@dinkish3: በስልካቸው የተቀነባበረ ሐሰተኛ የሞባይል ባንኪንግ የክፍያ መልዕክት እና ሀገራዊውን የፋይዳ መታወቂያ አስመስለው የሠሩትን ሐሰተኛ መታወቂያ አንግበው ሪዞርቶችን፣ የንግድ ቤቶችንና የእንግዳ ማረፊያዎችን ማመስ ጀመሩ። በስድስት ተቋማት ገብተው ውድ ሽቶዎችን ተቀቡ፣ የመዋኛና የመዝናኛ አልባሳትን መረጡ፣ ጫማና ሱሪውን ሸመቱ፤ ምግብና መጠጡን ኮመኮሙ፤ አልጋውንም ተጠቀሙ። ሲወጡ ግን በስልካቸው የውሸት «ተከፍሏል» መልዕክት እያሳዩ የላባቸውን ያተረፉ ነጋዴዎችን ኪስ አራቆቱ። ግን አንድ ነገር ረስተው ነበር — ሀዋሳ ባለቤት እንዳላት! የሀይቅ ዳር ክፍለ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር እሸቱ ጌታሁን እንዳሉት፣ ሕብረተሰቡና ፖሊስ ዓይንና ጆሮ ሆነው ተናበቡ። የታቦር ክፍለ ከተማ እና የዳካ ክፍለ ከተማ ሀይቅ ዳር ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤቶች በመረጃና በኢንተለጀንስ ጥበብ ተቀናጅተው ያቺን «ያሪስ» መኪና በጥብቅ ክትትል ውስጥ አስገቧት። መጨረሻው ግን ለሌቦቹ አሳዛኝ፣ ለሕዝቡ ደግሞ አስደሳች ሆነ። በታቦር ክፍለ ከተማ መኪናዋ ተከባ ስትፈተሽ፣ ተጠርጣሪዎቹ የተሰረቁትን ዕቃዎች ከመያዛቸውም በላይ አንዳንዶቹማ የሰረቁትን ልብስ ለብሰውት እጅ ከፍንጅ ተያዙ! ሐሰተኛ የፋይዳ መታወቂያዎቻቸውም አብረው ተመዘዙ። ከዚህ ታሪክ ምን እንማራለን? 1. የፖሊስና የሕዝብ አንድነት ኃይል፦ ሕዝብ ሲጠቁም፣ ፖሊስ ደግሞ በፍጥነትና በጥበብ ምላሽ ሲሰጥ ማንኛውም ወንጀለኛ መደበቂያ እንደሌለው በተግባር ታይቷል። 2. የቴክኖሎጂ ጥንቃቄ፦ ነጋዴዎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የደንበኛን ስልክ ስክሪን ብቻ አይተው «ተከፍሏል» ማለትን ማቆም አለባቸው። ገንዘቡ በራሳቸው አካውንት መግባቱን ማረጋገጥና የእንግዶችን መታወቂያ በአግባቡ መመዝገብ የግድ ይላል። በጀግንነት የሚጠብቀውና በሰብአዊነት የሚያገለግለው የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ሰሞኑን እያሳየ ያለው ቁርጠኝነት «ለሌቦች ሀዋሳ አትመችም!» የሚል ግልጽ መልዕክት አስተላልፏል። ምስጋና ለዓይነ-ንቁው ሕዝባችንና ለትጉ የሀዋሳ ፖሊስ አባላት! 👏🇪🇹 #hawassatiktok #sidamatiktok💚💙❤️ #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #ትኩረት @Sidama Police Official @@sidamapolice4656 @sidama police commissioner @Awnta Bersisa @ሲዳማ News🎤 @SouthRadioandTelevisionAgency @mesay awassa @Tsegaab Dawit @eyoba_101 @ሀዋሳ ከነማ ደጋፊዎች

ድንቅ Documentary 📽🎞ሀዋሳ
ድንቅ Documentary 📽🎞ሀዋሳ
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 19 November 2026 17:32:25 GMT
107725
11957
328
2852

