@teshomebalehageru: የአስራት አደራ ወንድማማችነትን ማጠንከር አቅቶ የጣናቸው ሃብቶች ታሪክ እንደሚነግረን መጀመሪያ ሰው ከመሆን ከዚያም ተመሣሣይ ቀለም ተመሳሳይ ሃይማኖት በክርስትና ይሁን በእስልምና አብሮ የሚያመልክ የተዋደደ የተዛመደ ህዝብ አንተ ትብስ አንተ ትብስ የሚባባል ማህበረሰብ ሁለት ጎልማሳና ጎረምሳዎች ተማምለው የነበረ ቢሆንም ሳይተማመኑ ተካክደው ሁለት ትልልቅ ኪሳራ በህዝብ እና በሃገር ላይ አደረሱ። የሚያሳዝን ታሪክ ግን መታረም የነበረበት በምንም መለኪያ ቢሆን አንድ ህዝብ አንድ ሃገር የነበረን ህዝብ የለየ አደገኛ ሴራ እና ውንብድና ተፈፀመ። ለቃሉ ይቅርታ እያልኩኝ ሁለቱ ጎረምሶች የጫካ ስምምነት ከፍ ሲሉ በጎልማሳነታቸው መተማመን አቅቷቸው ቤተሰብ እንዲበተን ሃገር እንዲከፈል አደረጉ ያማል ያበሳጫል። በአሁኑ የኤርትራ ወገኖቻችን እና በኢትዮጵያ መሀል ሳይጣሉ እንዲለያዩ የተወሰነባቸው በደለኞች አደረጓቸው ምነው ህልም በሆነ የሚያሰኝ መልኩ በትውልድ ውድመት ያደረሱ ወንድማማቾች የነበሩ የግል ጥቅም እና ስልጣን ብሎማ የጫካ ህልምን እውን ለማድረግ የተፈጠረ ያለማሠብ እና ሃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ተወሰነ ያች ቀን ጥቁር ቀን ነበረች። ጥሩ ጎረቤት አለመኖሩ እና ለሞኝ ስነግር ዋልኩ ብሎ ጎረቤቱ ሲበተን ስለት የሚሳል ዘላለማዊ የጭቃ ውስጥ እሾህ የሆነ ጎረቤት በመኖሩ ሁለቱ ለግዜው ተለያዩ ጎረቤቶችም ፈነደቁ ያበሳጫል። ታዲያ ጎረምሶቹ አንዱ ከወደቡ እኛ ከተውነው እሱ አይጠቀምበትም በሚል የቅርብ ብስጭት ግመል ያጠጡበት በሚል ሀገር እና ትውልድ የገደለ የበደለ ውሳኔ ተከወነ። ታዲያ በዚያን ግዜ የበደል በደል ወደብ ማድረቅ ብቻ ሳይሆን በሁለቱም በኩል የተፋታው የተባረረው የሠው ቁጥር ቀላል አደለም። ታዲያ ታሪክ እንደሚነግረን ለሺግግር መንግስት ብሄር ብሄረሰቦች ይሰብሰቡ ተብሎ እና ምሁሮች ሲመክሩ ጀግናው ምሁሩ ሀኪሙ ፓይለቱ ትንቢት ተናጋሪው ፕሮፌሰር አስራት ሃገር አትገነጠልም ኢትዮጵያን እና ለኢትዮጵያኖች አይቀጅም አግባብ አደለም ሀገር ገንጣይ አትሁኑ ብለው በማለታቸው ጤነኛ የነበሩ በታሪክ ደግመን ለማግኘት የሚከብድ ምሁር በሚችሉት ሁሉ በማሠር እና በሺተኛ ሆነው ህክምና በመከልከል የተኙበት ክፍል ድረስ በመግባት የማይገባ መድሃኒት እንዲዎስዱ በማድረግ ሃገር ትልቅ ሰው እንድታጣ ተደረገ ሌላ ተጨማሪ ኪሳራ። የመጀመሪያው የአስራት ጥያቄዎችን ጠንከር ያሉ ምሁሮች ሲያነሱ ነፍጠኛ ጠባብ ወዘተ የሚል ተቀጣይ ስም በመስጠት እና ሺፍታ ምንጠራ በሚል በተለይ የሸዋን ምሁር እና አርሶ አደሩን ለሰው በማይገባ መልኩ በተለይ ቀተጉለት እና ቡልጋ በይፋትና ጥሙጋ በመንዝ እና ግሼ በመረሀቤቴ እና ደራ አካባቢዎች ያሉ አርሶ አደሮች ላይ የደረሰው በደል እዚህ ላይ መናገር ነገሩን ያቀለዋል ጥያቄው የነበረው ግን ሀገር አትገነጠልም ወደብ አልባ አንሆንም ነበር። ወንድሜ አይሂድብኝ አብረን እንሁን ማለት በገደል የተገፈተሩ የቅርብ አጎቶቼ ይገኙበታል። ይህ ሀገር አትገነጠልም የሚለው ኢትዮጵያዊ መንፈስ ወደ ሰላማዊ ትግል እና በተወሰነ መልኩ የትጥቅ ትግል በፕሮፌሰሩ መታሰር እና እንግልት የተበሳጩ 38 የሆኑ የሸዋ ልጆች ተናበው የወያኔን እና የሻቢያን ተላላኪ በየተራራው መፋለም ጀመሩ ወያኔም በወቅቱ ከነበሩት በአማራነት አማራ ግን የስረአቱ አጎንባሽ በነበሩ አመራሮች በየቤቱ እየገቡ የታጠቀውን ካስቀመጠበት እንዲወጣ ጠርገው ወደ ትግራይ እና ሌሎች አካባቢ እንዲጫኑ ተደረገ በማስረጃ ማቅረብ ስለሚቻል ይህሁሉ በደል አርሶ አደሩ ሀገሩን ሲነኩበት ወንድሙን ሲነጥሉበት ደስ ስላለው ጥያቄ ቢያቀርብም ዝም በል ብቻ ሳይሆን እየተለቀመ በደብረብረሃን እና አጣየ ሸዋሮቢት ማጎሪያ ተከማቸ። ታዲያ እነ ቄስ አክሊለ እነ ከፈለኝ አበበ እነ እንግዳሰው ጎሹ ሃምሣ አለቃ አየለ አበበ ይልማ እነጋሼ መንግስቱ እነ ቄስ የማነ እነ ጀግናው ዮሴፍ ያልተዘመረለት ጀግና እና የጀግኖች ጀግና አስማረ ዳኜ እነ ጋሼ ማሙሸት እና ከጅሩ ከመንዝ ከይፋት ከተጉለት ሳሲት እና ሰላድንጋይ መረሀቤቴ ምንጃር እና ከሰም ቡልጋ ቀጠቅላላው ከይፋት እና አንኮበር በመሰባሰብ የደብረብረሃን ማረሚያ እና ሰላድንጋይ በግፍ የታሰሩ አርሶ አደሮች እና ጀግኖችን እስር ቤቱን በላውንቸር መተው ሲከፈት የሻቢያ ሰራዊት እና የወያኔ ሰራዊት በጠባሴ ካንፕ ያንቀላፉ ነበር። ጀግኖቹ አንድም ጉዳት ሳይደርስባቸው ወደቀያቸው ይዘው ተመለሡ። ይህ ሁሉ ትግል ታዲያ ሀገር ወደብ አልባ አትሁን ወንድሞቻችን በሴራ አይገነጠሉም ነበር እንጂ ሌላ ፍላጎት አልነበረም። የተፈራው አልቀረም በማናለኝበት ሃገር ተቆረሰች ምን እሱ ብቻ ባህር በርም ዘመዶቻችንንም አጣን። መጥፎ ታሪክ አሁንም ተሼ በወደብ ጉዳይ ምን ትላለህ ላላችሁኝ ሁሉ ትውልድ በኢኮኖሚ ተወዳዳዳሪ እንዲሆን አብሮነት እንዲቀጥል ኤርትራውያን ወገኖቻችን በርትተው እኛም ተናበን አንድ ሃገር እንዲኖረን ቢሰራ ደስ ይለኛል። ከታሰበ ይሆናልም ይህ ነገር የሚዘገይ ከሆነ ደግሞ ኢትዮጵያ ባህር በር ያሻታል አደለም ባህር በር ብቻ ሳይሆን እስከዛሬ በወደቡ ያልተጠቀመችበትን ኪሳራ የመጠየቅ እድል እንዲፈጠር የሚያደርግ ትውልድ መፈጠሩ አይቀሬ ነው። ጦርነት አዋጪ አደለም አይመከርም ሰጥቶ መቀበል ወይንም ሌላ አማራጭ ይፈለግ ካልሆነ ግን ተዘግቶ የቆየ ኬሚካል አንድ ቀን መፈንዳቱ አይቀርም ልክ እንደኤርታአሌ ቀድንገት ሊፈነዳ ከደረሰ ለማቀዝቀዝ ሊከብድ ይችላል። ስለዚህ የአያቶቼ የአስራት አደራ አንድ ኢትዮጵያ ከነክብሯ ማቆየት እና የተዛመደ የተዋደደ ማህበረሰብ በእኩልነት የሚያምን ትውልድ መፍጠር ነው። ባህር በር ያሻናል ይህ የግሌ እና የአባቶቼ የአስራት አደራ ነው ባለሃገሩ ተሾመ ህዳር 13/3/2019 ዓም
ባለሐገሩ ተሾመ balehageru Teshome
Region: ET
Sunday 22 November 2026 13:42:11 GMT
Music
Download
Comments
ሲጶራ21✝️ (ተጉለቴዋ🦅) :
አስራታችን❤️
2026-11-25 13:47:30
0
ባለሐገሩ ተሾመ balehageru Teshome :
የአስራት አደራ
2026-11-22 15:05:06
0
forest tiger 🐅 :
yeshewa mhuranochi hulem le Ethiopian yimotalu
2026-11-22 16:51:01
0
To see more videos from user @teshomebalehageru, please go to the Tikwm
homepage.