@3in1liy: ዛሬ በታክሲ ውስጥ እየሄድኩ አንድ ነገር አሰብኩኝና... እንዴት ነው ሰው አንድን ነገር እንዳይሆንለት እየጸለየ በተመሳሳይ ጊዜ እሱ እንዳይሄድበት እየተጣበቀ የሚኖረው? እንዴት ነው «ጌታ ሆይ፣ የእኔ ያልሆነውን ከሕይወቴ አስወግድልኝ» ብለን እየጸለይን፣ እሱ ሲያስወግደው ግን የልባችን ክፍል እንደተወሰደብን የሚሰማን?? አንዳንዴ እግዚአብሔር የጠየቅነውን መልስ ሲሰጠን መልሱን እንኳን ለመለየት እንቸገራለን። ምክንያቱም መልሱ እንደ ምኞታችን አይመጣም! እኛ መቆየትን እንሻለን ፤ እርሱ ግን መሄድን ይፈቅዳል። እኛ መከፈትን ስንጠብቅ ፤ እሱ ግን በርን ይዘጋል... አስቂኝ ነው አይደል? ለመዳን እየጸለይን ከተጣበቅነው መለየት ሲመጣ ለመዳን የጸለይን እኛው መለያየቱን እንደ መጥፋት እንቆጥረዋለን...! አንድን ሰው አስቡትማ...አንድ ጫማ በጣም ወድዶታል። ነገር ግን ጫማው እግሩን እየጎዳው ነው። ስለዚህ ህመሙ እንዲቆም መተው ይገባዋል። እኛም ብዙ ጊዜ የምንሰራው ይህንኑ ይመስለኛል ፤ የሚያምን ነገር ቢሆን እንኳን የምንወደው ከሆነ መተውን እንቃወማለን!! 'ይገርማል '! እኔ ብዙ ነገሮች ከሕይወቴ ሲወጡ አዝኛለሁ። አንዳንዶቹን ለማጣት ዝግጁ አልነበርኩም። አንዳንዶቹ በልቤ ውስጥ የወደፊት ቦታ እንኳን አዘጋጅቼላቸው ነበር። ሄዱ። ከእነሱ ጋር ያሰብኩትም ነገር ሄደ። እኔ ግን ቀረሁ። እናም ብዙ ጊዜ ያልገባኝ አንድ ነገር ነበር፤ ለምን የምወደው ሁሉ አይቆይም..? አንድ እውነት ግን ተረዳሁ...የምንወደው ሁሉ የሚጠቅመን አይደለም። የምንፈልገው ሁሉ የተዘጋጀልን አይደለም። እና በሕይወታችን ውስጥ የነበረ ሁሉ እስከ መጨረሻ አብሮን መጓዝ አይጠበቅበትም! ምናልባት የእግዚአብሔር ምሕረት አንዳንዴ በሚሰጠን ነገር ብቻ አይደለም፤ ከእኛ በሚያርቀውም ነገር ውስጥ አለ። እኛ የማናየውን እሱ ያያል፤ እኛ የማንረዳውን እሱ ያውቃል.. አንዳንድ ነገሮችን ስናጣ ሕይወታችን ባዶ የሆነ ይመስለናል፤ ምናልባት ግን እግዚአብሔር በሌላ ነገር ለመሙላት ቦታ እያዘጋጀ ነው! አንዳንዱ በመሄዱ የተጠበቀ ሕይወት አለ! የቀረውን በምስጋና ተመልከቺ፤ የሚመጣውን በእምነት ጠብቂ! ምክንያቱም እግዚአብሔርን የምንጠይቀው ሁሉ እንዲቆይልን አይደለም፤ ለእኛ የሚሆነው እንዳይጠፋብን እንጂ ስጀመር እግዚአብሔር በኛ አይደራደርም!!😔 . . . . . . #christiantiktok #viral #ethiotiktok #fypシ
𝑙𝑖𝑦🪺
Region: ET
Friday 27 November 2026 20:41:51 GMT
Music
Download
Comments
Meklit ✍️💌 :
Yessssss... endewm sometime tselye salchers nw react miyadergew 😊 he is truly Great!
2026-11-28 09:45:32
0
@Ruti :
በሚያስፈልገኝ ሰዓት ትክክለኛ ምክር ❤️🙏
2026-11-28 08:24:53
4
Afnan🌺 :
I know this feeling well. 🥺
Blessed🔥
2026-11-28 06:36:07
0
@emumelaku :
Betam
2026-11-28 04:15:50
1
Hatersata :
100%lik nesh tebareki egziabher bemelkam neger hiwoten endemimolawu akalew
2026-11-28 09:09:25
0
temu :
አሜን! ❤️አንዳንድ ጊዜ የምንለየው ነገር ሁሉ ኪሳራ አይደለም፤ አንዳንዱ ከማናየው አደጋ የሚያድነን የእግዚአብሔር ጥበቃ ነው። ስለዚህ የተዘጋውን በቁጭት ሳይሆን በእምነት፣ የሄደውንም በሐዘን ብቻ ሳይሆን በመታመን መቀበል እንማር። የእግዚአብሔር ፈቃድ ከምኞታችን በላይ ጥበብ አለው። 🙏❤️እግዚአብሔርን በሙሉ ልብህ ተማመን፤ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ።
ምሳሌ 3፥5
2026-11-28 05:57:08
2
ሜሮን🌸 :
ስሜቱን አውቀዋለሁ 🙆🫂
2026-11-28 08:59:51
0
Hani :
ምን አይነት መንፈስ ያለዉ መዝሙር ነዉ🙏🙏
2026-11-28 09:16:20
0
Fevenita🌹 :
Betekekel
2026-11-28 10:05:17
0
Derina Tasew :
Ewnet
2026-11-28 10:16:37
0
የንጉስ ልጂ። :
እግዚአብሔር ይመስገን።
2026-11-28 07:02:11
0
leta🦋 :
💯 Right 😂🥰🥰🥰
2026-11-28 09:39:01
0
Temu rasu :
:I know this feeling well. 🥺
Blessed🔥
2026-11-28 06:38:07
0
Taurus ♉ :
wow በእውነት ድንቅ መልዕክት 🙏🙏🙏🙏🙏
2026-11-28 06:57:46
0
Miss Tina :
absolutely true
2026-11-28 08:14:09
0
Betty Endale :
2026-11-28 10:15:27
0
Nardi Ma✝️ :
🙏🙏🙏🙏
2026-11-28 07:31:04
0
To see more videos from user @3in1liy, please go to the Tikwm
homepage.