@tesemamukura: «እባክህ ልጄን ይዘህልኝ ትሄዳለህ? እኔ የታክሲ ገንዘብ የለኝም... እቀፋት ንፁህ ናት!» ዛሬ ጠዋት ታክሲ ውስጥ ሙሉ ተሳፋሪውን በእንባ ያራጨ፣ እስከ አሁን ድረስ ውስጤን እያደማው ያለ ልብ ሰባሪ ክስተት... ጠዋት ወደ ስራ ለመሄድ ታክሲ ተሰልፌ ገባሁ። በመስኮት በኩል ሳስተውል አንዲት እናት በጣም ቆንጆ የትምህርት ቤት ዩኒፎርም የለበሰች ትንሽ ልጇን እጅ ይዛ ቆማለች። ታክሲው ሊሞላ ጥቂት ሰው ብቻ ነው የቀረው፤ «ይቺ እናት ለምን አትገባም? ልጇ አረፈደች እኮ...» እያልኩ በልቤ ሳስብ... እናትየው ድንገት ወደ መጀመሪያው ወንበር ተጠግታ መስኮቱን አንኳኳች። የፊት ወንበር ላይ የተቀመጠው ሰውዬ መስኮቱን ሲከፍተው በለዘበ፣ በሀፍረትና በጭንቀት በተሰበረ ድምፅ እንዲህ አለችው፦ «ወንድሜ... እባክህ ልጄን ይዘህልኝ ትሄዳለህ? እኔ የታክሲ ገንዘብ የለኝም... እቀፋት ንፁህ ናት!» ይሄን ስትል የታክሲው ድባብ ድንገት ፀጥ አለ፤ ልቤ ተንሰፈሰፈ! «እቀፋት ንፁህ ናት» የሚለው ቃሏ እንደ ጦር ልቤ ውስጥ ተሰካብኝ። ድህነት እንዲህ ያሳንሳል? የገዛ ልጇን ሰው እንዲሸከምላት ስትለምን እንኳ «ንፁህ ናት» ብላ ይቅርታ እንድትጠይቅ ያስገድዳል? የፊት ወንበር የተቀመጠው ጨዋ ሰው ያለምንም ማመንታት «ኧረ በደስታ እህቴ! ምንም ችግር የለውም፤ ችግር አይንካሽ አምጪያት» ብሎ ልጅቷን በክብር ተቀብሎ አቀፋት። ረዳቱም «የትምህርት ቤቱን በር አውቀዋለሁ እዛው አወርዳታለሁ አትጨነቂ» አለ። እናት ግን ልቧ አልቻለም... የልቧ ጭንቀት እረፍት ነሳትና ዐይኖቿ በእንባ ተሞልተው «እባክህ ስልክህን ጻፍልኝ?» አለችው፤ የእናት አንጀት አይደል! ስልኩን ተቀበለች። ድህነት አይኑ ይጥፋ ወላሂ! ይሄን ያየው ተሳፋሪ በሙሉ ልቡ ተነካ። ሁሉም ኪሱን ፈትሾ ለነገዋ፣ ለቀጣዩ ቀኗ የታክሲ የሚሆናትን ብር አዋጥቶ ሰጣት። ታክሲው ተነስቶ መንቀሳቀስ ሲጀምር... ያቺ ምስኪን እናት ታክሲው እይታዋ እስኪሰወር ድረስ እዛው ቆማ፣ በልጇ ላይ ያፈጠጠውን የፍቅርና የጭንቀት ዐይኗን ሳትነቅል እያየችን ቀረች። እናት ማለት ይቺ ናት... ለልጇ ትምህርት ስትል ክብሯን ጥላ የምትለምን፣ ራሷ በባዶ እግሯ ቆማ ልጇን ወደ ከፍታ የምትሸኝ! ፈጣሪ ለደጉ ተሳፋሪም፣ ለምስኪኗ እናትም ይድረስላቸው። Via Afi Natilus Ahadu Media አሀዱ ሚዲያ

tesema
tesema
Open In TikTok:
Region: ET
Friday 13 November 2026 01:14:10 GMT
42505
1920
109
298