Music

Download

Comments

chere2781
𝐂𝐡𝐞𝐫𝐞✨ :
የሀዋሳ ፖሊስ ሰሞኑ አልተቻለውም በርቱ ጀግኖች
2026-11-19 17:36:15
113
temegs08
keyu ቀዩ 0000 :
መቼም ከወንጀል የማይጸዳ ክልል
2026-11-20 03:23:02
1
afomiya341
afomiya :
አረ ለሀዋሳ ፖሊስ ክብር ይገባቿል🙏🙏🙏
2026-11-19 18:14:59
47
mariyana6939
Mariyana :
Oh my God, I love it How was
2026-11-19 20:40:24
0
esiraelmelese565
eso :
jegina ye hawassa police❤❤❤❤
2026-11-20 04:54:59
0
winta_567
wintana Tesfaye :
ሚገርም ነው💪
2026-11-20 05:53:11
3
user90150447762806
Abdujabar yasin :
thank you hawassa pollisse
2026-11-20 05:14:07
0
adugna.fire112221
Adugna Firew Apo lij :
የሀዋሳ ፖሊስ አልተቻለም👍👍
2026-11-19 19:09:03
5
zawdu.tamiru
zawdu tamiru :
🫶🫶🫶🫶🫶💪💪💪💪💪
2026-11-20 04:01:58
0
userzuye62818245695843
zufan zusha 12 :
ዎውው እግዚአብሔር ይመስገን
2026-11-19 17:56:38
3
user19257023553797
Abirham Urji (1) :
111111111111111111111111
2026-11-19 19:43:56
0
nardose056
almayo nardose :
are hawasa folse yengese
2026-11-19 21:46:17
2
mitiku.bale
Mitiku Bale :
:የሀዋሳ ፖሊስ ሰሞኑ አልተቻለውም በርቱ ጀግኖች
2026-11-19 23:11:28
1
naninadue
wube💎 :
አረ ለሀዋሳ ፖሊስ ክብር ይገባቿል🙏🙏🙏
2026-11-20 01:18:54
1
user7692425410349
melese :
thank you💪💪💪💪💪💪💪💪
2026-11-20 05:21:26
2
fantuzemedkun
fantuzemedkun :
ጀግና እናመሰግናለን
2026-11-19 19:27:47
2
user8857879714102
Tagusha🇪🇹 :
ye hawassa liji bemehone korawubach beritulin🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝
2026-11-19 18:32:19
8
zolabro4
DANGOTE :
የሲዳማ ከክልል ፖሊስ ሀዋሳ ከተማ ጀግንነቱ እንደቀጠለ ነው💪💪💪 እነዚህን ጀግኖች አለማድነቅ ንፉግነት ነው 🙏🙏🙏🙏🙏
2026-11-19 19:57:08
2
ebrahim.kedir954
Ebro Halabawu🇪🇹Eትዮጵያ ሁሌም ካፍ :
👍✨:የሀዋሳ ፖሊስ ሰሞኑ አልተቻሉውም በርቱ ጀግኖች እንዳዝህ ነዉ ለህዝብ መቆም
2026-11-19 19:15:17
9
asnake_melese
አስናቀ መለሰ :
ጀግኖች
2026-11-19 19:36:56
1
abynashi
abynashi :
ጄግናች የሀዋሳ ፖሊሶች
2026-11-19 22:15:30
1
user3954123738320
መስቀሌ መንገሻ :
ሀይ ጀግኖቹ ወደ ገጠርም እዩት
2026-11-19 21:16:57
1
fasika.gelan
fasika gelan🦋🦋🦋 :
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️የሀዋሳ ፖሊስ ሰሞኑ አልተቻሉውም በርቱ ጀግኖች እንዳዝህ ነዉ ለህዝብ መቆም
2026-11-19 20:46:38
1
user5879044963615
user5879044963615 :
Jaginochi baretu👍👍👍👍
2026-11-19 19:23:24
1
user4401345882290
user4401345882290 :
haapools
2026-11-19 19:49:34
1
To see more videos from user @dinkish3, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About