@eyoba6430: ይህ ሁለት የወንጌል ክፍል የመበለቲቱ መባ እና የኢየሱስ ስልጣን መጠየቅ በተለይ በሰሞነ ህማማት በእለት ማክሰኞ በስፋት ይነበባል,ይተረጎማል,ይዘመራል. በቤተክርስቲያናችን ትርጓሜም:-ስለ ደሀዋ መበለት መባ ሉቃ ፳፩÷፩-፬ ማር ፲፪ ÷፵፩ -፵፬ ኢየሱስ በቤተመቅደስ ሳለ ባለፀጎች ብዙ ገንዘብ ሲሰጡና አንዲት ደሀ መበለት ደግሞ ሁለት ሳንቲም ስትሰጥ አይቶ የተናገረው ነው. የልብ ፍቅር እና መስዋትነት:-እግዚአብሔር የሚመለከተው የስጦታ መብዛት ሳይሆን የሰጪውን ልብና እምነት ነው.ባለፀጎቹ ከትርፋቸው (ከተረፋቸው) ሲሰጡ እሷ ግን ለእለት ኑሮዋ የነበራትን ሁሉ በመስጠት ሙሉ ትምክህቷን በእግዚአብሔር ላይ አድርጋለች. ቤተክርስቲያናችንም ስታስተምረን:-ምእመናን በገንዘባቸው ማነስ ምክንያት ከመመፅወትና ከመባ ወደ ኋላ እንዳይሉ ያስተምራል.ትንሽም ብትሆን በንፁህ ልብና ፍቅር የምትሰጥ ስጦታ በእግዚአብሔር ዘንድ ከሁሉ እንደምትበልጥ ያሳያል ማቴ ፳፩÷፳፯ ሉቃ ፳÷፩-፰ የካህናት አለቆችም ይህን በምን ስልጣን ታረጋለህ ብለው ጠየቁት,የጠየቁትም እውነትን ለማወቅ ሳይሆን በተንኮል ኢየሱስን ለማጥመድ ነበርና."በራሴ ስልጣን"ቢላቸው ትእቢተኛ ሊሉት "ከእግዚአብሔር"ቢላቸው ደግሞ እኛ ነን የእግዚአብሔር እንደራሴዎች አንተን ማን ሾመህ ብለው ሊከሱት ነውና የጌታችን የኢየሱስም ጥበብ የተሞላበት መልስ,የልባቸውን ተንኮል ስለሚያውቅ እነሱ መመለስ የማይችሉትን ጥያቄ ጠየቃቸው ያን ጊዜ አናውቅም ብለው ሸሹ. ማሳሰቢያ⚠️ የክርስቶስን ፊልም ሌሎች እምነቶችም በመውሰድ በራሳቸው መንገድ የሚተረጉሙ እና ልክ ያልሆነና የተሳሳተ ትምህርት የሚሰጡ አሉና መለየት አለብን. #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር

eyoba
eyoba
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 17 November 2026 10:23:56 GMT
936
230
1
10

Music

Download

Comments

user87659395291421
beti lovely mama 💕 :
😘😘😘
2026-11-17 11:33:06
0
To see more videos from user @eyoba6430, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About