@signore1989: «ጸርሐ ገብርኤል እምሰማይ ዘይብል ጻዑ ተቀበሉ መጽአ ወልደ አምላክ ለቢሶ ሥጋ ማርያም ወጼዊዎ ነፍሳተ ዓለም» ​ትርጓሜ፦ «የአምላክ ልጅ የማርያምን ሥጋ ለብሶ፣ የዓለምን ነፍሳትን ማርኮ ከሲኦል ነጻ አውጥቶ መጥቷልና፤ ‘ውጡና ተቀበሉት’ እያለ ገብርኤል ከሰማይ ጮኸ።» ​ይህንን የቅዱስ ያሬድን ማኅሌታዊ ምስጋና ምሥጢር በጥላና በአማን፣ በምሳሌና በፍጻሜ እንመለከተዋለን። በዚህ ምድር ሥርዓት አንድ ኃያልና አፍቃሪ ንጉሥ ሀገሩን ሊያጠፋ፣ ሕዝቡን ሊያረክስና ሊያስጨንቅ የተነሣን ክፉ ጠላት ለመውጋት ወደ ጦር ግንባር ቢዘምት፤ ሕዝቡ በሥጋትና በጭንቀት ሆነው የጦርነቱን ወሬ ይጠባበቃሉ። ያ ንጉሥ ግን ግንባር ለግንባር ገጥሞ፣ የጠላቱን ኃይል ሰባብሮ፣ ተማርከው የነበሩትን ወገኖቹን ነጻ አውጥቶ፣ በታላቅ ምርኮና ክብር ወደ ከተማው ሲመለስ አዋጅ ነጋሪው ቀድሞ እየሮጠ ይመጣል። አዋጅ ነጋሪው በከተማው አደባባይ ቆሞ በከፍተኛ ድምፅ፦ «እናንተ የከተማ ነዋሪዎች ሆይ! ፍርሃታችሁ ተወግዷል፣ ጠላታችን ወድቆአል፣ ንጉሣችን ድል አድርጎ ተመልሷልና ወጥታችሁ በደስታ ተቀበሉት!» እያለ ይጮኻል። ያን ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ከቤትና ከመንደሩ እየወጣ፣ በእልልታ፣ በጭብጨባና በታላቅ ሐሴት ንጉሡንና የተመለሱትን ምርኮኞች ለመቀበል ይተማል። ​ይህ የምድራውያን ነገሥታት ታሪክ በብሉይ ኪዳን ጥላና ምሳሌ ሆኖ ሲታይ የነበረ ሲሆን፣ የነገሥታቱ ድል ግን የጊዜያዊ ሥጋዊ ነጻነት ምሳሌ ነበር። አብርሃም፣ ጌዴዎን፣ ዮፍታሔና ዳዊት ያዳኑአቸው ወገኖች ቆይተው እንደገና በሥጋ ሞተዋል፤ እውነተኛውና የዘለዓለሙ የነፍሳት ምርኮ ግን የተፈጸመው በዓለሙ መድኃኒት በኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ነአምን በአሐዱ አምላክ
ነአምን በአሐዱ አምላክ
Open In TikTok:
Region: DE
Saturday 28 November 2026 06:49:58 GMT
89
31
1
1

Music

Download

Comments

To see more videos from user @signore1989, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About