@addis.nostalgia.1: ተወዳጁ ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በድንገተኛ ሕመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ****************** ተወዳጁ ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ባጋጠመው ድንገተኛ ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በድንገተኛ ሕመም ሕይወቱ ማለፉን የቅርብ ወዳጆቹ ማምሻውን አረጋግጠዋል። ድምፃዊው በወልቂጤ ከተማ የሙዚቃ ሥራውን እያቀረበ በነበረበት ወቅት ባጋጠመው ድንገተኛ ሕመም ሕይወቱ ማለፉን የሙያ ባልደረባው ድምፃዊ ረሻድ ከድር ገልጿል። ሚኪያስ ቸርነት «የኔ ደሃ»፣ «አሁን ገባኝ»፣ «እዞዜ»፣ «ግርማ ሞገሴ ነሽ» እና «ኪያዬ» በተሰኙ ዜማዎቹ በበርካታ የሙዚቃ አድማጮች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፏል። «ሰላም አላት» እና «10/10» የተሰኙ ሁለት አልበሞችን ጨምሮ በርካታ ተወዳጅ ነጠላ ዜማዎችንም ለሙዚቃ አድማጮች አቅርቧል። ለወዳጅ ዘመዶቹና ለሙያ ባልደረቦቹ መጽናናትን ይመኛል። #ebc @ebc
ADDIS NOSTALGIA 🇪🇹1990–1999
Region: ET
Saturday 21 November 2026 19:30:14 GMT
Music
Download
Comments
There are no more comments for this video.
To see more videos from user @addis.nostalgia.1, please go to the Tikwm
homepage.