@orthodox_bible_study: ብሉይ ኪዳን ማለት የቆየ፣ የጥንት ውል ወይም ስምምነት ማለት ነው ከክርስቶስ ልደት በፊት ያለውን የአንድ አምላክ አማኞች የሆኑትን የዕብራውያንን ታሪክ ይተርካል በውስጡም ብዙ የተስፋ ቃሎችን የያዘ ነው ስለ መሲሕ ክርስቶስ መምጣትም የተነ ገሩ ትንቢቶች በብዛት አሉበት ብሉይ ኪዳን ከሐዲስ ኪዳን ተነጥሎ አይታይም ምክንያቱም ብሉይ ኪዳን የሐዲስ ኪዳን ትንቢት ሲሆን፤ ሐዲስ ኪዳን የብሉይ ኪዳን ፍጻሜ ነው አዲስ ኪዳን በብሉይ ኪዳን ውስጥ አለ፣ ሆኖም ግን ነቢያት የተነበዩለት አምላክ ወልደ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘመኑንና ጊዜውን ቆጥሮ በተገለጠ ጊዜ ስውር የነበረው ሐዲስ ኪዳን ተገልጿል በዚህ ምክንያት ብሉይ ኪዳን በሐዲስ ኪዳን ፍጻሜ እንዳገኘ እንገነዘባለን ብሉይም ሲባል ሕጉ ሁሉ ወይም ቃል ኪዳኑ ሁሉ ያረጀ ነው ማለት አይደለም፤ ግን ዘመኑ አርጅቷል፤ ብዙ ጊዜም አልፏል ስለዚህም በዚያን ጊዜ የነበረ መሆኑን ለማስረዳት ሲል ብሉይ ኪዳን ይለዋል የብሉይ ኪዳን መሥዋዕትም በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ መተካቱን ያመለክታል የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከተጻፉበት ጊዜ፣ ከያዙት አሳብና ከአጻጻፋቸው ሁኔታ አንጻር በ4 ምድቦች ይከፈላሉ የሕግ (የኦሪት) መጻሕፍት፣ የታሪክ መጻሕፍት ፣የመዝሙርና የጥበብ መጻሕፍት፣ የትንቢት መጻሕፍት ናቸው #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር #viralvideo #VoiceEffects #goviral #fyppp
📚
Region: ET
Thursday 26 November 2026 09:27:56 GMT
Music
Download
Comments
seni💗27 :
😍😍😍🙏
2026-11-26 17:23:50
0
Grez man :
🙏🙏🙏
2026-11-26 12:35:12
0
zershe :
❤️❤️❤️🙏🙏🙏
2026-11-26 13:19:35
0
ወሳኝ :
🥰🥰🥰
2026-11-26 17:12:15
0
To see more videos from user @orthodox_bible_study, please go to the Tikwm
homepage.