@anwar.radi7: #'የታክሲ የለኝም እባክህ ልጄን ይዘሃት ሂድ....😥; «እባክህ ልጄን ይዘህልኝ ትሄዳለህ? እኔ የታክሲ ገንዘብ የለኝም... እቀፋት ንፁህ ናት!» ዛሬ ጠዋት ታክሲ ውስጥ ሙሉ ተሳፋሪውን በእንባ ያራጨ፣ እስከ አሁን ድረስ ውስጤን እያደማው ያለ ልብ ሰባሪ ክስተት... ጠዋት ወደ ስራ ለመሄድ ታክሲ ተሰልፌ ገባሁ። በመስኮት በኩል ሳስተውል አንዲት እናት በጣም ቆንጆ የትምህርት ቤት ዩኒፎርም የለበሰች ትንሽ ልጇን እጅ ይዛ ቆማለች። ታክሲው ሊሞላ ጥቂት ሰው ብቻ ነው የቀረው፤ «ይቺ እናት ለምን አትገባም? ልጇ አረፈደች እኮ...» እያልኩ በልቤ ሳስብ... እናትየው ድንገት ወደ መጀመሪያው ወንበር ተጠግታ መስኮቱን አንኳኳች። የፊት ወንበር ላይ የተቀመጠው ሰውዬ መስኮቱን ሲከፍተው በለዘበ፣ በሀፍረትና በጭንቀት በተሰበረ ድምፅ እንዲህ አለችው፦ «ወንድሜ... እባክህ ልጄን ይዘህልኝ ትሄዳለህ? እኔ የታክሲ ገንዘብ የለኝም... እቀፋት ንፁህ ናት!» ይሄን ስትል የታክሲው ድባብ ድንገት ፀጥ አለ፤ ልቤ ተንሰፈሰፈ! «እቀፋት ንፁህ ናት» የሚለው ቃሏ እንደ ጦር ልቤ ውስጥ ተሰካብኝ። ድህነት እንዲህ ያሳንሳል? የገዛ ልጇን ሰው እንዲሸከምላት ስትለምን እንኳ «ንፁህ ናት» ብላ ይቅርታ እንድትጠይቅ ያስገድዳል? የፊት ወንበር የተቀመጠው ጨዋ ሰው ያለምንም ማመንታት «ኧረ በደስታ እህቴ! ምንም ችግር የለውም፤ ችግር አይንካሽ አምጪያት» ብሎ ልጅቷን በክብር ተቀብሎ አቀፋት። ረዳቱም «የትምህርት ቤቱን በር አውቀዋለሁ እዛው አወርዳታለሁ አትጨነቂ» አለ። እናት ግን ልቧ አልቻለም... የልቧ ጭንቀት እረፍት ነሳትና ዐይኖቿ በእንባ ተሞልተው «እባክህ ስልክህን ጻፍልኝ?» አለችው፤ የእናት አንጀት አይደል! ስልኩን ተቀበለች። ድህነት አይኑ ይጥፋ ወላሂ! ይሄን ያየው ተሳፋሪ በሙሉ ልቡ ተነካ። ሁሉም ኪሱን ፈትሾ ለነገዋ፣ ለቀጣዩ ቀኗ የታክሲ የሚሆናትን ብር አዋጥቶ ሰጣት። ታክሲው ተነስቶ መንቀሳቀስ ሲጀምር... ያቺ ምስኪን እናት ታክሲው እይታዋ እስኪሰወር ድረስ እዛው ቆማ፣ በልጇ ላይ ያፈጠጠውን የፍቅርና የጭንቀት ዐይኗን ሳትነቅል እያየችን ቀረች። እናት ማለት ይቺ ናት... ለልጇ ትምህርት ስትል ክብሯን ጥላ የምትለምን፣ ራሷ በባዶ እግሯ ቆማ ልጇን ወደ ከፍታ የምትሸኝ! ፈጣሪ ለደጉ ተሳፋሪም፣ ለምስኪኗ እናትም ይድረስላቸው።
Anwar radi ሰበሽ በለን 🇪🇹 🇵🇸
Region: ET
Thursday 12 November 2026 20:25:16 GMT
Music
Download
Comments
FREE FREE PALESTINE :
አድራሻ ፈልጉልን ቻሌንጅ ይጀመርላት
2026-11-13 05:18:07
33
abdu jobero :
ወላሂ እኔንም ገጥሞኛል ከአቶብስ ተራ አሸዋ ሜዳ ሶስት ልጆች ሁለቱ መንታ ሴት ልጆች አንደኛው ወንድ ታላቃቸው ረዳቱ ያላደረጋቸውን አትጠይቁኝ ካፉ ሚወጣው አልቻልኩም ተጣላን ከዛም ወንዱን ከዃላዬ ላለው ሁለቱን እኔ አቅፌያቸው እቤታቸው አደረስኳቸው አሁን ብታዩ መንገድ ሲያገኙኝ እንስፍስፍ ብለው ጥምጥም ነው ሚሉብኝ ከአባታቸውም አስተዋወቁኝ መልካምነት ለራስ ነው
2026-11-13 02:58:11
28
Ibrahim :
ታሪኩ በጣም ያማል ነገር ግን ታክሲው ላይ ያሉት ሰዎች አዋጥተው ከሰጧት ለምን እናቷ ቸከትላት ትምህርት ቤቷ ድረስ አልሄደችም??????
