@user6773691584006: #youtube #Love #پشتون_تاجیک_هزاره_ازبک_زنده_باد🇦🇫 #musteatinmycity

کليواله جلي
کليواله جلي
Open In TikTok:
Region: AF
Monday 23 November 2026 04:14:35 GMT
11
4
0
6

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @user6773691584006, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

የአህመድ ጀበል ሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳ አህመድ ጀበል
የአህመድ ጀበል ሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳ አህመድ ጀበል "ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ እንዴት ገባ?" በሚለው ርዕስ ላይ ብቻ አይደለም ሐሰተኛ ትርክት የሚፈጥረው። አንድ ወንድሜ በላከልኝ ቪዲዮ ላይ አህመድ ጀበል በንግግሩ እንዲህ ይላል፦ “መስከረም 30 ቀን 1401 ዓ.ም. ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች፣ ለ20 ዓመታት ሙስሊሞችን ሲበድልና ሲጨቁን የነበረውን ዐፄ ዳዊትን አንገቱን ቀልተው ያሸነፉበት የድል ታሪክ ነው”። ነገር ግን የግዕዝ መዛግብትን የመረመሩት ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ “ባሕረ ሐሳብ” በተሰኘው መጽሐፋቸው ገጽ 234 ላይ፣ “ንጉሥ ዳዊት (1374-1406 ዓ.ም.) ጥቅምት 9 ቀን ባዝራ ግንባሩን ረግጣ ገደለችው” ይላሉ። ስለዚህ በአጭሩ ዐፄ ዳዊት አንገቱ አልተቀላም፤ አልተቆረጠምም። መስከረም 30 ቀንም የድል ታሪክ አይደለም፤ በንጉሡ ላይ የተገኘ የድል ታሪክም የለም። ዐፄ ዳዊት የሞቱት ጥቅምት 9 ቀን እንጂ መስከረም 30 አልነበረም። አህመድ ጀበል እንደሚለው ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ንጉሡ ሙስሊሞችን አልጨቆነም። ደግሞም “20 ዓመት” የሚለው የነገሠበትን ዘመን ለማለት ከሆነ፣ ንጉሡ የገዛው ለ32 ዓመታት ነው። የነገሠበትን ዓመታት ለማወቅ ከ1374 ዓ.ም. እስከ 1406 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ በቀላል ሒሳብ ማስላት ይቻላል። ከውጭ ምሁራን ምስክርነት መካከል ደግሞ የሚከተለውን ማቅረብ ይቻላል "It is apparently in this context that we should also understand the circumstances of Dawit's death. In the fall of 1413, on his way back from a successful military campaign, he was kicked in the head by a horse and died. As his son, Zera Yakob wrote so plaintively, Dawit was victorious, (but) he never came back from the campaign against the enemy." (Kaplan, Steven. "Notes Towards a History of Aṣe Dawit I (1382–1413)." Aethiopica, vol. 5, 2002, p. 87.) በተጨማሪም ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት “Church and State in Ethiopia 1270-1527” በተሰኘው መጽሐፋቸው፣ የኢትዮጵያ የነገሥታት ዜና መዋዕልንና የቤተክርስቲያን ድርሳናትን በመጥቀስ ዐፄ ዳዊት ያረፉት ከፈረስ ላይ ወድቀው በደረሰባቸው ድንገተኛ አደጋ መሆኑን ጽፈዋል። ንጉሡ በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢ በነበሩበት ወቅት፣ የጋለቡት ፈረስ አሽቀንጥሮ ከጣላቸው በኋላ ጭንቅላታቸውን በመርገጡ ሕይወታቸው አልፏል። ከዚህ በፊትም አህመድ ጀበል “ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከ612-1700 የጭቆናና የትግል ታሪክ” በተሰኘው መጽሐፉ ገጽ 173 ላይ፣ “ንጉሥ ዘርአ ያዕቆብ... 'የነፍስ አባት' የሚባለውን ሥርዓት አስጀምሯል” በማለት የሐሰት ትርክት ሲያሰራጭ የነበረ ሰው ነው። ይህ የወሃቢይ አስተሳሰብ አራማጅ ግለሰብ፣ አባትንና ልጁን በሐሰት ታሪክ ፈጠራ ጠምዶ ይዟቸዋል። ዐፄ ዳዊት የዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ አባት ናቸው። አህመድ ጀበል በፋሽስት ጣሊያን የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስን ታሪክ ከመበረዝ አልፎ፣ የእሳቸው ያልሆነን ሌላ ፎቶግራፍ ሆን ብሎ በመጽሐፉ ውስጥ በማካተት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ታሪክ የሚያምታታና የሚበርዝ ነው። በአጠቃላይ የዚህ ግለሰብ መጻሕፍት ለታሪክ ጥናት በምንጭነት ሊያገለግሉ የማይችሉ የፕሮፓጋንዳ ጽሑፎች ናቸው።

About