍስን የሚያሳርፍ ገዳም ነው 💚
2026-11-12 14:11:37
2
ሳተናው ጎጄ :
በረከቷ ይደርብን
2026-11-12 16:38:20
2
ጎጃሜው@2085 :
አሜን ኤሜን@
2026-11-13 04:46:42
1
ቃሉ ይነበብ :
ያዬ ይናገር
2026-11-13 13:43:15
1
Mati 💚💚 💛💛♥️♥️ :
🙏🙏
2026-11-13 20:41:47
1
lij abusha :
እናቴ ወለቴ
2026-11-13 04:54:28
1
ዮናስ :
እናቴ ወለቴ አች ጠብቂን🙏🙏🙏🙏
2026-11-12 06:28:06
3
@nawi :
በጣም ቅዱስ ቦታ ነው ሂዱ ተፈወሱ
2026-11-12 13:52:22
2
user15390499253696 :
ወለትየ ቃል የለኝም
2026-11-12 12:41:09
1
Tsige Genet :
ለቤቷ ያብቃን ለእናታችን ወለተ ጴጥሮስ አመታዊ ክብረባል
2026-11-13 19:21:25
1
Mequ :
ወለተ ጼጥሮስ ገዳም
2026-11-12 14:49:12
1
Hani Hani :
እናቴ ወለቴ
2026-11-12 05:37:39
2
To see more videos from user @melkamukassaw148, please go to the Tikwm
homepage.