@yaltenebebugetsoch: ከሠላሳ ዓመት በፊት ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር እና አንድ አማካሪያቸው ጋር ለጉብኝት አንድ ቦታ ኼጄ ነበር፡፡ መንገድ ላይ ዕድሜው ዐሥር፣ ዐሥራ አንድ ዓመት የሚኾነው ልጅ በጠዋት ወደ ትምህርት ቤት ሲሮጥ መንገድ ላይ አገኘነው፡፡ ጫማው የእግሩን መዳፍ፣ ቁምጣውም ወሸለውን ብቻ ለመሸሸግ ያደረጋቸው ይመስላሉ፡፡ ከዚኽ የቀረው በሙከራ ሊጠቃለል ይችላል፡፡ መጽሐፍና ደብተሮቹ ሳይቀር የተቀዳደዱ ናቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልጁን እንድይዘው ትእዛዝ ሰጡኝ፡፡ መኪናውን አቅሜ እንዲገባ አደረጉት፡፡ ከዕድሜው የተነሣ ከውሃ በቀር የሚያልበው አይመስልም፡፡ ነገር ግን ገብቶ ቁጭ ሲል የመኪናው ጠረን በአንድ ጊዜ ተቀየረ፡፡ የፍዬል በርት የፍዬል በረት አለ፡፡ እንዲኽ ፍግ ፍግ የሚሸተው ምን ቢኾን ነው በሚል ቀና ብዬ ተመለከትኩት። እላዩ ላይ ደኅና ልብስ እንኳ የለም። መስኮቱን ልከፍት መስታወቱን ማንሸራተት ስጀምር፤ “ይኹን! እንደ ቅጣትም እንደ ዕጣ ፋንታም እንቀበለዋለን” አሉ ጠቅላይ ምኒስትሩ ወደ አማካሪያቸው ዘወር ብለው እየሣቁ፡፡ ይኽ ኹሉ ሲኾን ልጁ የወንበሩ ጫፍ ላይ ተቀምጦ ይወዛወዛል፡፡ ወደኋላ ደገፍ ብሎ እንዲቀመጥና ቀበቶ እንዲያሥር አደረኩት፡፡ ገረመው፡፡ እኔን ሳይቀር በትኩረት መረመረኝ፡፡ “ሰው ታምናለህ ማለት ነው?” አሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ “አላምንም!” ዘወር ብሎ እንኳ አላያቸውም፡፡ ቢያያቸውም የሚያውቃቸው አይመስልም፡፡ “እና እንዴት ገባህ?” አሉት፡፡ መልሱ ቁርጥ ያለች ነበረች፡፡ “ስላቆማችሁልኝ” “አንድ ነገር እኾናለሁ ብለህ አልፈራህም?” “እኔ እንደዚያ አላምንም” ሲያወራ መኪናው ውስጥ ያሉትን ነገሮች በመመርመር ነው፡፡ የተሠሩበትን ጥራት፣ ጥንካሬና ልስላሴያቸውን ለማወቅ በእጁ ይዳብሳል፡፡ “ኣሃ ምንም ነው የማታምነው?” አሉ አማካሪው ሣቅ እያሉ፡፡ “አዎ . . . ” ፈገግ እያለ መለሰላቸው፡፡ ሐሳቡን የበሰለ ፍልስፍና እንዳለው አድርገው ሳይረዱት አልቀረም፡፡ ንግግሩ እንደወረደ ከታዬ ተራ የልጅ መልክ ነበር፡፡ ሲያመሳጥሩት ግን ለየት ያለ አተያይና ፍልስፍና ኾነ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከያዝኩት ጥሬ ገንዘብ ትንሽ እንድቆነጥርለት አስታወሱኝ፡፡ የተወሰነ ብር አንሥቼ እጁ ላይ አደረኩለት። በጥርጣሬ ቀና ብሎ አየኝ። “እሳቸው ናቸው የሰጡህ አልኩት” ዘወር ብሎ አያቸው። “ምንድነው የማደርገው?” አላቸው። “ደስ ያለህን” “በሬ ልግዛበት?” አለ ፈገግ እያለ፡፡ “ደስ ያለህን” “አመሰግናለኹ ጌቶች” አለና እጅ ነሣ፡፡ ትንሽ እንደተጓዝን ከመንገዱ የምትገነጠል አንዲት አነስተኛ የገጠር መንገድ አገኘን፡፡ “በዚኽ በኩል ነው ትምህርት ቤቴ” አለ በእጁ አቅጣጫውን እያመላከተ፡፡ መኪናውን እንዳቆምኩ ፈጠን ብሎ ለመውረድ ብድግ ሲል ቀበቶው ይዞ አስቀረው፡፡ ምን ዐነቀኝ በሚል ገልመጥ አደረገኝ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኋላ ትከሻውን ያዝ አድርገው፤ “ስምህ ማነው?” አሉት፡፡ “አያና” ስሙን ማስታወሻ ደብተራቸው ጻፉት፡፡ * ከወራት በኋላ አንድ ቀን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሯቸው አስጠሩኝ፡፡ ያን ሰሞን የውጭ ጉብኝት አድርገው መመለሳቸው ነበር። ቁጭ እንዳልኩ፤ "አያናን ታስታውሰዋለህ?" አሉኝ። "በደንብ!" አልኳቸው። "ጥሩ። ቤተሰቦቹን ፈልገህ አግኛቸው። እና ልጃቸውን ለትምህርት ዐዲስ አበባ መላክ ይችሉ እንደኾነ ጠይቃቸው" አሉኝ። * አኹን ላይ ከተሸሙት ሚንስትሮች አንዱ ይኽ ልጅ ነው፡፡ . . .
ያልተነበቡ ገፆች / መረጃ እና ታሪክ /
Region: ET
Thursday 19 November 2026 17:24:52 GMT
Music
Download
Comments
girmay berhe :
ይገርማል ግን ያላለቀ ታሪክ ይመስለኛል አያና ማነው ?
2026-11-20 04:16:27
8
Wondu Demisee :
በጣም መሳጭ ታሪክ
2026-11-20 07:17:50
2
ጴንጤ ነኝ 🙌🙌 :
መሌ ጀግናው ይችላል
2026-11-20 10:23:10
3
Eth @1216 :
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ እኮ ሰው ነው!!
2026-11-19 21:30:22
22
Lorenzo 🇮🇹 :
ይገርማል ፈጣሪ ነብሳቸዉን በደጋጎቹ አጠገብ ያሳርፍልን አያና ማን ይሆን
2026-11-20 09:57:00
3
John :
አላምንምምምም
2026-11-20 10:35:13
1
tewelde :
"እንደ ቅጣትም እንደ ዕጣንም" ብለው ሲያበቁ የትምህርት ስርዓት ማስተካከል ይገባቸው ነበር። . . ለማንኛው የሚመሰገኑበትና የሚወቀሱበት ብዙ ስለሆነ ቀጣዩ ክፍል አስነብበን🙏።
2026-11-20 07:37:37
3
Juel :
መሌ ሁሌም በልባችን ትኖራለህ
2026-11-20 04:50:26
6
REBIRA :
ደስ ይላይ
2026-11-20 10:33:01
1
ኢትኤል ጊዜነው :
ይቅር ይበለን
2026-11-20 08:55:50
3
The Legend :
ኣያና የሚባል ሚኒስትር ማነው ????????
2026-11-20 01:44:09
3
dehabrtg5ob :
ገራሚ ነው
2026-11-20 06:50:08
1
Tekeba Mulugeta :
AAAAyiiiiiiìì Deg sew
2026-11-20 04:24:25
2
Yekalekidan Amelak :
Menged belelebt menged yalew Egziabeher yemsgen
2026-11-20 08:28:26
1
Aragaw hussen :
ቀጣዬን ንገረኝ
2026-11-19 18:21:41
2
user A2 :
ማንነው ?
2026-11-19 22:43:09
1
supra :
ጥሩ
2026-11-19 19:11:37
1
kinfe kidane :
🙏🙏🙏🙏
2026-11-19 21:05:24
2
Emishaw Gebre yohannea :
ሕይወት ከልቦለድም ትልቃለች ይሏል...
2026-11-19 18:14:01
1
ዴልታ ታንጎ :
ጆን ኧረ የሚቀጥለውን
2026-11-20 04:29:52
0
Mehari Fitsum :
አረ በናትህ አልጨረስከውምኮ ምን እያረክ ነው መጨረሻው ምን ሆነ ልጁስ ከምን ደረሰ? ማን ይሆን ያ ልጅ? 🥰🥰🥰🥰
2026-11-20 10:07:03
0
ክፍሌ ወልዴ :
ሚንስትሩን ሰሙንእና አሁን የለበትን ሁኔታ ብትገልፅልን ወይም እራሱ ቢገልፅ ከነአመለካከቱ
2026-11-20 12:23:25
0
Birhane tadese :
A
2026-11-20 11:01:22
0
Esrael :
በቃ ፎሎ ትደረጋለክ ሰለ ሊቁ አወራክ🙏🙏🙏
2026-11-20 04:04:25
2
tedy sky light :
አመሰግናለው ጌቶች [Pray][Pray]
2026-11-20 07:06:11
1
To see more videos from user @yaltenebebugetsoch, please go to the Tikwm
homepage.