@ethiopia.addisababa: አሳዛኝ ዜና/ተወዳጁ ወጣት ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል/Mikiyas Chernet Passed Away #ethiopian አመለ ሸጋው ተወዳጁ ወጣት ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል። ህልፈተ ሕይወቱ ያጋጠመው በወልቂጤ ከተማ ጉብሬ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የዘቢዳር ቢራ ፋብሪካ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በተጋባዥ ድምፃዊነት በተገኘበት ወቅት መሆኑ ታውቋል። ድምፃዊው በስፍራው የተገኘው ቢጂአይ ወልቂጤ ብራንች የሠራተኞች ቀንን ሲያከብር ለተዘጋጀው መርሐ ግብር እንደነበር ተገልጿል። ድምፃዊው በዝግጅቱ ስፍራ መድረክ ላይ እንደወጣ ገና ከመጀመሩ ይቅርታ ብሎ የወረደ ሲሆን፣ በኋላም «ደረቴን አቃጠለኝ» በማለት ድንገት ሕመም እንደተሰማው ተገልጿል። ከቦታው በ3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ወልቂጤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲወሰድ ሕይወቱ ማለፉ ታውቋል። በዘመናዊ ሙዚቃዎቹ ሰፊ ተወዳጅነትን ያተረፈው ሚኪያስ ቸርነት፤ «አሁን ገባኝ»፣ «የኔ ደሃ»፣ «ግርማ ሞገሴ ነሽ»፣ «ናተይ» እንዲሁም ከድምፃዊ ያሬድ ነጉ ጋር በጋራ በተጫወቱት «ጉዳዬ» በተሰኙት ተወዳጅ ሥራዎቹ በአድማጮች ዘንድ በስፋት ይታወቃል። በተጨማሪም «10 ከ 10 ይገባሻል» እና «ሰላም አላት» የተሰኙ አልበሞችን እንዲሁም በቅርቡ «እንዳማረ» የተሰኘውን ነጠላ ዜማ ለአድማጮች አድርሶ ነበር። ለባለቤቱ፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለሙዚቃ አፍቃሪያን በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን። ዜና, መረጃ, Mereja, Zena, ኢትዮጵያ, Ethiopia, Ethiopian, Ethiopian News, Addis Ababa, አዲስ አበባ, ወቅታዊ ዜና, Ethiopian #Ethiopia #ኢትዮጵያ #addisababa ኢትዮጵያ #ኢትዮ seber ሰበር ዜና #ሰበር_ዜና #ethiopianews አሳዛኝ ዜና ሚኪያስ ቸርነት #አሳዛኝ_ዜና #ሚኪያስ_ቸርነት #ድምፃዊ #ሚኪያስ #mikiyaschernet #mikiyas #chernet #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #amharatiktok #tigraytiktok🇻🇳🇻🇳tigraytiktok #oromotiktok❤️💚❤️ #ethiopia #addisababa #habesha #ethiopiansinger#habeshatiktok #amharatiktok💚💛❤️
Addis Ababa, Ethiopia 🇪🇹
Region: US
Saturday 21 November 2026 20:09:50 GMT
Music
Download
Comments
There are no more comments for this video.
To see more videos from user @ethiopia.addisababa, please go to the Tikwm
homepage.