@sarwitegetagiram: ‹‹ኅዳር 12›› የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሲመቱ/ የተሾሙበት ዕለት ነው። የሰማይ ሰራዊት ሁሉ አለቃቸው መልአከ ምክሩ የምክሩ አበጋዝ ይለዋል የቅድስት ስላሴ መንጦላእትን የሚከፍትና የሚዘጋ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ የገናናው ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት ቀን ነው። በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቅዱስ ሚካኤል ለማንም ያልተሰጠ እጅግ ታላቅ የሆነ ክብር እንደተሰጠው ተጽፎ እናገኛለን፡፡ ይኸውም በዕለተ ምጽአት ጌታችን ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ በክበበ ትስብአት በግርማ መለኮት በሚመጣበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሙታን ላይ ሥልጣን የተሰጠው ለዚሁ ለኃያሉ መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ከሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በምልጃው ይጠብቀን🙏

@sarwite Geta Giram የተዋህዶ ልጆ
@sarwite Geta Giram የተዋህዶ ልጆ
Open In TikTok:
Region: BH
Friday 20 November 2026 16:04:54 GMT
2590
924
17
32

Music

Download

Comments

tapashu2112
@$2112$$ :
አሜን ቅዱስ ሚካኤል አባቴ እርዳኝ
2026-11-20 17:07:14
0
alemuyimer07
alemuyimer07 :
እኳን ደና ገባሽ
2026-11-20 18:00:29
0
.deresh
ደራሽ Deresh :
ህዳር ሲታጠን ምድነው
2026-11-20 16:24:06
0
moulou.rhone
Moulou Rhone :
amne amne amne [Cœur rouge]
2026-11-20 17:14:41
0
sherifo841
sherifo :
ኣሜን
2026-11-20 16:17:10
0
segenate
✝️ትወድኝየለ ✝️አበርታኝ💞 :
አሜን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-11-20 16:17:47
0
marta.mamo5
Marta Mamo :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏💕💕💕💕
2026-11-20 18:13:59
0
martadachasa
Marta Dachasa :
❤️❤️❤️❤️❤️
2026-11-20 16:18:13
1
buba2124
yemaryam :
🙏🙏🙏
2026-11-20 17:13:22
0
fanta8726
Fanta :
🙏🙏🙏
2026-11-20 17:46:06
0
eden.alie
Eden Alie :
🙏🙏🙏
2026-11-20 17:14:33
0
firooman125
firoo🥀🫶🥀 :
❤️❤️❤️
2026-11-20 18:06:52
0
danielteerlde
bani :
🥰🥰🥰
2026-11-20 16:44:25
0
martadachasa
Marta Dachasa :
🙏🙏🙏🙏🙏
2026-11-20 16:18:14
0
hi.me7713
HI ME :
❤️❤️❤️
2026-11-20 16:12:41
0
user4518678750859
mayko 1221 :
❤️❤️❤️
2026-11-20 16:08:15
0
obsee.orth21
Obsee Orth ²¹ 💒🙇‍♀️❤️🥷 :
[Red heart][Red heart][Red heart][Red heart]
2026-11-20 17:52:50
0
To see more videos from user @sarwitegetagiram, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About