@2mmmmmw: #የዓመቱ ምርጡ ትወና ይህ ትወና የሆሊውድ አክተሮችን ያስንቃል ። ነገሩ ወዲህ ነው ። አዲሱ የተላላው አለቃ የአሜሪካ ብሄራዊ ቡድንን በስንብት መግለጫው እየተሰናበተ ነው ። እናም ፖች እንደ ማልቀስ ቃጣው ። አለቀሰም ። ከባድ የኬሪየሩ ውሳኔ እንደሆነም አሳወቀ ። እኔ ስሜታዊ ነኝ አለ ። በዛው በሀዘን ድባብ ማልቀሱንም ቀጠለ ። ነገሩ ለአሰልጣኝ ፖቸቲኖ እስካሁን ካሳለፈው በላይ ቀጣይ የሚጠብቀው መከራ ሆዱን ያባባው ይመስላል ። ጥያቄ መሆን ያለበትም አሰልጣኝ ፖቸቲኖ ምን የተለየ ስሜት የሚነካ ነገር ሰርቶ ነው እንዲህ በአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን ሽኝቱ ወቅት የሚያስለቅሰው ነው ። የፖች በእንባ የታጀበ ስሜታዊነትን ላየ አዲሱ የተላላው አለቃ እንደ ሊዮኔል ስካሎኒ በአርጀንቲና የአለም ዋንጫን በማይረሳ ስሜት ኮርኳሪ ውጣ ውረድ አሸንፎ ከብሄራዊ ቡድኑ ወርቃማ አይረሴ ገጠመኙ ፈፅሞ መለየት የተሳነው ብሄራዊ ጀግና ይመስላል ። ዕውነታው ግን ሲገለጥ ይህ አይደለም ። አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ዩናይትድ ካሪክን ካባረረ ማግስት እንደሚፈልገው ሲያውቅ ከአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን ለመለየት እራሴ ካሳ ጭምር ከፍዮ ካልወጣሁ ከሰሞኑ እንዳላለ አሁን በዚህ ልክ የሚያስነባው ምን የተለየ IMOTIONAL ATTACHMENT ከአሜሪካዊያን ጋር ፈጥሮ ነው የምር ያስብላል ። አብዛኞቹ አሜሪካዊያን አሁንም ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ የሀገራቸው ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ እንደነበር ጠንቅቀው አያውቁም ። በቆይታውም አሰልጣኙ የተለየ ለአሜሪካዊያን ያመጣው ውጤት የለም ። የአርጀንቲናዊ አሰልጣኝ በእንባ የታጀበ የUSA ስንብት አለቃቀስ ታዲያ የሆሊውድ ድንቆችን የሚያስከነዳ የPoch Cry opera የአመቱ ምርጡ ትወና ነው ። ፓች በዚህ የተዋጣለት የትወና ችሎታው እልፍ ነሆለል ኮሜዲዎች የወረሩት ክለብን ተቀላቅሎ በቀጣይ ደግሞ ምን ሊያሳየን ያስብላልም ? በርግጥም የቀድሞዎ የቶተንሃም እና ቼልሲ አለቃ ማንቸስተር ዩናይትድን የማሰልጠን ህልሙ ተሳክቷል ። ከሰውየው ጡረታ በኋላ ወደ ተላላው ዩናይትድ የመጡት መልሰው የተባረሩ አሰልጣኞች ሁሉ ገና ኦልድትራፎርድን እንደረገጡ የተናዘዙት ህልሜ ዕውን ሆነ My Dream come true ገጠመኝ አሁን የፖቸቲኖ ተራ ሆኗል ። ቲያትሩም ገና ከቲያትሩ ዓለም ይቀጥላል ። ዕዚህ ላይ ከቀልቡ ሆኖ ማሰብ ማሰላሰል ለሚችል ልባም ሰው መቅረብ ያለበት አንድ ቁልፍ ጥያቄ በመጨረሻ ታዲያ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ከአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን መለየቱ ነው ? ወይስ ማንቸስተር ዩናይትድን ለመቀላቀል መወሰኑ ነው ? በዚህ ልክ በእንባ የታጀበ ስሜታዊ ያደረገው ? በርግጥም ፖች በአሜሪካ ካሳለፈው የምቾት ግዜ በላይ ለቀጣዩ የመከራ የፈተና የጫና ዘመኑ በሰፊው የሚያነባበት የእዬዬ ግዜ ስላላው ምን አስቸኮለው ከወዲሁ እንባውን ቢቆጥብ መልካም ነበር '' የበርካቶች ሀሳብ ነው ።
Sports 999 News🥅⛹🏽♂️
Region: ET
Sunday 15 November 2026 09:54:55 GMT
Music
Download
Comments
መከረኛዋ ኢትዮጵያ :
በእውነት ነው የምለው ምርጥ ጋዜጠኛ ነህ🤔🤔🤔🤔🤔🤔
2026-11-15 12:01:45
0
MINILIK || NOW :
የምን ባላንስ ነው ቀጥል
2026-11-15 11:51:51
0
Dawit :
ኤፍታ ቀጥል የፈለገ መስማት አለመስማትም መብት ነው 🙏🙏🙏
2026-11-15 11:11:58
0
workineh basilel :
jegina
2026-11-15 10:56:10
0
መ :
👌👌👌👌👌👌
2026-11-15 11:45:38
0
To see more videos from user @2mmmmmw, please go to the Tikwm
homepage.