@mihlaamana5: ብድር የሃብት ምስጢር መሆኑን ታውቃለህ ብድር የሃብት ምስጢር ከሆነ ለምን ድሮ ስንማር ትምህርት ቤት ውስጥ አላስተማሩንም? መልሱ ያስደነግጣል፡፡ ምክንያቱም ብድር/ዕዳ በትክክል እንዴት እንደሚሰራ በተረዳችሁ ቅጽበት፣ ከፍተኛ ግብር ከፋይ መሆናችሁ ያበቃል።መቀጠርን እምቢ ትላላችሁ፡፡እናንተ አልቀጠርም ካላችሁ ባለሃብቶች እና ድርጅቶች ማንን ቀጥረው ያሰሩ?ትምህርት ቤቶች የሚያዘጋጁህ እንዴት ተቀጥረህ እንደምትሰራ ፤እድሜ ልክህን እንዴት ለገንዘብ እንደምትሰራ  እንጅ እንዴት እንደምትነግድ ወይም ገንዘብ ራሱ ለአንተ እንዴት እንደሚሰራ አይደለም፡፡ አብዛኛው ሰው ብድርን/ዕዳን እንዲፈራ ነው የሰለጠነው።ሀብታሞች ግን እንዲጠቀሙበት ነው የሰለጠኑት። ለምን እንደሆነ ላስረዳህ። ገንዘብ ስትበደር፣ አንድ ሳንቲም እንኳን ታክስ አትከፍልም ለምን? ምክንያቱም መንግሥት የተበደርከውን ገንዘብ እንደ "ገቢ" አይቆጥረውም።ታክስ አይጣልበትም። ቅጣትም የለበትም። ትምህርት ቤት ውስጥ ፈጽሞ የማንማረው ነገር ይሄ ነው ፡፡ ብድር/ዕዳ ማለት በትክክለኛው ትርጉሙ ገንዘብ እንዴት እንደሚፈጠር የሚያሳይ ቁልፍ ነው። ባንክ በየጊዜው ገንዘብ በሚያበድርበት ጊዜ፣ አዲስ ገንዘብ ወደ ሥርዓቱ ይገባል። ለዚህ ነው ባንኮች ተበዳሪዎችን በጣም የሚወዱት። ዕዳ /ብድር ሥርዓቱ እንዲያድግ ይረዳል።አሁን የሚገርመው ክፍል እዚህ ላይ ነው... ገንዘብ ስትበደር፣ ለጥሬ ገንዘብ ፍሰት (Cash Flow) መገንቢያ ትጠቀምበታለህ፡፡ እንዴት እንደሆነ ላሳይህ ፡፡ከታክስ ነጻ የሆነ ብዙ ገንዘብ ተበደር እና በገንዘቡ  ወርሃዊ ገቢ ሚያስገኝ ንብረት ግዛበት፡፡ ከዚያ ንብረቱ በየወሩ ጥሬ ገንዘብ እንዲያመጣ አድርግ፡፡ዕዳውን ለመክፈል በየወሩ የምታገኘውን ጥሬ ገንዘብ ተጠቀም፡፡ አየህ ያልተቋረጠ ወርሃዊ ገቢ የሚያመጣልህ አንድ መሳሪያ አገኘህ ማለት ነው፡፡ ገንዘብ ለአንተ ይሰራል ማለት ይህ ነው፡፡በቃ የገዛኸው ንብረት እራሱ ለገንዘብ ይሰራልሃል እንጅ አንተ ለገንዘብ አትሰራም፡፡ ከአንተ የሚጠበቀው ትክክለኛ ብድር መውሰድ ነው፡፡ እውነተኛ እሴት ለመፍጠር ባለሀብቶች ዕዳ /ብድር በብዛት ይጠቀማሉ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ የፋይናንስ እውቀት የሌላቸው ሰዎች እዳን/ብድርን የሚጠቀሙት የበለጠ ደሃ ለመሆን ነው፡፡ አብዛኛው የፋይናንስ እውቀት የሌለው  ሰው ዕዳን የሚጠቀመው መኪና ለመግዛት፤ለመዝናኛ፡ለሰርግ፤ለሌሎች ድግሶች ፤ለፍጆታ ዕቃዎች፤አቅም የማይፈቅድላቸውን እና ምንም ገቢ የማያስገኙ  ትልልቅ ቤቶችን ለመግዛት በአጠቃላይ ገቢ ከማስገኘት ይልቅ ገንዘብ ከኪስ የሚያስወጡ ነገሮችን ለመግዛት ይጠቀሙበታል፡፡ ለምሳሌ እኔ የማውቃቸው ብዙ ሰዎች ተበድረው ሰርግ የደገሱ አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች እድሜ ልካቸውን ብድር ሲከፍሉ ከመኖር ውጭ ምንም አማራጭ የላቸውም፡፡ይህ የፋይናንስ ትምህርት እጥረት ችግር ነው። ታዲያ ትምህርት ቤቶች ለምን ይህን አያስተምሩም? በጣም ቀላል ነው፡፡ትምህርት ቤቶች የተነደፉት ሠራተኞችን ለመፍጠር እንጂ ባለሀብቶችን ለመፍጠር አይደለም። ሠራተኞች ለገንዘብ ይሠራሉ።ባለሀብቶች ገንዘብ ለእነሱ እንዲሠራ ያደርጋሉ። ሠራተኞች ከፍተኛውን ታክስ ይከፍላሉ።ባለሀብቶች ዝቅተኛውን ይከፍላሉ። ትምህርት ቤቶች ዕዳ/ብድር  እንዴት እንደሚሠራ አስተምረው ቢሆን ኖሮ ሰው ብድርን/ዕዳን አይፈራም ነበር። በደሞዝ ላይ ጥገኛ አይሆንም ነበር። የውሸት ገንዘብ አያጠራቅምም ነበር። ለመንግሥት ብቻ በሚመች ስሥርዓት ውስጥ አይቆይም ነበር። ድሆች ይበደራሉ፤ ይበልጥ ይደኸያሉ።ሀብታሞች ይበደራሉ ፤ ይበልጥ ይበለጽጋሉ። ችግሩ ዕዳው አይደለም።ችግሩ በዕዳው የምትገዙት ነገር ነው። ስለዚህ የፋይናንስ ነፃነት ከፈለጉ ከዚህ በኋላ "ብድር ጥሩ ነው ወይስ መጥፎ?" ብለው መጠየቅ ያቁሙ። ይልቁንስ ይህን ይጠይቁ፦"ይህ ዕዳ ወደ ኪሴ ገንዘብ ይጨምራል ወይስ ከኪሴ ያወጣል?" ይህ አንድ ጥያቄ ድሆችን ከሀብታሞች ይለያል።ትምህርት ቤቶች ይህን ፈጽሞ የማያስተምሩት ለዚህ ነው። አንድ ነገር አስታውስ ይህ ሁሉ በዙሪያህ ያለው ባለሃብት ሃብታም የሆነው በራሱ ገንዘብ እንዳይመስልህ፡፡በብድር ነው፡፡ነገር ግን ብድሩን ከወሰደ በኋላ የተበደረውን እጥፍ በአጭር ጊዜ የሚያመጣለት ቢዝነስ ላይ ኢንቨስት ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ምትበደር ከሆነ በጭራሽ ለወጭ መሸፈኛ ብለህ እንዳትበደር፡፡ለቢዝነስ እና ለኢንቨስትመንት እንጅ   በል ፎሎው አድርግ