Music

Download

Comments

meaz525
Meaz🖤 :
እቀፋት ንፁህ ናት 😢😢😢
2026-11-13 06:13:13
28
abay11913
Abay :
ወንድሜ ያለንበት ሁኔታ ከባድ ነዉ, እቺ እናት ዳግም አግኝተህ ብዙ ደጋግ ኢትዮጵያዊ የቻልነው ብንረዳት....
2026-11-13 05:42:42
15
gashu.astatkie
ጋሹ-የደብረ ወርቁ 💪 :
በጠዋት ምን አለ ባታስለቅሱኝ😭😭😭😭😭
2026-11-13 04:12:01
32
baba04xyucovphpj
wegu :
😭አይገባንም እንጂ እናትኮ ሁሉ ነገር ናት ስለናት መከፍት፣ስለናት ማልቀስ ስለናት ሁሉን ነገር መሆን የናትን ዉለታ አይመልስም እንጂ
2026-11-13 09:42:21
1
12marti21
Marti Tsegay🎯🇪🇹🤷‍♀️❥꧁꧂ ꧁꧂ :
🥹🥹🥹🥹🥹🥹🥹
2026-11-13 07:11:26
0
user5691982748125
zed :
እቀፋት ንፁህ ናት እቀፋት ንፁህ ናት 😭😭😭እቀፋት ንፁህ ናት አልኩህ አይደል እንዴ ልጅህ እኮናት ያተ ልጅ 😭😭😭😭😭😭😭
2026-11-13 07:53:08
3
the.hope.of.my.life.is.g
KARAA DEMAA amboo gincii :
be hunet sorry ichi alem 😳😳
2026-11-13 08:28:09
0
tare97.com6
Tare PLC :
Adrashawa yet new Ebakachu Eniridat
2026-11-13 07:08:35
0
crstianye
kb23 :
አሁንስ ሁለተኛ አገር በኖረን ምናለ ፈጣሪ ይቅር በለን ምን ይባላል
2026-11-13 10:07:41
1
tk17710
Wedi keshi man :
እንዴትስ አምኖው ሰጡህ ፈጣሪ ሆይ እሺ አካውንታቸው ፃፍልን የአቅማችንን እናግዛቸው
2026-11-13 05:52:12
10
belete833
አያት :
ይሔን ከምፅፍልኝ ምናል ካንተ ወንበር ላይ ብትገባ የለዕት ብትከፍል ካለሕ አንተ በቀጣይ ብትሄድ 😭😭😭
2026-11-13 05:34:25
8
_habt_habetam
Habtam1921 :
እደኔ ያለቅስ🥰🥰
2026-11-13 06:22:36
13
user8341875444436
user8341875444436 :
እቀፋት ንፁሕ ናት ለንፁሕ አቃፊዎች ብቻ በልብ የሚቆይ መልዕክት
2026-11-13 09:08:37
2
mohamed55359
የሰብ ዘንጋ :
በናታችሁ አለን እንበላ
2026-11-13 09:06:28
2
mekdes33f
Demo :
ለራሴ አልቃሻ ነኝ ስበብ አገኛሁ😥🥺
2026-11-13 09:16:22
1
heganabe
heganabe :
እበክህ አድረሸወን ምተቅ ከሆነ
2026-11-13 06:46:33
4
amsal5916
Amsal :
ጌታ ሆይ እኛ ከማዘንና ከማልቀስ በቀር ምንም አላረን ላትም አንተ ግን ሁሉን ትችላለህ እባክህ ችግሯን አስረሳት 🙏
2026-11-13 09:13:00
0
enu.sisay7
Enu Sisay :
በጠዋት ምን አለ ባታስለቅሱኝ😭😭😭😭😭
2026-11-13 07:01:38
2
awol.sied852
Awol Almuniam wrk :
አሁላይ ከባድ ነው አይዞን ወገኔ
2026-11-13 03:02:48
5
sosina.be
SOSINA (ሙሉ ሸዋ) :
ውይ የኔእናት
2026-11-13 06:56:19
2
gashaw.getu21
የሽሜዋን ተፈፀመ :
አሁን ያለንበት ሁኔታ የብዙዎቻችን እንደዚህ ሁሉም ጥርሱን ነክሶ ባልሞት ባይ ተጋዳይ ነው እየኖረ ያለው ሐገሬ መጨረሻሽ ናፈቀኝ
2026-11-13 07:11:24
3
cruudiii7170
cruuudiii7170 :
አይ ኢትዮጲያ😭
2026-11-13 07:43:29
1
usercvu5j4h4knl
ABICHUU KING♨️♨️♨️♨️♨️♨️✈️ :
2026-11-13 06:26:11
1
mengeshaetyi
fasil mengesha :
የትነው ቦታው
2026-11-13 06:56:28
1
super.man3732
super man :
እጅግ ልብን የሚያንሰፈስፍ አጋጣሚ ነው ወዳጄ የብዙ ወገኖቻቺን ህይዎት ይህ ነው ታሪክ ቢቀየር ፈጣሪ ይርዳን
2026-11-13 05:30:39
1
To see more videos from user @tesemamukura, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About