@yazifo_42: ዛሬ ለእኔ ከእነዚያ ቀናት አንዱ ሆኖ አገኘሁት እና ቃላት ማሳመር ባልችልም የመፃፍ ፍላጎቴን ግን መግታት አልቻልኩም 😌…. ✍🏻ኖሬ ኖሬ የሆነ እድሜ ላይ ደረስኩ ከዚህ በፊት የእኔ ናቸው የምላቸው ሰዎች በራሳቸው አስበው «ዛሬ የተወለድሽበት ቀን ነው» ሲሉኝ ደስ ይለኝ ነበር። አክባሪ አይደለሁም ዲናችንም እንድናከብረው አላዘዘንም። ብቻ እኔን የሚመለከት ነገር ማስታወሳቸውና ስለእኔ ማሰባቸው ብቻ ያስደስተኝ ነበር። أعشق التفاصيل الصغيرة🫣 ዛሬ ግን ስላለፈው ጊዜ በተለየ መንገድ ማሰብ ጀመርኩ…..እሚቀንስ እንጂ እሚጨምር እድሜ እንደሌለም ገባኝ🙂 እናም በዚያ ጊዜ ምን አደረግኩ? ምን ተለወጠብኝ? ከስህተቶቼ ምን ተማርኩ? የተጸጸትኩባቸው ነገሮች ለእኔ ምን ትምህርት ሰጡኝ? ብዬ ራሴን መጠየቅ ጀመርኩ። እንጃ እያደኩ ይሆን… 🙂↔️ ከምንም በላይ ሁላችንንም ሊያሳስበን የሚገባው ነገር ከአላህ ጋር ያለን ግንኙነት ነው። በሶላታችን፣ ከቁርአን ጋር ባለን ግንኙነትና በኢባዳችን ላይ ምን ያህል ትኩረት እንሰጣለን? በዱንያ ብልጭልጭ ነገሮች ተዘናግተን ስህተት እንሠራለን፣ ወንጀል ውስጥም እንወድቃለን ከዚያም ራሳችንን እናስተካክላለን እንላለን፣ ግን ለነገ እናዘገየዋለን ከጊዜ በኋላም ማዘግየቱን እንለምዳለን፤ በዚህ መካከል ቆይታችን አጭር መሆኑን እንዘነጋለን… መዘንጋታችንን ስንዘጋ ጉዳዩ ባስ ይላል እኔስ ከጌታዬ ጋር ያለኝ ሁኔታ እንዴት ነው? ሶላቴን፣ ቁርአኔንና ኢባዳዬን በተገቢው ሁኔታ እየፈጸምኩ ነው? አንድ ሙስሊም ሰው ማድረግ ያለበትን ነገር በሙሉ እየተገበርኩ ነው? በእውነት ራሴን ለማስተካከል እየሞከርኩ ነው ወይስ እለወጣለሁ በማለት ውስጥ ብቻ እየተጓዝኩ ነው? በመፈለግ ውስጥ ነኝ ወይስ ወደ ተግባር ገብቻለሁ? የመጨረሻ ቀኖቼ መቼ እንደሚሆኑ አላውቅም፤ ከአላህም ጋር መቼ እንደምገናኝ አላውቅም። አሁን፣ ዛሬ፣ ነገ ምናልባት ከዓመታት በኋላ… አላሁ አዕለም። ዛሬ ዕድሜዬ ቢያበቃ አላህ ፊት ለመቅረብ ዝግጁ ነኝ? አላህን በሰላም ልብ የምገናኝበት መልካም ሥራ አለኝ? ወይስ የተውኳቸውንና ያልፈጸምኳቸውን ነገሮች ለማስተካከል ጊዜ ቢመለስ ብዬ እመኛለሁ? ከዚያ በኋላ ደግሞ ከሰዎች ጋር ያለኝን አያያዝ ማሰብ ጀመርኩ። ለሰዎች ጥሩ ነበርኩ? ሳላስበው በቃሌ ወይም በድርጊቴ የሰው ልብ ሰብሬ ይሆን? የሰውን ሀቅ ከመጠበቅ ተዘናግቼ ይሆን? የሚወዱኝንና የሚያስቡልኝን ሰዎች የሚገባቸውን ክብርና ፍቅር ሰጥቻቸው ይሆን? አላውቅም፤ ግን ራስን መመርመር ማለት ከራሳችን ጋር ያለንን ግንኙነት ብቻ ማየት ሳይሆን፣ የሌሎችንም መብትና ስሜት ማሰብን ያካትታል ብዬ አስባለሁ። 😌 ይህን ሁሉ ጥያቄ ለራሴ ስጠይቅ፣ መልሶቹ ዝግጁ ናቸው ማለት አይደለም። አሁንም በመመኘት፣ በመፈለግና በመሞከር ላይ ነኝ። ከስህተቶቼ መማርን፣ በዲኔ፣ በሥነ ምግባሬና ከሰዎች ጋር ባለኝ ግንኙነት የተሻለች ሰው ለመሆን እየሞከርኩ ነው። ለእኔ ይህ በራሱ ከራሴ ጋር ሂሳብ ማድረጌ ትልቅ ነገር ነው። በመጨረሻ፣ ዋናው ነገር ምን ያህል ጊዜ እንዳለፈ ብቻ አይደለም፤ ያንን ጊዜ እንዴት እንዳሳለፍነው፣ በውስጣችን ምን እንደተለወጠና በዚያ ጊዜ ምን እንዳደረግን ነው። እስቲ እናንተስ፦ ከራሳችሁ ጋር ተቀምጣችሁ ሕይወታችሁንና ራሳችሁን ስትመረምሩ፣ ወደ ተሻለ ሰው ተለውጣችኋል? ከአላህ ጋርና ከሰዎች ጋር ያላችሁ ግንኙነት እንዴት ነው? ዛሬ በሆናችሁት ሰው ደስተኛ ናችሁ? ሁሉንም አንብባችሁ እዚህ ከደረሳችሁ ሰብር አላችሁ ማለት ነው🤭👏🏻 #fypシ##islamic_video##yazifo_42##foryoupage##ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Foz✨
Region: SA
Tuesday 17 November 2026 20:38:28 GMT
Music
Download
Comments
𝚔𝚑𝚎𝚒𝚛𝚢𝚊 🤎☕ :
የኔ ዉድ ያላስተዋልናቸዉ አሁን አደግን መሰል የሚያሳስብን ሌላ ሆኑ
2026-11-17 21:42:52
1
Sinwar__ســـنوار :
صح أختي اللهم بارك و زيد علماً و فهماجزاك الله خيرا ✨
2026-11-18 03:28:12
1
To see more videos from user @yazifo_42, please go to the Tikwm
homepage.