2026-11-13 04:53:53
3
Abdilhamed Mohamed :
yet new yalechw yalegnn lredat felga ebakachu ngerugn
2026-11-13 03:28:43
0
እኔም ብሎ አኩራፊጨነቀኝ ብጠፊ :
የእዝነት በሩ ይክፈትልሾ
2026-11-13 07:18:52
2
My mom❤❤❤ :
ኡፉፉፉፉ አረ ቁጥሯ ካላቹ ባለን ነገር እንተባበራት ወላሂ አቦ ድህነት አይኑ ይጥፋ😭😭😭😭
2026-11-13 05:26:27
9
Ahmed Eshetu :
እርዳታ ሰጭ ነን የሚሉት ቲክቶከሮች የት ናቸው
2026-11-13 05:16:03
4
kedir56729 :
ወይኔ ችግርን አያጣዉ
2026-11-13 06:06:44
4
🦋ዲራር 🦅👈💗 :
ወላሂ እያለቀስኩ ነው ያነበብኩት የናንተም መልካምነት አላህ ያልታሰበውን ይለግሳት አቦ ያረብ😭😭😭
2026-11-13 10:43:29
1
lij mike✝️ :
አረ ኡ መረረን እኮ life 😭
2026-11-13 10:36:42
0
ቦን ካፌ እና ሬስቱራንት :
እንደምንም አድራሻዋን ስጡን እናግዛታለን
2026-11-13 08:33:08
1
ESAM💙💚🤐 :
allah kesua gar yihun
2026-11-13 07:38:42
1
አረ ጭዌ :
ሥልኳን ላኩልን እናግዛት
2026-11-13 11:38:41
0
ወሎ :
እኔ እራሴም ብዙ ችግር አለብኝ ነገር ግን መርዳት እፈልጋለሁ እኔ ሌላ ስርዳ አላህ ደሞ እኔን ይርዳኛል
2026-11-13 03:42:30
1
መሀመድ የመጋረጀ ስራ🇪🇹🇪🇹🇺🇸🇨🇦 :
እናት❤❤❤❤❤❤
2026-11-13 11:38:15
0
ኢሶጃን ሀደ ነገ :
አድራሻዋ የት ነው ወንድሜ
2026-11-13 04:09:12
1
ያልተኖረ ልጅነት :
😭😭😭😭😭😭😭😭አይይይይይይይ እናት 👍👍
2026-11-13 11:16:09
0
Ibrahim 🇨🇦❌🇩🇪 ❔❔♾🇪🇹 :
🥺🥺
2026-11-13 11:21:31
0
seyid Ali :
ኡፉፉፉፉፉፉፉ
2026-11-13 10:50:13
0
user86955405815178 :
ስልኳን ላኩልኝ
2026-11-13 07:18:11
0
Nesro_ :
ወለሂ አድረሻ ቻሌንጄ ይጀማር
2026-11-13 11:25:44
0
Life is Book 🤔🤔 :
ከሞት በለይ ኖሮ የስፈረል
በዜ ግዜ🥺😭😩
2026-11-13 11:04:54
0
Nesru Bilall :
ልብ ይሰብራል ለተቸገረ ሁሉ ፈጣሪ ይርዳው!
2026-11-13 11:14:29
0
Murade E :
ያዲስ አበባ ህዝብ ያለንበት ሁኔታ 😭😭😭
2026-11-13 09:05:04
0
Fafi :
ay chigr
2026-11-13 03:28:59
0
To see more videos from user @anwar.radi7, please go to the Tikwm
homepage.