@3in1liy: አንዳንድ ጊዜ የሚያሳምመው ሕልማችን አለመፈጸሙ ብቻ አይደለም፤ ያንን ሕልም ከእኛ በላይ እንደሚያምኑ ያሰብናቸው ሰዎች መቃወማቸው ነው...! ዮሴፍ ሕልም ነበረው። ግን ሕልሙን ከመኖሩ በፊት ብዙ ነገሮችን ማለፍ ነበረበት። በወንድሞቹ ተጠላ፣ ተሸጠ፣ ከቤተሰቡ ተለየ። በሐሰት ተከሰሰ፣ በእስር ቤትም ተሰረ... አስቡት... በሕልም የጀመረው ሕይወት በእስር ቤት ቀጠለ... ምናልባት በሰው ዓይን ዮሴፍ የተረሳ ሰው ነበር። ግን ሰው ረሰው ማለት እግዚአብሔር ረሰው ማለት አልነበረም ..... አንድ ቀን ያ በእስር ቤት የነበረው ሰው በግብፅ ላይ ገዥ ሆነ። ያ የተሸጠው ሰው ሕዝብን የሚያድን ሰው ሆነ። ነገር ግን ከዚህ ታሪክ የምንማረው ዮሴፍ በመጨረሻ ታላቅ ሰው ሆነ የሚለውን ብቻ አይደለም። በጥበቃው ወቅት ታማኝ መሆኑን፣ በፈተናው ውስጥ ባህሪውን እንዳልተወ፣ ለበደሉትም ይቅርታ ማድረጉን ነው... ምናልባት አንተም አሁን የማትረዳው የሕይወት ምዕራፍ ውስጥ ትሆናለህ። የሞከርከው ነገር አልተሳካም፤ ያመንካቸው ሰዎች አሳዝነውህ ይሆናል። የወደፊት ሕይወትህም ግልጽ አይሆንልህ ይሆናል። ግን የዛሬው ምዕራፍህ የመጨረሻው ገጽህ እንዲሆን አትፍቀድ። ከሰዎች ጋር ባለህ ቁርሾ ምክንያት መልካምነትህን አትተው። በመጠበቅህ ምክንያት እምነትህን አትተው ዮሴፍ በመጨረሻ ለወንድሞቹ እንዲህ አላቸው፦ «እናንተ ክፉ አሰባችሁብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ለበጎ አደረገው።»ዘፍ 50፥20 ምንኛ ጥልቅ እውነት ነው! ሰዎች በታሪክህ ውስጥ መጥፎ ምዕራፍ ሊጽፉ ይችላሉ፤ ግን የታሪክህ ደራሲ እነርሱ አይደሉም☺️ አንድ ቀን ዛሬ የሚያስለቅስህን ምዕራፍ ወደ ኋላ ተመልክተህ በምስጋና ልታስታውሰው ትችላለህ። ስለዚህ በመካከለኛው ምዕራፍ ላይ ታሪክህን አትፍረድ። እግዚአብሔር ገና እየጻፈ ነውና.....❤ . . . . . #christiantiktok #viral #caption #ethiotiktok
𝑙𝑖𝑦🪺
Region: ET
Friday 20 November 2026 18:48:12 GMT
Music
Download
Comments
God is good :
ልሁን ደስ ባለህ ቦታ
2026-11-21 16:23:44
1
martamale🥰 :
geta wudiketachinin lamimegnut asalfo aysetenm🥹
2026-11-21 05:30:44
4
mesik lave :
@mesik lave:tilk merdat nw Amen Egizabiher Eyetsafelin nw.....minalfbet huneta malefiya Dildiy Enij menoryachin ayidelem😍
2026-11-21 09:51:20
1
Haymi Bonda Meki 👗🧥👖🩳👜 :
በጣም ትክክል🙏🙏🙏
2026-11-21 08:14:11
1
asu 🥰 :
tkkl🤗🤗🤗
2026-11-20 22:20:16
0
temu :
«አሜን! ❤️ዮሴፍ የሕይወት ታሪክ አንድ ነገር ያስተምረናል፤ የሰው መቃወም የእግዚአብሔርን ዓላማ አያስቆምም። የምናልፍበት ፈተና የመጨረሻችን አይደለም። በመጠበቅ ውስጥ ታማኝ እንሁን፤ እግዚአብሔር በጊዜው ያደርጋል። የታሪካችን ደራሲ እርሱ ነው! 🙏❤️»
2026-11-22 05:59:04
0
🥀🥀🥀 :
🥹🥹🥹
2026-11-21 15:54:39
1
kefteshi :
[Twin hearts][Twin hearts][Twin hearts][Twin hearts][Twin hearts][Twin hearts][Twin hearts][Twin hearts]ameeeeen
2026-11-21 06:30:32
1
bilisee✝️❤️🔥 :
😳😳😳😳😳
2026-11-21 06:48:58
1
𝕝𝕚&𝕛❤🌎😇 :
💕💕💕
2026-11-21 21:01:18
0
kal love 🇨🇦🇨🇦🇺🇸🇺🇸 :
yes[Red heart][Red heart][Red heart]
2026-11-21 18:08:37
0
Elijah Adam(ኤሊያስ አዳም) :
❤️❤️❤️
2026-11-21 17:47:20
0
birhan-12 :
🥰🥰🥰
2026-11-20 19:49:28
0
kefteshi :
[Twin hearts][Twin hearts][Twin hearts]
2026-11-21 06:30:10
0
wolate :
[Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming]
2026-11-22 02:29:25
0
To see more videos from user @3in1liy, please go to the Tikwm
homepage.