@kidaneweld4: 📌 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመን ዘንድ «የአርብ ውሃ» (ሳይናገሩና ሳይቀደሙ ማለዳ ከምንጭ የሚቀዳ ውሃ) ለዘመናት የኖረ ጥልቅ እና ውብ የቤት ውስጥ መንፈሳዊ ልማድ ነው። ✍️ እናቶች ይህንን ሥርዓት በታላቅ ጥንቃቄና እምነት የሚፈጽሙት ዝም ብለው ሳይሆን፤ ከመጽሐፍ ቅዱስና ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ጉዞ ጋር የተያያዘ ጥልቅ መንፈሳዊ ሚስጥር ስላለው ነው። ✍️ ጉዳዮ ለምን «የአርብ ውሃ» ተባለ? መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቱ ምንድን ነው? 💎1ኛ. የዕለተ አርብ የውኃና የደም ሚስጥር (የፈውስ ምንጭ)፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ በዋለ ጊዜ፤ ቅዱስ ሥጋው በጦር በተወጋ ቅጽበት ከመለኮታዊ ጎኑ «ደም ውኃ» ፈሰሰ (የዮሐንስ ወንጌል 19፥34)።.......ይህ ውኃ ለዓለም ሁሉ የኃጢአት መታጠቢያ፣ የበረከትና የፈውስ ምንጭ ሆኖ የተሰጠ ነው። እናቶች በአርብ ማለዳ ሳይናገሩ ውኃ ሲቀዱ፣ ያንን በዕለተ አርብ.... ከጌታ ጎን የፈሰሰውንና ለዓለም ፈውስና ሕይወት የሆነውን መለኮታዊ ውኃ በምሳሌነት እያሰቡ በጽኑ እምነት ነው። ✍️ 2ኛ. «ሳይናገሩና ሳይቀደሙ» የመሄዳቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚስጥር...... እናቶች ውኃውን ለመቀዳት ጎህ ሳይቀድ( ፀሐይ ሳትወጣ) ሲነሱ፣ መንገድ ላይ ከሰው ጋር ላለመነጋገርና ላለመቀደም በጥንቃቄና በጭምትነት (በሱባዔ መንፈስ) ይጓዛሉ።...... ይህ ድርጊት ሁለት ታላላቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚስጥራትን ይዟል....... ✍️3ኛ. የክርስቶስን ዝምታና መከራ ማሰብ፦ ጌታችን በዕለተ አርብ ለፍርድ ሲቀርብና መከራ ሲቀበል እንደ በግ አፉን አልከፈተም፤ በዝምታ መከራን ታገሰ (ትንቢተ ኢሳይያስ 53፥7).... ✍️ እናቶችም ይህንን የጌታን የጽሞናና የጭምትነት መከራ በህሊናቸው እያሰቡ፣ በጸሎት ተወስጠው ስለሚሄዱ ከሰው ጋር ምድራዊ (ዓለማዊ) ወሬ አይነጋገሩም። ✍️ 4ኛ. የማለዳው የሴቶች ጉዞ ምስጢር ፦ በትንሣኤው ዕለት ማለዳ ገና ጨለማ ሳለ፤ ቅዱሳት እናቶች (እናቶች) ሽቶና ቅባት ይዘው ወደ መቃብር የገሰገሱበት ሳይቀደሙና ከመንገድ ወሬ ርቀው በልባቸው እያዘኑ ነበር (የሉቃስ ወንጌል 24፥1)። ✍️ የአርብ ማለዳ የውኃ ቅዳትም ይህንን ቅዱስ መንፈሳዊ ቅናትና ፍለጋ ያንጸባርቃል። ✍️5ኛ. ውኃው እንደ ጸበል ሆኖ የመፈወስ ኃይል፦ .....በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር በእምነት ለቀረበለት ነገር በግዑዛን ፍጥረታት ላይ ኃይሉንና በረከቱን ያሳርፋል። 💎 ለምሳሌ፦ የኤልሳዕ ጨው ውኃውን እንደፈወሰው (2ኛ ነገሥት 2፥21)... ወይም የጌታን ልብስ የዳሰሰችው ሴት በእምነቷ እንደዳነችው (የማቴዎስ ወንጌል 9፥22).....እናቶችም በዕለተ አርብ በሚያደርጉት ንጽሕና፣ ልባዊ ጸሎትና ጽኑ እምነት ምክንያት ያ!...ውኃ የእግዚአብሔር በረከት ይርፍበትና ልጆች ሲታመሙ ወይም ክፉ መንፈስ ሲያስቸግራቸው የሚረጭ፣ የሚጠጣ የፈውስ መሣሪያ (እንደ ጸበል) ይሆናል። 💎 ማጠቃለያ ፦ «የአርብ ውሃ» እናቶች ከቤተክርስቲያን ሥርዓት ተካፍለው ጸበል ማግኘት በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ እነሰኳ ሳይቀር፣ በቤታቸው ውስጥ ሆነው የክርስቶስን ስቅለትና የመስቀል ላይ በረከት በእምነት የሚሳተፉበት፣ ቤታቸውን ከክፉ ነገር የሚጠብቁበት ጥልቅና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው ውብ ክርስቲያናዊ ባህል ነው። ✍️ ዲ/ን ኪዳነ ወልድ

ዲ/ን ኪዳነ ወልድ
ዲ/ን ኪዳነ ወልድ
Open In TikTok:
Region: ET
Friday 13 November 2026 08:27:46 GMT
17435
1185
83
253

