@rhrabbi70:

🇧🇩R……🇸🇦
🇧🇩R……🇸🇦
Open In TikTok:
Region: SA
Saturday 14 November 2026 20:46:37 GMT
0
0
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @rhrabbi70, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


"የዓይኔ ተስፋ"🫶☺️ ✨አንጋፋው ምኒልክ ወስናቸው ረቡዕ ታህሳስ 15 ቀን 2001 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከንጋቱ አስራ አንድ ሰዓት ተኩል ላይ ነበር በ68 ዓመታቸው ይቺን ዓለም በቃኝ ብለው ለመጨረሻ ገዜ የተሰናበቱት ከ 17 ዓመት በፊት መሆኑ ነው 🙏🥺 ጋሽ ጀምበሬ በሚል ቅጥል ስም የምንጠራቸው በአዘፋፈን ዘያቸውም ይሆን በሙዚቃ ስታይላቸው ምን አልባት ከበርካታ አንጋፎች ወጣ ያሉት ተወዳጁ ምኒልክ ወስናቸው በኛ በወጣቱም ዘንድ ሳይቀር እጅግ ተወዳጅ ሙዚቃዎችን ያስደመጡን ምን አልባት ብዙዎቻችን ባናውቅም ግሩም ገጣሚም የነበሩ ለነጥላሁን አይንት ሙዚቀኞች ግጥም የሰጡ ታላቅ የሙዚቃ ሰው ነበሩ 🥰🙏 ውድ ቤተሰቦቼ ታዲያ እኚን ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ደጋግመው ስሟን ያስጠሩ በመድረክ አያያዛቸው ብዙዎችን እጅን በአፋ ያስጫኑ ታላቅ የሙዚቃ ሰው በድጋሚ ስራዎቻቸውን በ1988 በነ አበጋዙ ፋሲል ዎሂብ ቴዎድሮስ መኮንን አለምሰግድ አይነት ታላላቅ የሙዚቃ ሰዎች ጋር በመሆን ካሳተሙት አይረሴው አልበም "ጋሽ ጀምበሬ" አልበም ላይ እጅግ የምወደውን "የዓይኔ ተስፋ"ን ጋብዤያቹ እግረ መንገዴን እኚን ታላቅ የሙዚቃ ሰው እንድንዘክራቸው እንዳከበራቸው ላወሳቸው ወደድኩኝ🥰 አዲስ አበባ ተወልደው ሀረር ያደጉት ምኒልክ ወስናቸው የሙዚቃ ጅማሬያቸው በ1951 ዓ.ም በተቀጠረበት ዝነኛው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቴያትር ኦርኬስትራ ነበር። በዛም ብዙ ምርጥ ዘፈኖችን ተጫውተው ነበር – እነ “ፍቅር በአስተርጓሚ”፣ “ፍቅር አያረጅም”፣ “ስኳር ስኳር” እና የመሳሰሉትን። ከዛም በ1957 ዓ.ም. አካባቢ በግርማ በየነ አማካኝነት በተቋቋመው ሁለተኛው የ“ራስ ባንድ” ተብሎ የሚታወቀውና የራስ ሆቴል ባንድ ውስጥ ከእነ ግርማ በየነ፣ ተስፋማሪያም ኪዳኔ፣ ኃይሉ (ዝሆን) ከበደ፣ ግርማ ዘማሪያም እና ሠይፉ ዮሐንስ ጋር የሙዚቃ ቡድኑ አባል በመሆን እንደተካቱ ይታወቃል። “አምሃ ሪከርድስ” የተሰኘው የሙዚቃ አሣታሚ ድርጅት “መቃብሬን ልየው” የሚለውን የምኒልክን ሸክላ እንዳሳተመ ስለእሳቸው የተፃፉ መዛግብት ይጠቁማሉ። የዚህ አልበም የሙዚቃ አቀናባሪ ታዋቂው የሙዚቃ ባለሙያ ሙላቱ አስታጥቄ እንደነበረም መረጃዎች ይጠቁማሉ። ድምፃዊ ምኒልክ ወስናቸው ከዘፈናቸውና በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተደናቂነትን ካተረፉለት ውስጥ “ትዝታ አያረጅም”፣ “ጋሽ ጀምበሬ”፣ “ፍቅር ባስተርጓሚ”፣ “ስኳር ስኳር”፣ “እንገናኛለን”፣ “ፍቅር አያረጅም”፣ “አደረች አራዳ”፣ ... የሚሉት ከብዙ በጥቂቱ ናቸው። በተጨማሪም በሱዳንኛም ይዘፍኑ እንደነበር ይታወሳል። አንጋፋው ምኒልክ ወስናቸው የአራት ልጆች አባት ነበሩ፣ አብዮቱ የፈነዳ አካባቢ ለስደት ተዳርገውም ነበር። ታዲያ በሱዳንና በአሜሪካን ሀገር ለ22 ዓመታት በስደት ሲኖር ቆይተው ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ከ12 ዓመት በላይ ቆይተው እትብታቸው በተቀበረችበት ኢትዮጵያ ለመቀበር በቅተዋል። እኛም ታዲያ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እየተመኘን ነፍስ ይማር ብለናል 🙏🙏 በህይወት ሳሉም ላበረከቱልን እጅግ ተወዳጅ ሙዚቃዎች እመስግነን 🙌🥰 በሌላ የሙዚቀኞች ዳሰሳ እስግንገናኝ ለዛሬ አበቃን🙏 ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡🙌 @musictube 🇪🇹 #fyp #ምኒልክወስናቸው #የዓይኔተስፋ #musictube369 #ethiopianmusic

About