@aj.ethiopia: )"የዛሬ 50 ዓመት ገደማ የመጀመሪያ የሥራ ቦታዬ በጎጃም እምብርት በምትገኘው ፍኖተ ሰላም ነበር። በወቅቱም አብዛኛውን ጊዜ ብቸኛው ሐኪም እኔ ነበርኩ። ከዚያ ዘመን የማልረሳው ትልቁ ትዝታዬ ግን እኔ ሐኪም ሆኜ ሳለ እኔን ያከሙኝና ኢትዮጵያዊነትና አማራነት ምን እንደሆነ ያስተማሩኝ የዳሞት ገበሬዎች ናቸው። አማርኛቸው፣ ልበ ሙሉነታቸው፣ ደግነታቸው፣ ሳቃቸውና ትዕግሥታቸው ለዘላለም የማልረሳው ትምህርት ሆኖኛል። በዚያን ዘመን ጎጃም ባላባትና ጭሰኛ የሚባል ልዩነት የሌለባት፣ ሁሉም በክብር የሚኖርባት አካባቢ ነበረች። ሁሉም የተሟላ ኑሮ ነበራቸው፤ ደጋሽነታቸውም የማይረሳ ነበር። «በሞቴ ይብሉ» የሚሉት አነጋገር እስከዛሬ ከአእምሮዬ አይጠፋም። በወቅቱ የሚጠጡት ውኃ ኮረፌ ነበር፤ ለሕፃንም ለአዋቂም የዕለት መጠጥ ይህ ነበር። አብዛኛው ገበሬም ጫማ አያደርግም ነበር። የእግራቸው ጥንካሬ ይገርመኝ ነበር፤ እኔም ለመሞከር ብሞክር አልቻልኩም። ጥርሳቸውን ባይቦርሹም ከሕፃን እስከ ሽማግሌ ጥርሳቸው ጤናማና ሙሉ ነበር። የአፍ ሽታም ሆነ የሰውነት ጠረን አያስታውሳቸውም። በቀን ሁለት መለኪያ ሴስቴ መጠጣትም የጎጃም ሰዎች የተለመደ ልማድ ነበር። እኔ ግን ለመላመድ አልቻልኩም። አንድ ቀን ገበያ ላይ ያላወቀኝ ገበሬ ሴስቴ ሊጋብዘኝ ሲል አልስማማም አልኩት። እሱም በሳቅ «እንደኛ ደመ መራራ ስላልሆኑ ነው» ብሎ መለሰልኝ። የወቅቱን የፖለቲካ ሁኔታን በማስታወስ፣ አብዮት የተባለው እንቅስቃሴ ጎጃምን አልዘለቀም፤ ካድሬዎችም ከከተማ ወጥተው ወደ ገጠሩ መሄድ ይቸገሩ ነበር። ለስብሰባ ሲጠሩም ሰው አይመጣላቸውም ነበር። ጎጃም ራሷን የቻለች ሪፐብሊክ እስከመሆን የደረሰች ትመስል ነበር። የአካባቢው ባላባቶች ፊታውራሪና ደጃዝማች በሚል የክብር ማዕረግ ይጠሩ ነበር። እኔም የትውልድ ሐረጌን ካጣሩ በኋላ በየድግሳቸው የክብር እንግዳ አድርገው ይጋብዙኝ ነበር። ከእነርሱ ጋር በክብር ማዕድ እቀርብ ነበር። በዚያን ዘመን ፍኖተ ሰላም አንድ በሬ አራጅ ብቻ ነበራት። በሬ ማረድ እንደ ዝቅተኛ ሥራ ይቆጠር ስለነበር ይህ ሰው የሚበላው ሥጋ ብቻ ነበር። ብርንዶ መውደዴን ካወቀ በኋላ ግን ጥሩ ሰንጋ ባገኘ ቁጥር በሌሊት ወደ ግቢዬ ይመጣና በሩን አንኳክቶ፣ «ይሄውልህ አንተ ጅብ፣ ዛሬ ቀንቶሃል፤ ሽንጡ ያንተ ነው» ይለኝ ነበር። ሥጋውን ሸጦ ከጨረሰ በኋላ ሽንጡን ይዞልኝ ይመጣል። ከጎረቤት ጠጅ በማንቆርቆሪያ ይመጣል። ሽንጡን በግቢዬ ውስጥ ባለው ዛፍ ላይ ሰቅለን በጆፌና በመንደር ውሾች ተከበን እንበላ ነበር። ከዚያም ለእሱ የገዛሁለትን የደገላ ምንጣፍ አንጥፎ እዚያው ያድራል። አካባቢው ጅብ የሚበዛበት ቢሆንም እንዳይበላው ብዬ ወደ ቤት ገብቶ እንዲተኛ ስነግረው፣ «ጅቡ ይፈራኛል» ብሎ ይመልስልኝ ነበር። በእርግጥም ጅቦች መጥተው አጠገቡ ያለውን ቅሪት እንጂ እሱን ምንም አያደርጉትም ነበር። ታዲያ ዳሞትና ጎጃም እንዴት ከልቤ ሊጠፉ ይችላሉ? #Gojjam

AJ Ethiopia
AJ Ethiopia
Open In TikTok:
Region: ET
Wednesday 18 November 2026 13:45:04 GMT
21564
1052
55
81