Music

Download

Comments

2kina7
ኪና❤️🙏 :
ይሔን መልእክት ለአቡነ ኤርሚያስ ንገራቸው በአል ማክበር የለም የአርብ ውሃ የሚባል የለም ላሉት ጥሩ መልእክት ነው ከቻልክ ከንግግራቸው ጋር አታች አድርገህ ብትፖስተው 🙏 ለምን ምእመኑ አንተ ከጻፍከው ይልቅ እውነት የሚመስላቸው የሳቸው ንግግር ነው
2026-11-14 04:38:38
6
ejige0
ejige :
ለፊተኛ እናቶቻችን ክብር ይሁን ሳያነቡ ላመኑቱ አሁንም የሚያኖረን የነሱ ፍፁም መታመን ነው🙏
2026-11-13 13:16:50
16
ethio.talk
Ethio talk :
እናቶችን ግን ይሄን ሁሉ ሚስጥር የትኛው ሰባኪ መምህር ነግሯቸው ነው ይህን ስጋና ደም በእውነት አልገለጠላቸው የሰማይ አባቴ እንጂ እንዳለ ክርስቶስ ልዮ ናቸው የቀደሙት🥰🙏
2026-11-13 12:06:42
6
hiwoteatamiru
Emnet Belete :
እምነት በነሱ ግዜ ቀረ ሃይማኖት ከምግባር በእውነት
2026-11-13 13:32:43
4
denk559
denk559 :
እኔ ግን እናቴ ነፍሱዋን በአፀደ ገነት ያኑራትና የአርብውሐ ቡና በሰንበት አይቆላም አይወቀጥም እኔም እደሰዋ ትርጉሙን ሳላውቅ አሁንም የአርብ ውሐ እቀዳለሁ ተባረክ ቃለሕይወት ያሰማልን
2026-11-13 12:12:34
5
ema9328596199413
yesemaeta,lj :
ቃለህይወት ያሰማልን 🥰🥰🥰
2026-11-17 13:18:36
2
girum.beyene1
Girum Beyene :
ቤታችን ከልጅነት ጀምሮ ይቀዴል ሚስጢሩ ግንአልገባኝም እደዚህ በዝርዝር አሁንም ባለቤቴ ነቤቶቼን ይዛ ይቀዳል ያለውን ጠቀሜታ አስረዳለሁ አመሠግናለሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
2026-11-13 12:33:04
4
debebe.tafa
Debebe Tafa :
ቃለ ህይወት ያሰማልን
2026-11-15 10:11:59
2
mebtu391
mebtu :
እምነት በናቶቻችን
2026-11-13 23:19:53
4
yaleletmisganaw
yalelet :
ችግሩ የቀደሙት አያቶቻችን ብዙ ምስጢራትን ደብቀውብን ነው የሔዱት
2026-11-13 15:50:41
5
yizuachewzeleke29
Yizuachew Zeleke :
እውቀቱን አብዝቶ ይስጥልን።ፀጋውን ይደለን
2026-11-17 04:24:12
2
awaju23
AWAJU KEFYALEW :
🙏ተባረክ ቃለ ህይወት ያሰማልን🙏
2026-11-15 01:10:13
1
reyot.abi.1229
እውነቱ የት አለ Reyot1229 :
ቃለ ህይወትን ያሰማልን
2026-11-17 12:39:23
1
newxd69
its me hilu :
amen amilak yirdan
2026-11-17 14:15:58
2
tigistmekonnen96
tigistmekonnen96 :
እግዚአብሔር አብዝቶ ይስጥልን!!!
2026-11-17 19:29:43
1
user230275744
Kiya :
ቃለህይወት ያሰማልን
2026-11-14 07:06:32
1
etate528
etate :
ተባረክ
2026-11-15 17:48:56
1
abushe12246
abush ye ቅ/ሚካኤል☦️🤍 :
berta
2026-11-14 21:49:58
1
yeginbie.mekete
Yeginbie Mekete :
ቃለህይወት ያሰማልን በትክክል እኔም ሳድግ የአርብ ውኃ እየቀዳሁ ነው ምስጢሩን ግን አላውቀውም ነበር እግዚአብሔር ይባርክህ
2026-11-13 16:27:21
3
bqts58
🖤ÄB💣qúötës🔥🔥⚡ :
አይገርምም አላቅም ነበር ሚስጥሩን ጥልቅ ነው በቀደም አንድ አባት የኦሪት ልማድ ነው ይሄ ተው ሲሉ ሰምቸ ደስ አላለኝም ነበር ሚስጥሩን በማወቄ ተደስቻለሁ አመሰግናለሁ ስላካፈልከን ከምታቀው
2026-11-17 12:10:07
1
metekutsige
Meteku Tsige :
እግዚአብሔር ይስጥልን የህይወት ቃል ያሰማልን ያበርታህ።
2026-11-16 18:18:18
1
user9785496035803
shisema fikre የሚካኤል ነኝ :
ቃለ ሔወት ያሰማልን
2026-11-13 14:55:13
2
girmanissan
girmanissan :
ቃለህይወትያሠማልን!!!
2026-11-13 12:28:22
2
user9062184236016
የስላሴ ባርያ :
ትክክል ነው ወላጅ እናቴ አጥብቃ የአርብ ውሀን ከሰንበት ውሀ ጋር እንዳይቀለቀል ትጠነቀቅ ነበር።
2026-11-14 10:42:01
2
sisay2544
sisay :
ቃለ ህይወት ያሰማልን
2026-11-13 18:39:46
3
To see more videos from user @kidaneweld4, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About