DUNYA
DUNYA
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 16 November 2026 13:27:31 GMT
27353
1122
49
373

Music

Download

Comments

fanos.achamo
Fanos Achamo :
ምርጥ ምክር + ታላቅ ትምህርት! በአብዛኛው ሕዝብ ዘንድ የተሰወረውን ገለጥክ👍
2026-11-19 12:18:53
2
elias.hassen.ali
1 2 3 4 5 :
exactly
2026-11-18 11:02:24
0
user7842442654165
ጀማል መሀመድ :
እውነት
2026-11-17 11:16:51
6
tesfaya.amaha
Tesfaya Amaha :
ትክክል ብለሀል ወንድሜ።
2026-11-17 11:51:34
4
kelela.chala
Kelela Chala :
IT is good idea.$$$$$$$$$$$
2026-11-17 18:34:38
2
yibelnuy0uk
satori :
መምህሮች አያውቁትም
2026-11-18 02:10:33
1
lewi.man1
lewi man :
waw yamir good advice
2026-11-19 17:00:21
0
ashrak.hamdegba
Ashrak Hamdegba :
thats true good
2026-11-17 14:04:27
1
user8508573965853
user8508573965853 :
you have made a good assessment to all government worker. bless you!
2026-11-19 12:02:26
0
tigest.neguse15
Tigest Neguse :
The schools was teach us.
2026-11-19 14:12:59
0
ademriskey1
@$& ris :
አቦ ተመቸሀኝ
2026-11-18 17:33:22
0
user2820675662073
user2820675662073 :
ድህነትን መገንባት ማለትነው
2026-11-17 12:45:41
0
gg360772
gg :
እውነት
2026-11-17 17:55:51
1
hussen.heiru
Hussen Heiru :
በትክክል ብለሀል
2026-11-19 06:18:36
0
mahamud.yasin8
Mahamud Yasin :
Thankyou
2026-11-19 15:29:49
0
gerezgihertesfay8
ገረዝግሄር :
you are all right
2026-11-18 19:42:06
0
yared.marketing
Yared Media and production :
Great !
2026-11-18 18:37:57
0
zelalemshimelis
zoltec :
2026-11-17 20:11:17
1
ngusu.mulgeta
Ngusu Mulgeta :
wow🥰🥰የሚገርም ትምህርት
2026-11-18 16:05:38
0
kedir1178
kedir እጣን :
ዋው
2026-11-18 16:21:23
0
lightstar770
LIGHT STAR⭐✨✨ :
Lembeder erasu birr yasfelgal zemibelo birr yemseti bank yelem!
2026-11-19 22:27:45
0
ahamad5210
Ahamad. :
recpeckt
2026-11-19 20:50:37
0
wondye.girma00
Wondye Girma :
Thank you.
2026-11-18 16:21:53
0
jemanesh.hailu
Jemanesh Hailu :
wowwww
2026-11-18 17:26:07
0
shemsu.nasir94
shemsu nasir :
ዉሸት
2026-11-17 18:05:21
0
To see more videos from user @mihlaamana5, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About