@mikre_timihirt: ✍️ 1ኛ Over Generalization ይባላል።  አንድ ሀገር ሄድኩና አንድ ናይጄሪያዊ አግኝቼው ጉዳት አደረሰብኝ እንበል። ያ ግለሰብ ያደረሰብኝን ጉዳት ከእርሱ ጋር በቀጥታ ከማገናኘት ይልቅ የናይጄሪያ ሰዎች እኮ ክፉዎች ናቸው፤ መጥፎዎች ናቸው! ብዬ እጠቀልላለሁ። ይህም የተሳሳተ መረዳት የአሉታዊ አስተሳሰብ አንዱ አካል ነው። ✍️2ኛ  Polarization ይባላል። ለምሳሌ ፦ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደርን በተመለከተ አንዳንዶች ፈጽመው ሙሉ በሙሉ ሲቃወሙት ሌሎች ደግሞ ሙሉ በሙሉ ይደግፉታል። የሚቃወሙት ይህ አስተዳደር አንድም በጎ ነገር አያደርግም ሲሉ፣ የሚደግፉት ደግሞ ይህ አስተዳደር አንድም ጥፋት አያጠፋም፣ ፍጹም ነው ይላሉ። ይህ ዋልታ ረገጥ አስተሳሰብ ነው Polarization የሚባለው። ✍️3ኛ  Mental Filtering ይባላል።   እኔ በአንድ አዳራሽ ውስጥ 2000 ሰዎች በተሰበሰቡበት ስልጠና ሰጠሁ እንበል። እያስተማርኩ እያለ አንድ ሰው ብድግ ብሎ አዳራሹን ጥሎ ወጣ። ማታ ቤቴ ስገባ የማስበው ሰለተማሩት እና ስለተደሰቱት 1999 ሰዎች ሳይሆን ጥሎ ስለወጣው አንድ ሰው ይሆናል። ይህ Mental Filtering ይባላል፡፡   ✍️4ኛ Discounting the Positive ይባላል። በዚህ መገለጫ ማንኛውም እኛ ያለንን ጥሩ ነገር እናጣጥለዋለን። ለምሳሌ አንድ ሰው አንዲት ሴትን “ቆንጆ ነሽ" ካላት መልሷ "ምን ዋጋ አለው ቁንጅና? ታጥቦ አይጠጣ!" ትለዋለች። ጥሩ ተምረሃል" ከተባለ ሌላው ሰው “ምን ዋጋ አለው ብለህ ነው ትምህርት! ገንዘቡ ያለው እንደሆነ ያልተማሩት ጋር ነው" ይላል። የሚነገራቸውን ጥሩ አስተያየት ሁሉ ያጣጥሉታል፤ አይቀበሉትም ይህም Discounting the Positive ይባላል።  ✍️5ኛ Jumping to Conclusion ይባላል። አንድ ሰራተኛ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደርጋል። ንግግሩን ከጨረሰ በኃላ አንድ ክፍል ሀላፊ የእርሱን ንግግር የሚቃወም የሚመስል ነገር ተናገረ እንበል። በሌላ ቀንም ባጋጣሚ ይህ ሰራተኛ ከተናገረ በኃላ ያው የቢሮ ሀላፊ የሰራተኛውን ሀሳብ የሚቃወም ሀሳብ ተናገረ። በዚህ ጊዜ ሰራተኛው ይሄ ሰውዬ በጣም ይጠላኛል ብሎ እርግጠኛ ይሆናል። ይህም Jumping to Conclusion ይባላል። ✍️6ኛ  Magnification ነው። ይህ ደግሞ ችግሮችን ከመጠን በላይ አጉልተን እንድናይ የሚያደርግ ነው፡፡ ቤት ውስጥ የምትሰራ ስራተኛ ስሀን ስታጥብ ከእጇ አምልጦ ተስበረባት እንበል፡፡ እመቤቲቱ መጥታ ለምን ስበርሽው? ትላታለች። ትቀጥልና እስከመቼ ነው እቃ እየሰበርሽ ምትኖሪው? ትላለች። አሁንም ትቀጥልና እኔ ገንዘብ ከየት የማመጣ ይመስልሻል? ወይስ አውቀሽ ነው ምትሰብሪው? ሰሀኑ መሰበሩ እውነት ነው እመቤቲቱ ግን በጣም ከመጠን አብልጣ ታጎላዋለች። ይህም Magnification ነው። ✍️7ኛ Emotional Reasoning ይባላል። ይህም በስሜት ሆኖ መወሰን ነው። አንድ አለቃ በጣም ሚጠቅመውን ሰራተኛ በድንገት ተነስቶ ያባርረዋል፡፡ ይህ ግን የተሳሳተ ውሳኔ ነው! ያንን ሰራተኛ መልሼ ላግኝህ ቢለው እንኳን ያስቸግረው ይሆናል። ውሳኔውን በስሜት ነው የወሰነው። አስቦበት አይደለም የወሰነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ አንዲት ሚስት በባሏ ተበሳጨች እንበል፡፡ ድንገት ተነስታ ቀለበቷን አውልቃ ወርውራ፣ ሻንጣዋን ሽክፋ፣ በጣም መጥፎ ነገር ባለቤቷን ተናግራ ከቤት ትወጣለች፡፡ ይህም ትዳራቸውን ያናጋዋል ወይንም ያፈርሰዋል። ይህ ነው Emotional Reasoning የሚባለው። 🗣 ዶ/ር ወዳጀነህ መኀረነ

ምክረ-ትምህርት
ምክረ-ትምህርት
Open In TikTok:
Region: ET
Wednesday 11 November 2026 15:58:40 GMT
10804
258
16
53

Music

Download

Comments

user8346933228114
user8346933228114 :
I like it
2026-11-13 08:54:33
1
user3532475038876
user3532475038876 :
ትክክል
2026-11-12 15:32:51
1
tse.security
Tse security :
Wow Dr thanks
2026-11-12 01:08:19
1
user1507938931470
user1507938931470 :
Oh Dr, they are very nice taughts and teachable. Really I proud to you, please keep it up for future also. So many thanks Dr.
2026-11-11 21:15:48
1
john199454
Jo Jo. :
Good job🥰🙏
2026-11-12 17:14:34
1
user1946200911978
dani :
smart
2026-11-12 11:27:39
0
bire.tashe
Bire Tashe :
[Red heart][Red heart][Red heart][Red heart][Red heart] Yaada Baay'ee barumsaa Guddaa Namaf kennudha.
2026-11-13 21:18:58
0
user7660670409239
gashe :
Ejg yemitekimina asfelagi timidity.
2026-11-13 14:57:32
1
mamush.aisda
Mamush AISDA :
👍👍
2026-11-12 09:57:35
1
To see more videos from user @mikre_timihirt, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About