@mrjmshne: real life built-in beauty filter ✨ @SKINEVER PH #skinever #sunscreen #bodylotion #whiteninglotion #evenskintone

elneshne on ig
elneshne on ig
Open In TikTok:
Region: PH
Friday 20 November 2026 07:03:50 GMT
555
50
2
1

Music

Download

Comments

joan.reboton
anisu :
hindi ba sya dumidikit sa damit and pag nagpapawis hindi rin ba sya nahuhulad
2026-11-20 07:13:43
0
roamike2
Mike Roa :
[Heart eyes][Heart eyes][Heart eyes]
2026-11-20 07:12:57
1
To see more videos from user @mrjmshne, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በ98.7 በመቶ ድምፅ አዲስ የተሻሻለ የሥርዓት ደንብ አጸደቀ። ኅዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም [#ሐመረ_ተዋሕዶ_ሚዲያ] በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሰብሳቢነት የሚመራው የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፤ ለ41 ዓመታት ሲያገለግል የቆየውን የ1985 ዓ.ም (እ.ኤ.አ.) መሠረታዊ የሥርዓት ደንብ በማዘመን አዲስ ሰነድ አጽድቋል ።  በግብፅ ዋዲ ናጥሩን በሚገኘው ታሪካዊው የቅዱስ አባ ቢሾይ ገዳም ሎጎስ ማዕከል ከኅዳር 8 እስከ 10 ቀን 2019 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. ኅዳር 17–19 ቀን 2026) ለሦስት ቀናት በተካሄደው  መደበኛ ስብሰባ፤ በ10 የውይይት ዙሮች ሰፊ ምክክር አድርጓል።  ከጠቅላላው 138 የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል 116ቱ በአካል የተገኙ ሲሆን፣ 15 አባላት በጤና እክል ምክንያት መገኘት ባይችሉም በሲኖዶሱ ውሳኔ መስማማታቸውን ገልጸዋል።  ይህንን አዲስ ደንብ ለማዘጋጀት ከግንቦት ወር ጀምሮ ሰፊ ዝግጅት ሲደረግ የቆየ ሲሆን፤ ከ102 የሲኖዶስ አባላት የተሰበሰቡ የማሻሻያ ሐሳቦች በጽሕፈት ቤቱ ኮሚቴ ተደራጅተውና በታዋቂ የሕግና የቋንቋ ባለሙያዎች ተረቀው ቀርበዋል። ረቂቁም በፓትርያርኩና በቋሚ ኮሚቴው ለሰዓታት ከተገመገመ በኋላ ለምልአተ ጉባዔው ቀርቦ፣ እያንዳንዱ አንቀጽ በተናጠል ውይይት ተደርጎበትና በኤሌክትሮኒክስ የምስጢር ድምፅ አሰጣጥ ሥርዓት ተመዝኖ በ98.7 በመቶ አጠቃላይ የድጋፍ ድምፅ በይፋ ጸድቋል።  አዲሱ የሥርዓት ደንብ ቀደም ሲል የነበሩትን 12 ምዕራፎችና 72 አንቀጾች ወደ 14 ምዕራፎችና 100 አንቀጾች ያሳደገ ሲሆን፤ በዋናነት በቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ዲሲፕሊን፣ በሰብዓዊና የእረኝነት  እንክብካቤ እንዲሁም በተቋማዊ አደረጃጀት ላይ ጉልህ ማሻሻያዎችን ይዟል። በዚህም መሠረት የፓትርያርኩንና የጳጳሳትን የሥልጣንና የኃላፊነት ወሰን በግልጽ ከመወሰኑም ባሻገር፣ አዳዲስ ጳጳሳት የሚመረጡበትን ግልጽ አሠራርና የዲሲፕሊን ተጠያቂነት ሥርዓቶችን አካቷል።  በተጨማሪም ደንቡ ለአረጋውያንና በሕመም ላይ ለሚገኙ ብፁዓን አባቶች ጤናዊ፣ ሥነ ልቦናዊና የኑሮ ድጋፍ የሚደረግበትን ሰብዓዊ እንክብካቤ በተደራጀ መልኩ አስቀምጧል። በሀገረ ስብከቶች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በሕመም ምክንያት አገልግሎት ሲስተጓጎል የሚወሰዱ እርምጃዎችን፣ ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር ያለውን የኢኩሜኒካል ግንኙነት፣ በውጭ ሀገራት የሚደረገውን ሐዋርያዊ መስፋፋት እንዲሁም የዲጂታል ዘመን ቴክኖሎጂያዊ የአገልግሎት ፍላጎቶችን ያገናዘቡ አዳዲስ አንቀጾች በደንቡ ውስጥ ተካተው መጽደቁን ከcoptic Orthodox church ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::  የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ በ-ዲ/ን አየለ Coptic Orthodox Church - الكنيسة القبطية الأرثوذكسية

About