@tusbaxle0988:

إِبْنُ سَيْدَ 👳🏾‍♂️🪼
إِبْنُ سَيْدَ 👳🏾‍♂️🪼
Open In TikTok:
Region: SO
Saturday 14 November 2026 09:15:37 GMT
453
61
1
31

Music

Download

Comments

ayaan.ahmed.abdi6
اتق الله :
[Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming]
2026-11-14 16:53:43
0
To see more videos from user @tusbaxle0988, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

የቤተ ክርስቲያን ክፍሎችና ትርጓሜያቸው ቤተ ክርስቲያን ሦስቱ ክፍሎች ያሏት ሲሆን እነዚህም ቅኔ ማኅሌት፣ ቅድስትና መቅደስ በመባልም ይታወቃሉ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ክፍሎች (ክፍሎቿም) ጎልተው የሚታዩት በክብ ቅርጽ በታነፀ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው፡፡  የቤተ ክርስቲያን ክፍሎችም ሦስት የሆኑበት ምክንያት አንደኛው በሦስቱ ዓለማተ መላእክት ማለትም በኢዮር፣በራማ፣በኤረር ምሳሌ መሆኑ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ በሦስቱ መዓረጋት (ክህነት) ዲቁና፣ቅስና፣ኤጲስቆጶሳት ምሳሌ ሲሆን በሦስቱ ጾታ ምእመናን፡ ማለትም ካህናት፣ ወንዶች፣ ሴቶች የሦስቱ ኆኅተ ገነት (የገነት በሮች) ምሳሌም በመሆኑ ነው፡፡ አገልግሎታቸው ፩. ቅኔ ማኅሌት በዚህ ክፍል ውስጥ መዘምራን፣ ደባትር ካህናት ማኅሌተ እግዚአብሔር ያደርሱበታል፡፡ በመስዕ (ሰሜን ምሥራቅ) ንዑሰ ማዕዘን በኩል ቀሳውስትና ዲያቆናት በመንፈቀ ሌሊት ሰዓታት፤ በነግህ ኪዳን ያደርሱበታል።  ለጥምቀት፣ ለቊርባን ያልበቁ በትምህርት በንስሓ የሚፈተኑ /ንዑሰ ክርስቲያን/
የቤተ ክርስቲያን ክፍሎችና ትርጓሜያቸው ቤተ ክርስቲያን ሦስቱ ክፍሎች ያሏት ሲሆን እነዚህም ቅኔ ማኅሌት፣ ቅድስትና መቅደስ በመባልም ይታወቃሉ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ክፍሎች (ክፍሎቿም) ጎልተው የሚታዩት በክብ ቅርጽ በታነፀ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ክፍሎችም ሦስት የሆኑበት ምክንያት አንደኛው በሦስቱ ዓለማተ መላእክት ማለትም በኢዮር፣በራማ፣በኤረር ምሳሌ መሆኑ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ በሦስቱ መዓረጋት (ክህነት) ዲቁና፣ቅስና፣ኤጲስቆጶሳት ምሳሌ ሲሆን በሦስቱ ጾታ ምእመናን፡ ማለትም ካህናት፣ ወንዶች፣ ሴቶች የሦስቱ ኆኅተ ገነት (የገነት በሮች) ምሳሌም በመሆኑ ነው፡፡ አገልግሎታቸው ፩. ቅኔ ማኅሌት በዚህ ክፍል ውስጥ መዘምራን፣ ደባትር ካህናት ማኅሌተ እግዚአብሔር ያደርሱበታል፡፡ በመስዕ (ሰሜን ምሥራቅ) ንዑሰ ማዕዘን በኩል ቀሳውስትና ዲያቆናት በመንፈቀ ሌሊት ሰዓታት፤ በነግህ ኪዳን ያደርሱበታል። ለጥምቀት፣ ለቊርባን ያልበቁ በትምህርት በንስሓ የሚፈተኑ /ንዑሰ ክርስቲያን/ "ፃኡ ንዑሰ ክርስቲያን" እስከሚባል ድረስ የሚቆዩበት ክፍልም ነው፤ ወንዶች ምእመናንም ቆመው ያስቀድሱበታል። በሌብ /ደቡብ ምሥራቅ/ ንዑስ ማእዘን በኩል የሚገኘው ቦታ የሴቶች መቆሚያ ነው፡፡ ከውጭ ወደ ቤተ መቅደስ ስንገባ የምናገኘው የመጀመሪያው ክፍል ሲሆን ሦስት በሮችም አሉት፤ የካህናት፣ የወንዶችና የሴቶች ምእመናት መግቢያዎች ናቸው፡፡ ፪.ቅድስት የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማእከላዊ ክፍል ቅድስት ይባላል፡፡ ካህናት በድርገት ጊዜ ምእመናንን የሚያቆርቡበት ክፍል ሲሆን በስብከተ ወንጌል ጊዜም መምህራን ቆመው ያስተምሩበታል፡፡ በተክሊልና በቊርባን አንድ ለሚሆኑ ሙሽሮች ጸሎት የሚደርስበትና በካህናት እጅ የሚባረኩበት በዚህ ክፍል ውስጥ ነው፡፡ በስቅለት ዕለት ሥርዓተ ጸሎት ይፈጸምበታል፤ በምዕራብ በኩል ቆሞሳት፣ ዲያቆናት፣ ቀሳውስት ይቆሙበታል፤ በሰሜን መነኮሳትና የሚቈርቡ ወንዶች ምእመናን ይቆሙበታል፤ በደቡብ የሚቆሙት ደናግል መነኮሳይያት፣ የቀሳውስትና የዲያቆናት ሚስቶች ናቸው፤ በምሥራቅ በምዕራብ በሰሜንና በደቡብ ዐራት በሮች ይኖሩታል፤ ነገር ግን የማይቆርቡ ምእመናን በዚህ ክፍል ቆመው አያስቀድሱም፡፡ ፫.መቅደስ በብሉይ ኪዳን ቅድስተ ቅዱሳን በሚል ስያሜ ይጠራ የነበረው የቃል ኪዳኑ ታቦት የሚገኝበት ክፍል መቅደስ ነው፡፡ ንዋያተ ቅድሳትም ከመንበረ ታቦቱ ጋር በዚህ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በምዕራብ በሰሜንና በደቡብ ሦስት በሮች ሲኖሩት እያንዳንዱ በር በመንጦላዕት ወይም በመጋረጃ የሚጋረድ ነው፡፡ ከዲያቆናትና ሥልጣነ ክህነት ካላቸው በቀር ወደ መቅደሱ ማንም መግባት አይችልም፡፡ ##ንዋያተ_ቅዱሳት #ቤተክርስቲያን #የቤተክርስቲያን_ክፍሎች #ጉልላት #ካህናት @MomTok @Dawit Gobena @Tibebe yiheyis @eyasu waltengues @የጉለሌ አምባ ኪዳነ ምህረት ወቅድስት አርሴማዋሻ @Eden Israel @Ermi_art

About