Music

Download

Comments

sefineh.mekuriaw
ትንሹ369 :
የፍኖተ ሰላም አካባቢ ልጅ ነኝ። ምናልባት አርባይቱ እንሰሳ ቀበሌን ወይም ቤተክርስቲያኑን ታውቁት ከሆነ!?ወይም ዛምሬት፦መርጊ፦ቄስ አምባ ሲባል ሰምተዉ ከሆነ!?እኔ የዚያ አገር ልጅ ነኝ።ከፍኖተ ሰላም በስተደቡብ አቅጣጫ 6 ወይም 7 km እራቅ ብሎ። ስለ ሀገሬ ሲያነሱ ደስ ስላለኝ ነው እሺ ከልቤ አመሰግናለሁ🙏🙏🙏
2026-11-18 15:28:22
13
maexporte
muller :
በጣም ደስ በሚል አገላለፅ ነው የገልፅህው ማርያምን እኔ የ መንዝ ልጅ ነኝ ከ ፉነተሰላም 8kilo ሜትር ኮረፌ የ ሚለውን ጠላ በሚል ቢስተካከል አመ👍👍🥰🥰ሰግናለሁ
2026-11-18 19:55:11
3
earnake
ABEMELEK አቤሜሌክ :
ኮረፌ ግን የጎጃም ባህል አይደለም እንዳውም አይታወቅም
2026-11-18 19:30:50
5
geche7696219800129
ማሒር :
የዛው አካባቢ ተወላጅ ነኝ የአካባቢውን ሁኔታ በተወሰነ ገልፀከዋል ግን ኮረፌዋን በጠላ ብትቀይራት የበለጠ ይገልፀው ነበር
2026-11-18 16:21:34
24
user6614935467581
eyasu.ye :
tizitaye....
2026-11-19 05:10:32
0
user8737851461563
@Mekdi love19 :
በመቸ አመተምህረት ይሆን ደስ ይላል
2026-11-18 14:59:42
3
atakelt.asemie
Atakelt Asemie :
ይህ ዘመን ያምጣልን ግን አሁንም ህዝብ ለይ ችግር የለም ።።ገን ናፍቀውኛል
2026-11-18 17:41:23
4
gulma9238
Gulma :
ወይ ሀገሬ ሰውማ ዛሬም ያው ነው በሞቴ ብሉልኝ። ምን ዋጋ አለው?
2026-11-19 05:47:37
1
user8513825560872
user8513825560872 :
አቤት እንዴት ያለ ምርጥና ድንቅ አገላለፅ ነው እኔ የፍ/ሰላም እምብርቷ ነዋሪ ነኝ እርስዎ የተናገሩት እውነተኛና የማይፋቅ ሀቅ ነው የላህን እና የአረራን ውሀ የጠጣ ምን ጊዜም በጎ አሳቢ ነው ዕድሜ ከጤና ጋር ይስጥልኝ
2026-11-19 00:54:14
2
user6068611681192
alex dereje :
ትክክል ዳሞት ያስተፋል አሞት
2026-11-19 02:37:58
0
yene3369
𝙮𝙚𝙣𝙚𝙣𝙝🍏 :
ውቢቷ ሀገሬ ፍ/ሰላም
2026-11-18 17:41:31
2
ayemanotman0
haymanot :
ጐጃም
2026-11-19 02:19:30
1
siyumett
seyoum :
አገላለፁ በጣም ይመቻል እንደርስዎ ያሉትን የዋሆች ያብዛልን
2026-11-18 18:50:35
1
c394961
c394961 :
ፍኖተሰላም ወይም ጎጃም ኮረፌ ሳይሆን በጠላ ነው ምትታወቀው ኮረፌ ጎጃም ባህርዳር ብቻ የሚገኘው
2026-11-18 17:29:13
1
alemenhwoubesht.a
my name is Ethiopia :
እውነት ነው ከዛሬ 4 ዓመት ገዳማ ይመስለኛል የዶክተርን ሙሉ ቃለ መጠይቁንና የሰጠውን ኢንተርቪው ተከታትየዋለሁ እናም የዙሪያ ገበሬዋችን የንግግር አገላልፅ ባህሪ ግሩም ነው ሲል በተለይ አንዳንድ ቃላቶችን ሲናገር እሳት በርሐ ይሸቀሽቀኛል ቅንድቤን እያለ ነው አወ ክፍና ደግ የለየሁበት ጎጃም ፍኖተ ሰላም ነው ይላል በትዝታም .....
2026-11-18 18:59:40
1
hope2def5
Melody :
እኔን ያገሬ ሰው🥰🥰🥰
2026-11-18 18:33:50
1
tejitubelchewgmail
[email protected] :
100% perfect
2026-11-18 19:04:44
1
alixe.man
@ካልታማህ አትነግስም man :
waw 💪💪💪💪💪
2026-11-18 18:33:38
1
user300800111915
ጎጃሜው :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-11-18 22:48:36
1
akliludestaw
akila :
Real history
2026-11-18 18:25:22
1
habtie9
ሀብቴ z aman :
2026-11-18 17:33:32
0
seidu483
seidu ali :
ልጅነቴን አስታወስካኝ
2026-11-18 17:51:19
1
user25928296005944
ማኪባ :
እናመሰግናለን🙏🙏🙏
2026-11-18 16:49:35
1
magnaw00
Magnaw :
እውነት ነው
2026-11-18 16:42:21
1
anex41
YEMA :
my Gojjam
2026-11-18 16:14:58
1
To see more videos from user @aj.ethiopia, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About