@userecmajme710: ጫማ ሰፊው እና ልጆቹ ‎ቤተክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከምትዘክራቸው መካከል ጫማ ሰፊው ስምዖን ነው ። ‎ታሪክ እንደሚነግረን ስምዖን ጫማ በመስፋት ራሱን የሚያስተዳድር በትርፋቱም ለሽማግሌዎች ውሃ የሚየመላልስላቸው በሥራው የከበረ ትጉ ሰው ነው ። ‎በዘመኑ የነበረው ሊቀ ጳጳሳት አባ አብርሃም በወንጌል « የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ። ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር።" ሉቃ 17:6 ተብሎ የተጻፈውን ‎አድርገህ አሳየን ተብሎ በተጠየቀበት ወቅት በጫማ ሰፊው ስምዖን ምክንያት ይሄ ድንቅ ተአምር ተደርጎለታል ። ‎ ‎ይሄውም ተራራውን እንደ መሶብ አንስተው የወንጌልን እውነት የገለጡ አበው ናቸው ። ‎ስምዖን በሥራው ጫማ ሰፊ ቢሆንም በእምነቱ ግን ተራራ ያፈለሰ ነበር ። ለዚህም ነው እምነትን በሥራ ብዛት እና በጥሩ አለባበስ .. መለካት ተገቢ የማይሆነው ። ‎ ‎የጫማ ሰፊው ልጆችም የልቡናቸውን ጫማ በአባታቸው የጸና እምነት ልዩነታቸውን ሁሉ ሰፍተው ርስ በእርስ መለያየት ሳይኖርባቸው የአባታቸውን ገዳም በክብር ጠብቀው በማኖራቸው ከከበረው ዐፅሙ አምኖ የመጣው ሁሉ እየተባረከ ይገኛል ። ገዳማቸውን በሁለተናዊ ዘርፍ ‎የሚንከባከቡበትን መንገድ ለሚያይ ሁሉ እውነትም የጫማ ሰፊው ልጆች መሆናቸውን ሥራቸው ይናገራል ። ‎ ‎ የቅዱሱ በረከት ይድረሰን ነቢየ ልዑል አዳሙ ሕዳር 4/03/2019 ዓ.ም ካይሮ -ግብጽ

☦️አነ ዘክርስቶስ☦️
☦️አነ ዘክርስቶስ☦️
Open In TikTok:
Region: SA
Monday 16 November 2026 04:54:47 GMT
1437
229
0
66

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @userecmajme710, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About